DIRSANE TIBEB
195 subscribers
70 photos
2 videos
5 files
32 links
This channel is your visual arts Utopia. Dive deep into the world of film, TV, and art creation. From BTS secrets to practical how-to's, I'll share my insights and experiences 🎥 🎬

Join me @addispupi on this artistic journey & explore the magic of art.
Download Telegram
በሚቀጥለው ፀሑፋችን እስከምንገናኝ ለወዳጆቻችሁ ይህን የጥበብ-ምህዳር በማጋራት ትተባበሩን ዘንድ እና የጥበብ እንቅስቃሴያችንን እንድታግዙን በትህትና እየጠየቅን መልካም ግዜ ተመኘን::
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
የታሪክ መተንበያ ዶሴ
Story Clock Notebook
_______________
ባለፈው ስለ ታሪክ አይነቶች እና ታሪኩን መፃፍ ከመጀመራችን በፊት ዋና ዋና ነጥቦችን ዝርዝር በተራ ቁጥሮች ማስቀመጥ እንዴት እንደሆነ አይተናል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የምናየው ደግሞ እንዴት የታሪክ ሀሳባችንን ወደ ፅሑፍ እንቀይረዋለን የሚለውን ነው፡፡ ከዛ በፊት ግን የብዙዎቻችን ችግር ወይም እንደ ደካማ ጎን ሊወሰድ የሚችል ጉዳይ አለ : ከተሰጥዖ ወይም ልምድ ማነስ ሊከሰት ይችላል ይህም የታሪኩ መጀመሪያ ፣ መሐል ወይም መጨረሻ ከሦስቱ አንዱ ወይም የሁለቱ ሐሳብ ሊመጣልን ይችላል፡፡ ታዲያ ቀሪውን ክፍል ወይም ገቢር/Act ለመድፈን ፍዳችንን እናይ ወይም የይድረስ ይድረስ ልንሞላውና ልንፅፈው እንገደዳለን፡፡ ይህን እና ተመሳሳይ ሌሎች ክፍተቶችን/ችግሮችን ለመቅረፍ እንደ ማነሳሻ ቀጣዩን ማስተማሪያ ይዘንላቹ ቀርበናል፡፡

የታሪክ መተንበያው የሚሰራው ተመጣጣኝ/Symmetry የሆኑ መስመሮችን በመጠቀም በአንደኛው ገቢር ያለን አንድ ክስተት ከሌላ ገቢር ካለ ተቃራኒ ወይም መልስ በሚመስል የተከሰተን ክስተት በማገናኝት ነው፡፡

እንግዲህ ይሄን አሰራር ከዚህ ቀጥሎ በተሰጡት ምሳሌዎች እና የአሰራር ረጂ ጥናቶች እናዳብራቸዋለን፡፡
——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ሦስት የገቢር አይነቶች
Story Clock - 3 Act Structure
_______________
ብዙ የተሳካላቸው የፊልም እና የቴያትር ፀሀፊያንና አጥኚዎች ፁሑፋቸውን በሦስት ክፍል ወይም ገቢር መጀመሪያ ፣ መሀል እና መጨረሻ በማለት የተዋቀረ አርገው ይከፍሉታል፡፡ ይህ ሲባል ግን ግድ በቅደም ተከተል መቀመጥ አለባቸው ማለት አይደለም የፈጠራ ችሎታችንን ተጠቅመን የራሳችንን አቀማመጥ ልናሲዘው እንችላለን፡፡

ገቢር 1/መጀመሪያ (ትውውቅ)
ይህ ክፍል መሪ ገፀ-ባህሪውን የምናስተዋውቅበት ሲሆን የሚኖርበት አለም ፤ ፍላጎቱን ፤ ከሌሎች ጏደኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዘተ መደበኛውን/የተለመደውን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ በመጨረሻም ገቢሩ ማለቁን ለማሳየት ወሳኝ የሆነ ክስተት/የመጀመሪያ ግጭት/ እንፈጥራለን ይህም ለገፀ-ባሕሪው ካአሁን በኅላ ኑሮው እንደቀድሞ እንደማይሆንና እንደተቀየረ የሚገነዘብበት ይሆናል፡፡

——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ሦስት የገቢር መዋቅሮች (የቀጠለ)
3 Act Structure
_______________

• ገቢር 2/መሀል (መጋፈጥ) •

በዚህ ክፍል ደግሞ በመጀመሪያው ገቢር የፈጠርነውን የመጀመሪያ ግጭት የምናግልበት/የምናጦፍበት ገቢር ሲሆን ዋና ገፀ-ባሕሪው ግጭቱን ለመፍታት ሲታገል የምናሳይበት ይሆናል አክሎም ወደመፍትሄው የተቃረበ እና ግጭቱን የፈታው እስኪመስለው ድረስ እንሄዳለን እውነቱ ሲገለጥ ግን ጭራሽ ግጭቱን እንዳባሰው እና እንደተሸነፈ የሚረዳበት ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ይሄ ገቢር ማለቁን ለማሳየት ገፀ-ባሕሪው አንድ ትልቅ ነገር እንዲገነዘብ እናደርጋለን ይህም ግጭቱን ለመፍታት መጀመሪያ እራሱን መጋፈጥ እና የፍርሃቱን ጥግ ማሸነፍ እንዳለበት ይህ ሁለተኛውን ግጭት ይፈጥርልናል ወይም እንደ ለውጥ ቦታ(Turning Point) እንቆጥረውና ገፀ-ባሕሪው ለውጥ ይጀምራል፡፡

• ገቢር 3/መጨረሻ (መፍትሄ) •

አሁን በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ግጭት የፈጠርናቸውን የመጨርሻው ጡዘት የምናደርስበት እና እስካሁን ለተነሱት ግጭቶች መፍትሄ የምንሰጥበት ወይም የምንፈታበት በተጨማሪም ለእስካሁኖቹ ጥያቄዎች መልስ የምንሰጥበት ይሆናል

አስተውሉ ይህ ለታሪክ አፃፃፍ እዲረዳ ተደርጎ እንደ ማነሳሻ/ማስተማሪያ የተሰራ ነው እንጂ ህግና ደንብ ወይም ግዴታ አይደለም፡፡

በሚቀጥለው ከምሳሌዎች ጋር እና ለናንተም ለመለማመድ እንዲረዳ በPdf የተዘጋጀውን የታሪክ መተንበያ ዶሴ ይዘን እስከምንመለስ መልካም ጊዜ 🎩
——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
የአቬንጀርስ ፊልም በታሪክ መተንበያ ሲተገበር
The Avengers (Story Clock)
Screenplay by (Joss Whedon & Zak Penn)
_______________
There are 4 symmetry story lines in the first phase of the Marvel universe saga. Play with the resource we gave you earlier, practice with your favorite films. Most of Steven Spielberg films are story clocked like this, we will post some relevant resources like this in the future.

Until we meet again 🎩 Adios!
——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ይሄን ያውቁ ኖሯል?
Did you know this?
_______________
አሁን የምንገኝበት ወቅት የሚዛን ህብራተ ክዋክብት በሰማይ ላይ የሚታዩበት ሲሆን ይህን ስያሜ ያገኝው እንደ ቀደምት ሊቃውንት አባቶቻችን በብራና ላይ ከትበው እንዳስቀመጡት የቀኑ ጊዜ/ሰአት እና የማታው ሰአት እኩልነታቸውን ለመግለፅ ነው::

Our ancestors named this season’s constellation which is visible on the sky mean this month stars of the balance(ሚዛን Mizan), or Libra , those where the days and nights being equal.

የምልክቱ ተራ ቁጥር : ፯
Sign Number : 7

ህብረ-ኮከብ ስም : ሚዛን
Constellation Name : Libra

ወቅት : ከመስከረም ፲፪ - ጥቅምት ፲፪
Season : September 23 - October 23

ግዜ : ፴ ዕለት ከ፲ ኬክሮስ
Time : 30 Days
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
የጁራሲክ ፓርክ ፊልም በታሪክ መተንበያ ሲተገበር
Jurassic Park (Story Clock)
Screenplay by (Micheal Crichton & David Koepp)
_______________
There are 2 simple & 2 bounced symmetry story lines in the first part of Jurassic Park sequel. Play with the resource we gave you earlier, practice with your favorite films.

Research • Practice • Write • Re-Write

As always we will post resources like this in the future.

