ድምፀ ተዋሕዶ
11.4K subscribers
3.49K photos
86 videos
189 links
ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል።

የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን
ለታማኝ መረጃዎ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ መንፈስ ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት /ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ፦
« ንሕነ ሕያዋን እለ ንተርፍ አመ ምጽአተ እግዚእነ ንትመሠጥ በደመና ምስሌሆሙ ኅቡረ ከመ ንትቀበሎ ለእግዚእነ ውስተ አየር »
« እኛ ሕያዋን ሆንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ። ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ጌታን በአየር ለመቀበል ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። ስለዚህ እርስ በእርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ» በማለት የክርስቶስ ዕርገት ለምዕመናን ዕርገት መሠረት መሆኑን ገልጾልናል (፩ተሰ. ፬፡፲፯)። ወደ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱም « በሥጋ የተገለጠ፣  መንፈስ የጸደቀ፣  ለመላእክት የታየ፣  በአሕዛብ የተሰበከ፣  በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ» በማለት ልደትን እንደ ዘር ዕርገትን እንደ መከር አድርጎ ገልጾልናል። (1ጢሞ.3፥16)
ወርሐ ዘር የመከር ጊዜ ነው፡፡ ገበሬ በጎተራ ያለውን እህል እያወጣ ሲዘራ ከላይ ዝናም ከታች ጭቃውን ታግሶ ነው፡፡ በመከር ጊዜ ያን የዘራውን ምርት በጥፍ ሲያገኝ ደስ ይለዋል መከራውን ይረሳዋል፡፡ ምነው በጨመርኩበት ይላል የክርሰቶስም ልደቱ ስለኛ መከራን ለመቀበል ነውና፥ በሥጋ የተገለጠ ብሎ ትሕትናውን አሳየ፡፡ ዕርገቱን ግን በክብር ያረገ ብሎታል፡፡ ምክንያቱም የሰውነትን ሥራ ፈጽሟልና ድል ነስቶአልና ይህን በሥጋ ዕርገቱን ስናስብ ለምን ዕለቱን ተነሥቶ እለቱን አላረገም ለምንስ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ ቆየ ቢሉ ፡ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ የቆየው ትንሣኤው በግልጽ እንዲረዳ ደቀ መዛሙርቱንም መጽሐፈ ኪዳንን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምር ዘንድ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ » ብሏል። (ዮሐ.3፥13)

ጌታችን ሞትን በሥልጣኑ ከሻረ፣ ሙስና መቃብርን ካጠፋ፣ የትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በዕለት ሰንበት ከሞት ከተነሣ በኋላ በምድር ላይ መቆየቱ የማያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ በምድር ቆይቷል፡፡ በነዚህም የ40 ቀናት 3 ጊዜያትጉባኤ ዘርግቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ " ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ " እንዲል ወንጌላዊው ዮሐንስ (ዮሐ.21፥14 ) እነዚህንም 3 ጉባኤያት የተባሉትን ሊቃውንት አባቶቻችን፡-
1ኛ በዕለተ ዕሁድ በዕለተ ትንሣኤ
2ኛ በአግብኦተ ግብር /በዳግም ትንሣኤ/
3ኛ በጥብርያዶስ ባሕር
የተገለጡ ጉባኤያት መሆናቸውን አመሳጥረው ያስተምሩናል።
ጌታችን በ40 ቀናት ውስጥም መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ/” ብሏል፡፡ ‘ዐረገ’ መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው፡፡
አንድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በእመቤታችን ጀርባ መታዘሉንም ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናትና። ከማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል” (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው።
ቤተ ክርስቲያናችንም በሥርዓተ ቅዳሴዋ “ላዕለ ይኩን ኅሊናክሙ በሰማይ የሀሉ ልብክሙ አእምሩ ኀበ ትቀውሙ ስምዑ ቃለ ጽድቅ ወአስምዑ ዜና ሰናይ” እያለች ዕርገቱን ታሳስበናለች።

ሃይማኖተ አበው "ዐርገ እግዚአብሔር በቃለ ቀርነ መዊእ ወኢይቤ አዕረግዎ አላ ለሊሁ ዐርገ ወኢፈቀደ መራሔ ፍኖተ፥ እስመ ከመዝ ኢክህለ ኤልያስ ይዕርግ በዝንቱ መካን ነኪር አላ ኀይላት አዕረግዎ ኀበ ተአዘዙ ወቃለ እግዚአብሔርሰ ዋሕድ ለሊሁ ዐርገ በሥልጣኑ እስመ እግዚአ ኀይላት ውእቱ። ወበእንተ ዝ ይቤ ሉቃስ ወንጌላዊ በመጽሐፈ ግብር እስመ አርዳኢሁ ያንቀዐድዉ ኀቤሁ እንዘ የዐርግ ሰማየ ወኢይቤ አዕረግዎ ወኢሂ ጾርዎ እስመ መካን ኀበ ዐርገ ዘዚኣሁ ውእቱ"  ይላል። ሃይ. አበ. ዘዮ. አፈ. ፷፯፡፲፪-፲፬

ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ
ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ
ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ
ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ
ጰራቅሊጦስሃ መንፈስከ ፈኑ።

ሰላም ለዕርገትከ በዘባነ መብረቅ ወነጎድጓድ፤
ከመ ትፈኑ መንፈሰከ በአምሳለ ነፋስ ወነድ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመንግሥትከ ዋሕድ፤
ይቤሉከ ለለ ዕለቱ ሰማያውያን ነገድ፤
መንግሥቱ ዘለዓለም ወምኩናኑኒ ለትውልደ ትውልድ፡፡

ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። (መዝሙር 67፥ 33)

መልካም በዓል

𝐀𝐬𝐜𝐞𝐧𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐨𝐮𝐫 𝐋𝐨𝐫𝐝, 𝐆𝐨𝐝 𝐚𝐧𝐝 𝐒𝐚𝐯𝐢𝐨𝐫 𝐉𝐞𝐬𝐮𝐬 𝐂𝐡𝐫𝐢𝐬𝐭
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አርባ ምንጭ ከተማ እንዲህ ባለ ድምቀት ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በልጅነት ክብር ተቀብላ ተባርካለች።

ሁሌም ሙቀቱ የማይለየው የደቡብ ህዝብ ዛሬም አባቶቹን በክብር ተቀብሏል።በተለይ አርባ ምንጭ ብዙ ያልተደረገለት ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ሀገረ ስብከት ነው።

ድምፀ ተዋሕዶ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM