DevVoltz Technology company
509 subscribers
175 photos
4 videos
2 files
181 links
DEVVOLTZ TECHNOLOGY PLC is a software and technology company dedicated to building innovative digital solutions, empowering young talents, and transforming ideas into real-world products.

www.devvoltz.com
Download Telegram
ስንቶቻችው ChatGPT 5.2 መለቀቁን ሠምታችዋል?

Open AI GPT-5.2 የተሰኘውን ሞዴሉን ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ሞዴል እንደ Coding እና ሒሳብ ባሉ ዘርፎችም ላይ መሻሻሉም ተገልጿል።

በዚህም GPT‑5.2 Instant, Thinking እና Pro የተባሉ ሞዴሎችን አስተዋውቋል። GPT‑5.2 Thinking ለprofessional እና Real world ለሆኑ ፕሮጀክቶች ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል።

Check ማድረግ ከፈለጋችሁ የchatGPT አፕሊኬሽን ክፈቱና የ+ ምልክቱን ነክታችሁ model ውስጥ auto, Instant እና Thinking የሚሉ አማራጮች አሉላችሁ። check አድርጉት።

#DevVoltz #ChatGPT5.2 #AI #TechInsights #MachineLearning #Innovation #Coding #DeveloperLife #FutureTech #AIRevolution
2
AI ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በትክክል እንዴት ነው የሚሰራው?

ChatGPT፣ Midjourney ወይም የዩቲዩብ Recommendation Algorithm አጠቃላይ አለማችንን እየቀየሩ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሲስተሞች በስተጀርባ እንዴት እንደሚያስቡ እና ውሳኔ እንደሚሰጡ ጠይቀው ያውቃሉ?

ብዙ ሰው AI ልክ እንደ ሰው አእምሮ በራሱ የሚያስብ ይመስለዋል፤ ነገር ግን እውነታው ከዚህ የተለየ ነው። የ AI አሰራር በ 3 መሰረታዊ ደረጃዎች ይጠቃለላል፡

1. መረጃ መሰብሰብ (Data Input)
AI ያለ መረጃ ምንም ነው። ልክ አንድ ህጻን ልጅ አካባቢውን እያየ እንደሚማረው ሁሉ፣ AI መጀመሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ መረጃዎች (ጽሑፎች፣ ምስሎች፣ ድምጾች ወይም ኮዶች) ይመገበዋል።

2. ቅጦችን መፈለግ (Pattern Recognition)
ይህ የ AI ዋናው አስማት ነው! ኮምፒውተሩ የተሰጠውን ግዙፍ መረጃ በማጥናት በመረጃዎቹ መካከል ያለውን ተመሳሳይነትና ግንኙነት (Patterns) ይፈልጋል።
ምሳሌ፡ ለአንድ የ Machine Learning ሞዴል 100,000 የድመት ፎቶዎችን ካሳየነው፣ የድመትን ጆሮ፣ አይንና አፍንጫ ቅርፅ ለይቶ ማጥናት ይጀምራል።

3. መተንበይ እና መገመት (Prediction & Generation)
አዲስ መረጃ ሲሰጠው ቀድሞ ከተማረው በመነሳት ውጤቱን ይገምታል ወይም አዲስ ነገር ይፈጥራል። ChatGPT ቀጣዩን ቃል የሚገምተው፣ Midjourney አዲስ ምስል የሚስለው በዚህ ቀድሞ በተማረው Pattern መሠረት ነው።

የአሁኑ ዘመን የ AI ሞዴሎች የሚገነቡት የሰው ልጅ አእምሮ የነርቭ ሴሎችን (Neurons) አወቃቀር በመኮረጅ ነው። መረጃዎች በተለያዩ ደረጃዎች (Layers) ውስጥ ያልፋሉ፤ እያንዳንዱ ደረጃ ደግሞ መረጃውን ይበልጥ እያጠራውና እየተረዳው ይሄዳል።                                    

#ArtificialIntelligence #MachineLearning #SoftwareEngineering #DevVoltz
1