Until we meet again 🎩 ሰላም ለኩልክሙ!
——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ቀጣዩ ምንድነው?
___________
ወደቴሌቪዥን ጣቢያ ለመሄድ በታክሲ ውስጥ ነበርኩ፡፡ የታክሲ ሹፌሩ እየሳቀ "አስታወስከኝ?‛" ሲል ጠየቀኝ፡፡ አላስታወስኩትም ነበር፡፡ ያም ቢሆን እንዲህ ሲል ቀጠለ፡፡

"ከስድስት ወራት በፊት ይሄንኑ ታክሲ ተሳፍረህ ስትጓዝ ሥራህ ምንድነው ብዬ ስጠይቅህ ድራማዎች እንደምትፅፍ ነግረኽኝ ነበር፡፡ ሚስቴ 'ፀሐፊዎች ቀድሞውኑ ከመፃፍ ተሰጥዖ ጋር ይወለዳሉ' ስትል እኔ ደግሞ 'በትምህርት የሚያገኙት ችሎታ ነው' እያልን እንደምንከራከር ነገርኩህ፡፡ እናም አንተን 'ፀሐፊዎች ይወለዳሉ ወይስ በትምህርት ይፈጠራሉ?' ብዬ ስጠይቅህ ሰዎች ብዙ የሚማሩት ነገር እንዳለ ጠቅሰህ አንድ ምሳሌ ሰጠኽኝ፡፡ የክዋኔ፣ የውሳኔና የጭብጥ ታሪክ ዓይነቶች እንዳሉ ነበር የነገርከኝ፡፡ ትክክል ነኝ?"

"አዎ! ሶስት ዓይነት ናቸው፡፡ ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አለህ፡፡"

"አልረሳዋቸውም፡፡ እንዴት እንደማስታውሳቸው ታውቃለህ? ዘውትር ምሽት ከሚስቴ ጋር በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ፊልሞችን እያየን ፊልሙ በየትኛው የታሪክ ዓይነት እንደተፃፈ በመገመት እንወራረዳለን፡፡ አንድ ልጅ ፍቅረኛውን ከኤሌክትሪክ ወንበር ፍርድ ለማትረፍ ዱካው የጠፋ ምስክሩን የሚፈልግ ከሆነ የክዋኔ ታሪክ ይሆናል፡፡ አይሆንም? መጀመሪያ ላይ ሚስቴ ያታለልኳት መስሏት ነበር፡፡ ቆይታ ግን ተረዳች፡፡ አሁንማ ከኔም በልጣ ታሪኩ ከመጠናቀቁ አስቀድማ ዓይነቱን ትናገራለች፡፡ እባክህ ሌላ የምታስተምረኝ ካለ ዝግጁ ነኝ፡፡ ቀጣዩስ ምንድነው?"

"ቀጣዩስ ምንድን ነው?" ጥያቄ በታሪክ አፃፃፍ ውስጥ እጅግ አስደሳቹ አካል ነው፡፡ ቀጣዩን ምዕራፍ ከመጀመርህ/ሽ በፊት ግን እንደታክሲ ሹፌሩ እናተም የምታዩትና የምትሰሟቸውን የታሪክ ዓይነቶች ለይታቹ መመደብ ተለማመዱ፡፡ ይህ የጥሩ ታሪክ ፀሐፊ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

•ታሪክን የመፃፍ ጥበብ• በእንየው ደቻሳ

Until we meet on the next post
የጥበብ ምህዳራችንን ለወዳጆ ያጋሩልን ፤ ቤተሰባችን ከፍ እና ሞቅ እንዲል ይርዱን
StayTuned!
😳
————————————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
Have a Lit🔥Knowing Folks 🙌🏽
ግጭት (Conflict)
• ታሪክን የመፃፍ ጥበብ •
————————
"I’m Yankee Doodle Dandy" እና “Give My Regards to Broadway” በተባሉ ዘፈኖች የሚታወቀው George M. Cohan የተዋጣላቸው ሙዚቃዊ ኮመዲዎችን ፅፏል፡፡ ኮሃን ለመድረክ ትርዒቶቹ ሁሉ የሚጠቀምበት አንድ ቀላል የአፃፃፍ ስልት አለው፡፡

