DIRSANE TIBEB
195 subscribers
70 photos
2 videos
5 files
32 links
This channel is your visual arts Utopia. Dive deep into the world of film, TV, and art creation. From BTS secrets to practical how-to's, I'll share my insights and experiences 🎥 🎬

Join me @addispupi on this artistic journey & explore the magic of art.
Download Telegram
Channel created
Hello 👋🏽 Everyone !
ሰላም ለኩልክሙ!

Welcome to Dirsane Tibeb Channel

We are Ethiopian underground art societies giving and making visual art resources & how-to-trip tutorials for anyone who wants to tell stories, make entertaining & educational stuffs.

We will use our forgotten language ግእዝ combining it with አማርኛ and English.

Our categories include:
• Film, Documentary & Game Writing
• Directing
• Video & Music Editing
• Visual Effects
• BTS (Behind the Scene)
• PopCulture

በቅርቡ የጥበባት ፅሑፋችንን እና ምስለ-ትርክታችንን እስከምንጀምር ድረስ ለወዳጆቻችሁ ይህን የጥበብ-ምህዳር በማጋራት ትተባበሩን ዘንድ እና የጥበብ እንቅስቃሴያችንን እንድታግዙን በትህትና እየጠየቅን መልካም ግዜ ተመኘን::

Again Welcome to Our Channel &
Thanks for Joining Us!


StayTuned! 😳
————————————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
Channel photo updated
ሰላም ቤተሰቦች
This week’s • How To • blog is Script Writing, we will start by telling you how stories can be setup and build.
Thanks for your patience!
————————————
• How To • Script Writing
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
•ከዕለታት አንድ ቀን•
Once Upon A Time
__________________________________________
#ScriptWriting - #StorySetup

ሰዎች ሌላው ሰው ወይም ገፀባህሪ ችግር ውስጥ ገብቶ ከዚያ ከችግሩ ጋር ሲታገል ማየት ያስደስታቸዋል፡፡ ልክ በሀይለኛ ፍጥነት ከሚጋልቡ ፈረሶች መንጋ እንደገባች ጫጩት የምታክል ጨቅላ ህፃን ለመውጣት የምታረገው ጥረት ፤ የቡጢና የትግል ግጥሚያዎችን እንደሚከታተል ታዳሚ ወይም በቲቪ ድራማና ፊልም ታሪክ እንደሚስቅና እንደሚያለቅስ ተመልካች ዓለም በሙሉ አንድ ታጋይ ማየትን ይወዳል፡፡ ተመልካቹ ከጀግናው ወገን በመሆን ትግሉን እንዲያሸንፍ ይፈልጋል፡፡

Ted Ray/ቴድ ሬይ ከሥራ መልስ ቤት ሲገባ ባለቤቱ እንዲህ ስትል ጠየቀቸው . . .

•”ቴድ ዛሬ ምሽት ወደ ሲኒማ ቤት አንሄድም እንዴ?"
•"አንሄድም!" አለ ቴድ፡፡ "በጣም ደክሞኛል፡፡ እስቲ ለዛሬ ምሽት እንኳ (James Bond) ጄምስ ቦንድ ያለኔ ድጋፍ ሽጉጥ ይተኩስ፡፡"

ይህ አባባል (BBC Entertainment TV) ላይ ይቀርብ ከነበረ የኮሜዲ ትርዒት የተወሰደ ሲሆን ዓላማው ምዕራባዊያን የፊልም ተመልካቾችን ለመንካት ነበር፡፡

ተመልካቾቹ ራሳቸውን ከፊልሙ ዋና ባለታሪክ ጎን በማሰለፍ ችግሩንና አደጋውን እየተካፈሉ ሕይወቱን በመኖር ጠላቶቹን አሸንፎ ልጃገረዷን በማዳን ከረጢት ሙሉ ብር ተሸክሞ እስኪጠፋ ድረስ አብረውት ይሆናሉ፡፡