💡ገቢር አንድ፡ ጀግናውን ዛፍ ላይ እዲወጣ አድርግ
💡ገቢር ሁለት፡ ቋጥኝ እንዲናድበት አድርግ
💡ገቢር ሦስት፡ ከዛፍ ላይ እንዲወርድ አድርግ

በሌላ አነጋገር መሪ ገፀ-ባህሪውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከቶ ከችግሩ ለመውጣት ሲታገል ማሳየት ማለት ነው፡፡

•የፈለገውን ለማግኘት ሲታገል ማሳየት•

ታሪክ ፀሐፊያን መሪ ገፀ-ባህሪውን ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጠንካራ ትግል ግጭት/Conflict/ ይሉታል፡፡ ግጭት ለማንኛውም ታሪክ አስፈላጊ ቅመም ነው፡፡ ግጭት ከሌለህ ታሪክ አይኖርህም፡፡ ግጭት ከሌለህ ተመልካችም አታገኝም፡፡ እኛ በተመስጦ ማየት የምንፈልገው መሪ ገፀ-ባህሪህ ችግሩን ሲፈታ፤ ውሳኔ ሲያሳልፍ ወይም ለሕይወቱ ወሳኝ የሆነ እውነታን በመረዳት ዙሪያ ከተቃዋሚው ጋር ሲጋጭ ነው፡፡

💡 የመፅሔት ታሪክ ፀሐፊዎች የሚጠቀሙበት ተወዳጅ የአፃፃፍ ስልት እንሆ . . .

1️⃣ አንባቢያኑ ግለሰቡን እንዲወዱት አድርግ
2️⃣ ግለሰቡ የሆነ ነገር አንዲሻ አድርግ
3️⃣ መንገድ ላይ መሰናክል አድርግ
4️⃣ መሰናክሉን እንዴት እንደሚያልፈው አሳይ

ከዚህ ስልት በጣም አስፈላጊው የትኛው ነው? መንገድ ላይ መሰናክል አስቀምጦ እንዴት እንደሚያልፈው ማሣየት ነው፡፡ እስቲ ያሻውን ነገር በእጁ ለማስገባት ሲታገል እንመልከት፡፡

ከፍተኛ ፍላጎትና ከፍተኛ ተቃዋሚ ሲጋጩ ከፍተኛ ድራማ ይፈጥራሉ፡፡ አንድ ፀሐፊ ለአሳታሚዎች የሚልካቸው ፅሑፎች ሁሉ "ግጭቱ አንሷል!" ከሚል የአርታኢው አስተያየት ጋር ተመላሽ ሆነውበት ነበር፡፡
በመጨረሻ ፀሐፊው "እሺ ለግጭት ጥሩ ምሳሌ ስጠኝ፡፡" ሲል አርታኢውን ይጠይቀዋል፡፡

📣 አርታኢውም ይመልሳል 📣
"ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ ሁለት ብቻ፡፡ አንደኛው ጀት አብራሪ መሆን ሲፈልግ ሌላኛው ደግሞ የባህር ጠላቂ መሆን ይመኛል፡፡ ነገር ግን ሁለቱ መንትዮች የተጣበቁ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ አየህ... ግጭት የሚባለው ይሄ ዓይነቱ ነው፡፡"

ግጭት ለታሪክ የልብ ትርታው ነው፡፡ ያለሱ አይንቀሳቀስም፡፡ ግጭት በብዙ መንገዶች ይፈጠራል፡፡

በሚቀጥለው ፅሑፋችን እጅግ የተለመዱትን ሶስት መንገዶች እንመለከታለን፡፡

Until we meet next time, as always :
Research • Practice • Write • Re-Write
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
Have a Lit🔥Days Folks 🙌🏽
ግጭት (የቀጠለ)
፩ኛ •ሰው ከሰው ጋር•
————————
የመጀመሪያው መሠረታዊ ግጭት ሰው ከሰው ጋር የሚያደርገው ነው፡፡ ሁለት ጠንካራና ብልህ ተዋጊዎች ፊት ለፊት ሲፋጠጡ ተመልካቹ ይረካል፡፡ ግጭቱም ይጦፋል፡፡ አንደኛው እያጠቃ ፤ ሌላኛውም የመልሶ ማጥቃት እየሰነዘረ ከተዋጊዎቹ አንዱ ባላንጣውን እስኪያሸንፍ ድረስ ግጭቱ እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ወንዶች ለገንዘብ፣ ለስልጣን፣ ለሴትና ለሌላም ዓላማ እሽቅድምድም በሚያደርጉባቸው ታሪኮች ውስጥ ይህ ዓይነቱ ግጭት የጀርባ አጥንት ነው፡፡

መሪ ገፀ-ባህሪው ገንዘብ፣ ሥልጣን፣ ደረጃ፣ ሴት ወይም ሌላ ግብ ይኖረውና ድንገት አንድ ሰው መንገድ መሃል ቆሞ ከጉዞው ይገታዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ሰው አሸንፎ ያለመውን ነገር ማሳካት ይኖርበታል፡፡

📌ብዙዎቹ የሆሊውድ ፊልሞች ቀጣዩን የአፃፃፍ ስሌት ይጠቀማሉ . . .

1. ልጁ ከልጅቷ ጋር ይገናኝና ፍቅር ይይዘዋል
2. ባላንጣው ልጁን ወደጎን አድርጎ ልጅቷን ይወስድበታል
3. ልጁ በድፍረት ይነሳና ባላንጣውን ገጥሞ ይረታዋል
4. በመጨረሻ ልጁና ልጅቷ ወደምትጠልቀው ጀምበር እጅ ለእጅ ተያይዘው ይፈሳሉ

🎭ይህ ሁሉ የተለመደ አይደል?

በነገራችን ላይ አብዛኛው በElzie Crisler Segar የተፈጠረው "Popeye the Sailor" ካርቱን ፊልሞች አፃፃፍ ስልት ይሄው ራሱ ነው፡፡ ወደፊት የፓፔዬ ካርቱኖችን በቲቪ ስትመለከቱ ቀጣዮቹን ነጥቦች ታገኛላቹ፡፡

⭕️ ፓፔዬ Olive Oylን እንዳያት ያፈቅራታል
⭕️ ግዙፉና ፈርጣማው ባላንጣው ይመጣና ፓፔዬን አሽቀንጥሮ ኦሊቭ ኦይልን ይወስድበታል
⭕️ ፓፔዬ ቅጠሉን ቀቅሎ ይበላና ወደር በሌለው ጥንካሬ ባላንጣውን ከመሬት ይደባልቀዋል
⭕️ ፓፔዬና ኦሊቭ ኦይል ወደ ጀምበሯ ይወርዳሉ

ሰው ከሰው ጋር የሚያደርገው ግጭት ወንድ ከሴት፣ አባት ከልጅ፣ አማት ከአማች/ምራት/ ወይም በማንኛውም ጥንዶች መሃል የሚፈጠረውን ግጭትም ይጨምራል፡፡ አንድ ሰው ከወገንተኞች ወይም ቡድን ጋር ሊጋጭ ይችላል፡፡

በሰዎች መሃል ግጭቱን የፈጠራቹ እንደሆነ ባላንጦቹ ተመጣጥነው የተሳሉ መሆናቸውን አረጋግጡ፡፡ በጠንካራና ለፈስፋሳ ሰዎች መሃል የሚደረገውን ትጥቅ አልባ ውጊያ ማን መመልከት ይፈልጋል? ውጤቱ ምን እንደሚሆን እናውቃለን፡፡

📌በትግላቸው አቻ የሆኑ ባላንጦች አገናኝቶ አንደኛው ሌላኛውን አሳሩን ካላበላው በቀር የማይመለስ አድርጎ ማቅረብ የተመልካችን ስሜት በእጅጉ ይስባል፡፡

በሚቀጥለው ፅሑፋችን ቀሪዎቹን "ሰው ከሕሊናው ጋር" እና "ሰው ከተፈጥሮ ጋር" የሚያደርጉትን ግጭቶች እንመለከታለን፡፡

Until we meet next time, as always :
Research • Practice • Write • Re-Write
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ግጭት (የቀጠለ)
፪ኛ •ሰው ከህሊናው ጋር•
————————
ሁለተኛው መሠረታዊ ግጭት ሰው ከሕሊናው ጋር የሚያደርገው ግጭት ነው፡፡ ይህ ሰው ከገዛ ራሱ አእምሮ ጋር ሲታገል ያሳያል፡፡