የመዝናኛ ቢዝነስ የተገነባው ባብዛኛው በዚህ ሃቅ ላይ ነው፡፡ አንድ ሰው ችግር ሲጋፈጥ ለተመልካች ማሳየት ቀልብ ይስባል፡፡ ለዚህ ነው ታሪኮችን የምንወደው፡፡ ምክንያቱም ታሪክ ማለት ባጭሩ አንድ ሰው ችግር ሲያጋጥመውና ችግሩን ለመፍታት ሲታገል የሚፈጥረው ዝርዝር ነገር ማለት ነው፡፡

•ታሪክን የመፃፍ ጥበብ• በእንየው ደቻሳ

Until we meet on the next post
የጥበብ ምህዳራችንን ለወዳጆ ያጋሩልን ፤ ቤተሰባችን ከፍ እና ሞቅ እንዲል ይርዱን
StayTuned! 😳
————————————————
Join The Underground Art Movement!
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
Have a Lit🔥Knowing Folks 🙌🏽
• Recommendation of the Week •
የሳምንቱ ጥቆማ
This week’s 📖 📽 worth checking
📌 Million Dollar Baby (By Clint Eastwood)
📌 Gladiator (By Ridley Scott)

Links for actual scripts below👇🏽
አንድ ገፀ-ባሕሪ ~ አንድ ችግር
A Character ~ A Problem
________________
#ScriptWriting - #StorySetup

ታሪክ የግድ አንድ ትልቅ እክል/ችግር የገጠመው አንድ ትልቅ ገፀ-ባሕሪ ይፈልጋል፡፡ ገፀ-ባሕሪው ችግር የሚገጥመው ካልሆነ የምትፅፉት ወይም የምታወሩት ነገር ቀልድ፣ አጋጣሚ፣ የገፀባህሪ ጥናት ወይም መግለጫ እንጂ ታሪክ ሊሆን አይችልም፡፡

ይህን መሠረታዊ ደንብ በመስበር ታሪካችሁን ማበላሸት ካልፈለጋችሁ በቀር ለአንድ ከባድ ችግር አንድ ሁነኛ ገፀ-ባሕሪ ብቻ መፍጠር፡፡ ዋናዋ ገፀ-ባሕሪ ከችግር ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት የበለጠ ለማክበድ ብቻ ከሆነ ተጨማሪ ገፀ-ባሕሪያትና ችግሮች መፍጠር ይቻላል፡፡ ዋናዋ ገፀ-ባሕሪ ችግሩን እራሷ እንድትፈታ መተው እንጂ በመጨረሻው ደቂቃ ፖሊሶች 👮🏽‍♀️እንዲረዷት ማስገባት ትክክል አይደለም፡፡ ይህ ተመልካቾች ይቅርታ የማይሰጡት ስህተት ነው፡፡ እነሱ የሚሹት ዋናዋ ባለታሪክ በገዛ ጥንካሬዋ፣ ሐሳቧና ብልጠቷ ችግሩን እንድትፈታ ነው፡፡

በሚቀጥለው ጽሑፋችን: በአግባቡ ከተጠቀምንበት በእጅጉ ጊዜን ሊቆጥቡ የሚችሉ ሦስት የታሪክ ዓይነቶችን ይዘን እንቀርባለን፡፡

እስከዛው ድረስ ለወዳጆቻችሁ ይህን የጥበብ-ምህዳር በማጋራት ትተባበሩን ዘንድ እና የጥበብ እንቅስቃሴያችንን እንድታግዙን በትህትና እየጠየቅን መልካም ግዜ ተመኘን::
————————
Join The Underground Art Movement!

ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
• Have a break have a plant •
Plant your Print for a Green Legacy
🌳አረንጓዴ አሻራ እናኑር🌳
———————————
📷addispupi

ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
• Recommendation of the Week •
የሳምንቱ ጥቆማ
This week’s 💿📖 worth checking
📌 Celtx Win 2.9 (Script Writing Software)
📌 Braveheart (By Mel Gibson)

Files for App & Screenplay below👇🏽