📌 አንድ ሰው የሚያምንበት የህይወት መመሪያ ይኖረዋል፡፡ ይሁንና ከዚህ መመሪያው ውጭ በሆነ ተቃራኒ መንገድ ለመራመድ የተገደደ ጊዜ ሰው ከሕሊናው ጋር ግብግብ ይገጥማል፡፡

፫ኛ •ሰው ከተፈጥሮ ጋር•
————————
ሶስተኛውና መሠረታዊው ግጭት በሰውና በተፈጥሮ ኃይል መሃል ይፈጠራል፡፡ ይህ ዓይነቱ ግጭት ሰዎች የሚያንገበግብ ሙቀት ካለበት በረሃ ወይም በድን የሚያደርግ በረዶ ከተጋገረበት ጠፍ መሬት ጋር ሲታገሉ የሚያሳዩ ታሪኮች ውስጥ ይገኛል፡፡

📌 መርከበኞች ከማዕበል ጋር ሲተናነቁ፤ ገበሬዎች ከድርቅ ጋር ሲታገሉና በሌሎች ማብቂያ በሌላቸው የተፈጥሮ ቀውሶች ሰዎች ህይወታቸው ሲናጥ ማሳየት የዚህ ግጭት ዓይነተኛ መለያ ነው፡፡

በሚቀጥለው ፅሑፋችን ግጭቶችን በጥምረት እንዴት እንደምንጠቀም እና አቀራረቡን ከጥሩ ምሳሌ ጋር ይዘን እንመለሳለን፡፡

Until we meet next time, as always :
Research • Practice • Write • Re-Write
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
https://www.youtube.com/watch?v=eImeyxf91vI

ከዚህ በፊት ቪዲዮ ኤዲት(Video Edit) አርገው ያውቃሉ? ካረጉስ ቪዲዮአችሁን ለማሳመር አንዳንድ እንቅስቃሴ ያላቸው ፅሑፎች እና ሞሽን ግራፊክሶች(Motion Graphics) ለመጠቀም ሞክረዋል? እሱን ለማሳካት ኤዲት ከምታረጉበት አፕሊኬሽን ውጪ ለመጠቀም ተገደዋል? እንግዲ ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ይሄ ቪዲዮ ሁነኛ መፍትሄ ይዟል።

ቪዲዮ ኤዲት ስታረጉ አንዳንድ አኒሜሽኖችን(Animations) ብትጠቀሙ ቪዲዮዋችሁን በጣም ማራኪ እና ልታስተላልፉ ያላችሁትን መልክት በማገዝ ተመልካቻቹ ሳይሰላች ፍሬ ሃሳባችሁን ለማየት ፍላጎቱ ይጨምራል።

በዚህ ቪዲዮአችን የቪዲዮ ኤዲቲንግ አንዱና መሰረታዊ ክፍል የሆነውን አኒሜሽንእናያለን፣ እንደ እድል ሆኖ ይህን ቪዲዮ ለመጀመሪያ ግዜ ለቀቅን እንጂ ከዚ በፊት የሚቀድሙ ወይም ስለ ኤዲቲንግ መሰረታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫዎች እንደ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ምንድነው? የሚሉ ፤ ኤዲት ማድረጊያ አፕሊኬሽኑ(Application) እና መሳሪያዎችስ የሚለውን በሚቀጥለው ቪዲዮአችን ይዘን እንመጣለን።

አዲስ የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማረግ በየሳምንቱ የምንለቃቸውን ቪዲዮዎች እዩ።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መፃፍ • መቅረፅ • ኤዲት ማድረግ
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb

👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል (5 ደቂቃ)
https://youtu.be/KK5ugUuXOiE
የፊልም መግቢያ እና መውጫ ክሬዲትቶች
• Movie Credits and Sequences •

የፊልም መግቢያ እና መውጫ ላይ ያሉ የProdaciton ባለሞያዎች ስም ወይም ርዕስ አጻጻፍን ጥበባዊ እና ሳቢ በሆነ መንገድ ሲታይ አስተውላቹ ታቃላቹ ?

ይህ ጥበብ በጣም ማራኪ እና ለፊልማችን ወይም ለሰራነው ተራኪ ቪዲዮ እንደልዩ ግብአት ያገለግላል፤ ይህ ስራ የራሱ የሆነ አሰራር ሂደት እና ባለሞያም አለው።

ዛሬ ይህን አሰራር በጥልቅ እና በምሳሌ የBlack Panther ፊልም መጨረሻ ላይ ያለውን End Credits መሰረት በማድረግ የምንሰራ ይሆናል።

ይህን ስራ ለመስራት የRed-Giant Product የሆነውን 3D-Form እና Shine Pluginsእንጠቀማለን። ጨምረንም እንዴት background እንደሚፈጠር, plugins እንደምንጠቀም, camera setting, animation እና text እንደምንሰራ እናያለን።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል (11 ደቂቃ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Civilization VI Ethiopian Pack
—————————
ከሰሞኑ የሲድ ማየርስ ሲቪላይዜሽን 6 (Sid Meier’s Civilization VI) የኢትዮጲያ ትልቅ እዲስ ምሽግ ማለፊያ ጥቅል የመጪው ሐምሌ 16 /ነገ በይፋ ይመረቃል::
ይህንም አስመልክቶ ብዙ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የመጀመሪያ እይታ ሲያጋሩ ነበር::

እኛም ባደረግነው የቅድመ አወጣጥ ግምገማ ከዚ ቀደም የተሰሩትን የተለያዩ የእውነታ እና ተከታታይነት ስተቶች እንደተስተካከሉ እና አዲስ ግብአቶችም እንደተጨመሩ አስተውለናል:: ለምሳሌ ያክል በሲቪላይዜሽን 5 ላይ የሚኒልክን ስም በሀይለስላሴ ፊት እና ድምፅ ነበር የተሰራው በዚህኛው ላይ ግን በደንብ አስተካክለውታል እስኪ በዚህ ጥቅል ውስጥ ከተካተቱትን ዋና ዋና ነጥቦች እናንሳ:
- የተሻሻለ የኢትዮጲያ ግዛት
- ባህል እና እምነት
- የኦሮሞ ፈረስ ጋላቢዎች
- ገፀባህሪ ከጥሩ የአመራር ብቃት ጋር
- የድብቅ ማህበረስቦች
- የቅርሶች ጥናት ቤተ መዘክር
- አዲስ የሚኒስቴሮች ምክርቤት

እነዚህን ሁላ ፊቸርስ ተጠቅመው በተዋበ እና በጥሩ ሁኔታ በተገነባው የአምመራር ስነጥበብ ላይ የሚያተኩረውን ጨዋታ በገራሚ የማጅቢያ ሙዚቃ በመታገዝ ኢትዮጲያን እንዴት ይመሯት ይሆን?

ለማንኛውም እኛም ይህን የመጀመሪያ እይታ እንጋብዞ ....

ማስፈንጠሪያው https://m.youtube.com/watch?feature=youtu.be&v=YCVa4LYYmoo
—————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
Checkout the official soundtrack for Civilization 6 :
Listed below are time stamps for game level and segment chapter tracks

0:00 - Ancient Era
2:59 - Medieval Era
7:54 - Industrial Era
12:11 - Atomic Era

It’s really amazing hearing our motherland distinct music genre in orchestrated full vibes such a way that lifting up those “Tizita and Bati” with the first Blues theme. 👏🏽👏🏽👏🏽

Composer : Geoff Knorr
Live Krar: Minale Bezu
Tenor Saxophone: Getachew Mekurya

Link Below 👇🏽
—————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb

https://youtu.be/mXTsJ5bjG-c
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Live Recording and Composing
———————
On the video Geoff Knorr(Composer)
Arranging and Recording soundtrack for official Civilization 6 Ethiopia Pack: New Fortress Pass

Enjoy !!
———————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
ጽሑፎች በፕሪሚየር ፕሮ
• Texts in Premiere Pro 2020 •


ጽሑፎች ለተለያዩ የቪዲዮ ስራዎቻችን እንደግብአት ልንጠቀማቸው እንችላለን። ለምሳሌ ያክል የሰራነውን ቪዲዮ ርዕስ ልንጽፍበት እንችላለን፤ ወይንም የቪዲዮችን መጨረሻ ወይም መጀመሪያ ላይ የሚታዩትን የባለሞያዎች ዝርዝር እና አንዳንዴም ለምንሰራው ታሪክ ገላጭ የሆኑ ምስለ ትንተናዎችን ለመጻፍ እንጠቀምበታለን።

በዚህ ክፍል ጽሑፎችን እንዴት እና በምን መሳሪያ/Tools ተጠቅመን ፕሪሚየር ፕሮ 2020 ላይ እንደምንጽፍ፣ መለከ ፊደላትን እንዴት እንደምንቀይር እና እንደምናስውብ እናያለን ጨምረንም በፊልሞች ላይ ያሉ የመጨረሻ የተዋናዮች እና ባለሞያዎች ዝርዝር እንዴት ወደላይ እንዲወጣ እንደምናረግ በተግባር እየሰራን በመጨረሻም ሌሎች ጠቃሚ የጽሑፍ አጠቃቀሞችን እናያለን።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/dfavWIYRbgY
ማስክ እና ትራክ በፕሪሚየር ፕሮ
• Mask and Tracking in Premiere Pro •

አንዳንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የአልኮል እና ያልተከፈለባቸው/አለአግባብ የሆኑ ማስታወቂያዎችን በደበዘዘ ምስል ሲሸፈኑ/ሲደበቁ አይታችሁ ታቃላችሁ? ይህ አሰራር ወይም ዘዴ ማስኪንግ(Masking) ተብሎ ይጠራል።

እነዚህ ምስሎች ወይም ቁሶች ተንቀሳቃሽ ሲሆኑ ለመሸፈን ሊያስቸግሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ያክል የመኪና ታርጋ ሊሆን ይችላል ወይም የሰው ፊትም ሊሆን ይችላል፤ የፖሊስ ፕሮግራሞች ላይ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎችን ፊታቸው ብለርድ/ብዥታ/ ሆኖ አይታቹ ይሆናል እና በአጭሩ እነዚህን ቴክኒኮች አጭር እና ቀላል በሆነ ዘዴ ምንም ተጨማሪ ፕለጊን/Plugin ሳንጠቀም እናያለን።

በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ
መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል

https://youtu.be/VbpB3CvZdr0
ካፒቴን ማርቬል ርዕስ አሰራር
• Captain Marvel Title Sequence •

ከሰሞኑ Marvel Studios የካፒቴን ማርቬል 2ትን ፊልም ዳይሬክት የሚያደርግ ሰው ቀጥረዋል እሱን ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት የሰራነውን የካፒቴን ማርቬልን የመጀመሪያ ፊልም የማስታወቂያ ርዕስ አሰራርን የVideo Copilot ምርት የሆኑትን Element 3D እና Optical Flareን በመጠቀም ለመስራት እንሞክራለን።
በሚቀጥለው ቪዲዮ እስክንገናኝ

መለማመድ • መስራት • ድጋሚ-መስራት
————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
👇🏽 ቪዲዮውን ከስር ያገኙታል


https://youtu.be/rfCd7Cp4pgc
ሦስት የገቢር አይነቶች
Story Clock - 3 Act Structure
_______________
ብዙ የተሳካላቸው የፊልም እና የቴያትር ፀሀፊያንና አጥኚዎች ፁሑፋቸውን በሦስት ክፍል ወይም ገቢር መጀመሪያ ፣ መሀል እና መጨረሻ በማለት የተዋቀረ አርገው ይከፍሉታል፡፡ ይህ ሲባል ግን ግድ በቅደም ተከተል መቀመጥ አለባቸው ማለት አይደለም የፈጠራ ችሎታችንን ተጠቅመን የራሳችንን አቀማመጥ ልናሲዘው እንችላለን፡፡

ገቢር 1/መጀመሪያ (ትውውቅ)
ይህ ክፍል መሪ ገፀ-ባህሪውን የምናስተዋውቅበት ሲሆን የሚኖርበት አለም ፤ ፍላጎቱን ፤ ከሌሎች ጏደኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዘተ መደበኛውን/የተለመደውን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ በመጨረሻም ገቢሩ ማለቁን ለማሳየት ወሳኝ የሆነ ክስተት/የመጀመሪያ ግጭት/ እንፈጥራለን ይህም ለገፀ-ባሕሪው ካአሁን በኅላ ኑሮው እንደቀድሞ እንደማይሆንና እንደተቀየረ የሚገነዘብበት ይሆናል፡፡

——————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb