ጥልቅ ሀሳቦች
2.32K subscribers
691 photos
24 videos
6 files
36 links
ጥልቅ ሃሳቦች ...
Download Telegram
ልትፅፍ ትፈልጋለህ ግን ያለህ ስሜት በፅሁፍ ደረጃ ሊገለፅ እንደማይችል ይሰማሀል። ልትናገር ትፈልጋለህ ነገር ግን አሁንም ቢሆን የትኛው የቃላት ስዳሬ ውስጥህን ከያዘው ውጥረት አይገላግለውም። ልትጮህ ትሻለህ እሱም ቢሆን የልብ አድርስ አይደለም። በስተመጨረሻም ግን ዝም ማለት ህመም ቢኖረውም እርሱ እንደሚሻል እና እንደሚበልጥ ትረዳለህ 😐 ከንቱ አለም


#ውዱ_ብዕረኛ
💔7💯3
“እንደሌሎች ልጆች አልነበርኩም፤ ሲከፋኝ ከእናቴ እቅፍ ይልቅ ወደ አልጋዬ መሄድ እመርጣለሁ..”

                      —ቫን ጎግ
💔12🔥1
እኔ ጦርነቱን አልፈልግም!!❞
❝ እኛ ጦርነቱን አንፈልግም!!❞
❝የገዛ ወንድሞቻችን ላይ አንዘምትም!!❞

ትናንት ማለትም ሁለት ሺህ አስራ ሁለት አመተ ምህረት.......ፌዘኛው  መንግስትና የትግራይ አመራሮች መከላከያ ሠራዊትን ማዕከል አድርገው በሰሩት ድራማ ህዝብ ሁለት ጎራ ይዞ ተሰለፈ ! ትግራይ እና ኢትዮጵያ ፤ ከሀዲ እና የተካደ ሠራዊት ፤ ባንዳ እና ሀገር ወዳድ ፤ ጡት ነካሽ እና ክብር መላሽ ተብለው ተከፈሉ በሁለቱም በኩል ከአራቱም ማዕዘናት ወንድም ወንድሙን ሊወጋ ፈለሰ  ሰሜናዊ ፣ ምዕራባዊ ፣ ምስራቃዊ እና ደቡባዊ ኢትዮጵያ  ከ ሰሜናዊ ፣ ምዕራባዊ ፣ ምስራቃዊ እና ደቡባዊ ትግራይ ጋር ገጠመ የሆነው ሆነ ከሦስት እና አራት አመታት ኋላም #ይብቃ ተባብለው ይህንን ቴአትር ለመቋጨት ደቡብ አፍሪካ ሄደው ተስማማን ብለውን መጡ። በተስማሙ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደ ቅጠል የረገፈው ወታደር እና እንደ እሳትራት ሄዶ የተማገደው ወጣት ደም ትዝ በማይላቸው መልኩ አደባባይ ላይ ተሰብስበው ወረቀት እና ዋንጫ ተሸላልመው ተሳስመው አብረው ጨፍረው። በአንድ ጉድጓድ ቅበሩን በአንድ ነጠላ እናስቀድስ በአንድ ብርጭቆ ካልጠጣን ሲሉ ከርመው በስተመጨረሻም ፍስሐ ኮነ ብለው ተለያዩ።

.....................................................

አሁን ዘንድሮ ❗️
የለመደች ጦጣ ይሉት ነገር ሆኖባቸው ሁለቱም አካላት አፈሙዝ ለመደገን መውዜር ለመማዘዝ የጎሪጥ እየተያዩ በል ሞክር ልሞክርህ በል ግጠመኝ ልክህን ላሳይህ አይነት ዛቻ እየተወራወሩ እያየን ነው። የእናቶች እንባ ከአይናቸው ስርጉድ ላይ ሳይደርቅ ፣ የአባቶች ሐዘን ከልባቸው ጓዳ ሳይከተት ፣ በዚያኛው ዙር የተጎዳው ወጣት  በክራንች መሄዱን እንኳ በቅጡ ሳይለምደው ፣ ወንድሟን ያጣች እህት እህህህህ ብላ አልቅሳ እርሟን ሳታወጣ እነዚህ ቴአትረኛ አመራሮች መልሰው ህዝብ ለመማገድ ተነሱ። ያሳዝናል ተምሬ አልፎልኝ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ እቀመጣለሁ ያለውን ወጣት አዋግተው የቢሮ ተሽከርካሪ ወንበር ያሰበውን የአካል ጉዳተኛ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ አስቀሞጠውት ሲያበቁ ፤ ከአንድ ቤት አምስት እና ስድስት ሰው አርግፈው ሲያበቁ ፤ ድንገት ደጇን አንኳኩቱው "ልጅሽ ተሰውቷል " ብለው የነገሯት እናት እንባዋን ሳታብስ፤ ይጦረኛል ያለው ልጁን የተነጠቀው አባት ካለፈ ትካዜው ሳይድን፤ የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ካጋጠመው  የስነልቦና ረብሻ ሳያገግም በድጋሚ ህዝቡን " ና ተማገድ " ሊሉት በርቀት እየተያዩ ዳርዳርም እያሉ ይገኛሉ።
ካለፈው ያጣነው ውድ ወንድሞቻችንን ውድ እህቶቻችንን ነው ተጨማሪ ይህ ፌዘኛ አመራር ለሚጫወተው ጨዋታ የምንገብረው ሰው የለንም። ያጣነው የመከላከያ ሠራዊት ሀይላችንን ነው እየተራበ እየተጠማ ወንድሙን ውጋ ስለተባለ ሲወጋ የነበረ ሀገርን ሚጠብቅ ሀይልን በዚያም በኩል አዲስ የምናዋጣው ሠራዊት አይኖረንም። ሚሰሩ እጆች ናቸው ዛሬ ክራንች የጨበጡት። የሚሰሩ እግሮች ናቸው ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠው መራመድ የተሳናቸው። ታዲያ ለማን ደስታ ነው የገዛ ወንድሜን ምወጋው? ለዚህ ደም ለጠማው አመራር? ለዚህ በሚጫወተው ጨዋታ ላይ ጦርነት እንደ #ጆከር ካርድ ጨዋታ ለማስቀየሪያ ለሚጠቀም ብሽቅ መንግሥት ? ለማነው ምንፋጀው ለማነውስ ወንድማችንን የምንሰዋው?ጦርነት ትርፉ እልቂት ነው ወንድማማቾች ነን ልንተላለቅ አይገባንም። ነገ መልሶ ለሚሳሳም እና ለሚተቂቀፍ አመራር የገዛ ወንድሞቻችንን ነብስ አናጠፋም ለነሱ መነገጃ የምንሆንበትም ምክኒያት የለም እንንቃ❗️

ተጨማሪ ህዝብ ፤ ተጨማሪ ወጣት፤ተጨማሪ ወታደር ፤ ተጨማሪ ወንድሞች፤ ተጨማሪ እህቶች የምንገብርበት ምክኒያት የለንም❗️❗️

°
ግደፍዋ ዛ'ደይ ግደፍዋ ....
ዘይሓወየ ቀስሊ ገና ለዋ
ግደፍዋ ዛ'ደይ ዛ'ዕንበባ
ክንደይ ጀጋኑ'ድያ አረኪባ
ትፈልጦ'ያ ምረት ናይቲ ኩናት
ክንደይ'ዳ ከፊላ እቶም ዕሸላት
ገና'ኳ ሓዘን ዘይዓጸወት
ማዳ ኮይኑ ገጻ ዝጸምለወት 🎶
°


#ጦርነት_ይብቃን
#ጦርነት_አንፈልግም

በያላችሁበት ቦታ እያጋራችሁት ❗️
🔥5💊21👌1
ያዘግመዋል
እንጂ መተናነስ
ሰብቆት እንዳቀረቀረ፤
ምን ፍቱን ሊዳኘው
ቁስሉን ላፈቀረ።


Unknown poet
💔11
💯
💯9
😁
🤣9
ዶክተሮች የቱንም ያህል ቢጥሩ ከበሽታው በላይ ተስፋ መቁረጣችን ነው የሚገድለን።
💔9💯4
ጥልቅ ሀሳቦች
Photo

​ እኔ ማን ነኝ ? ማንነቴ ምንድን ነው? ከየት ነኝ ? .. የመሳሰሉ ጥያቄዎቹን  ብዙ ጊዜ ራሳችንን ጠይቀነዉ እናውቃለን ። ለነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ወደ ውስጣችን ጠለቅ ብለን መልስ ከመፈለግ ኣንፃር ወደ ውጫዊው ዓለም ማንነታችንን ለመፈለግ ብለን በዚያ ጠፍተን እንቀራለን፣ በዕለት ተዕለት ውሎአችን ውስጥ መኖራችንን እንገልጸዋለን። ለምሳሌ “እኔ እንደ እገሌ እኮ ነኝ፣ ከእከሌ ጋር እሰራለሁ፣ ይህንን እወዳለሁ፣ ያንን እጠላለሁ” በማለት ማንነታችንን እንዘረዝረዋለን። ይህ ግን እኛ ማን እንደሆንን ከማሳወቅ ይልቅ ፤ ከእኛ ውጪ ያለውን ዓለም እንዴት እንደምንመለከትውና እንዴት እንደተቆጣጠረንና ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ብቻ ይገልጻል።

​የማንነታችን እውነተኛ ምንጭ ለማወቅ የምንፈልግ ከሆነ ወደ ውስጣዊ ህይወታችን መመለስ፣ ከራሳችን ጋር መነጋገር ፣ የህልውናችን ጥልቀት ማሰላሰል ያስፈልገናል። ማንነታችን ማለት ከውጭ  የምንሰራውን ስራ፣ የምንለብሰው ልብስን ፣ የምናሳየው የውጭ ገጽታም  አይደለም፤ ማንነት(identity ) ከነዚህ ሁሉ ነገሮች  በላይ ነው ፥ ማንነት ማለት በኣጭሩ የውስጣዊ ህይወታችን ይወክላል።  ይህ ማንነታችን ጊዜንና ቦታን አይወስነውም ፣ በሰዎች አስተያየትም አይለካም !።
​ የማንነታችን ጥያቄ ራሳችንን  ባልጠየቅነው ቁጥር፣ ህይወታችንን ከራሳችን ኮምፓስ ዉጪ ይሆናል፥ በትርጉም ባልተሞላ ህይወት ራሳችንን እናገኘዋለን ፥ ህልውናችን ከማለፍና ከመጥፋት ያለፈ ምንም ትርጉም አይኖረውም።

​ስለዚህ  እውነተኛ ማንነታችንን ማግኘት የምንችለው ከህልውናችን ጥያቄዎች ጋር ፊት ለፊት ስንፋጠጥ ነው። ማንነታችንን ከማግኘታችን  በፊት ህልውናችንን ለምን እንደምንኖርና ምን እንደምንሰራ በመጠየቅ ልንጀምር ይገባል። ዓላማ የሌለው ህይወት መሬት ላይ  እንደ  ወደቀ  ዛፍ ነው፡  ስር የለውም፣ ፍሬም አያፈራም። ማንነታችንን ለማሳደግ እና  ራሳችንን ለመሆን፣ የህልውናችንን ዓላማ ማወቅ ይኖርብናል።
​ማንም ሰው በህይወት ዘመኑ መጣርና  መልፋት ያለበት ለዚህ ትርጉም ነው። ይህ ትርጉም በገንዘብ አይገኝም፣ በዝናም ኣይታወቅም ፤ ይህ ትርጉም የሚገኘው  በውስጣችን በሚፈጠር ስምምነት ነው። ማንነታችን ከህልውናችን ጋር ሲስማማ፣ የውስጣችን ሰላም ይረጋጋል። ይህ የውስጥ ሰላም ደግሞ ለውጫዊው ዓለም ትርጉም ይሰጠዋል።
​እና የዛሬ ፅሑፌን በዶስቶቮስኪ ኣባባል ልቋጨው..

But how could you live and have no story to tell‽
👌8
አልረሳውሽም...አለመኖርሽን ነው የለመድኩት።
💔13🔥1
ጥልቅ ሀሳቦች (deep thoughts )🎴

Even if I don’t delete all the posts, from now on the channel will not be active like before. I will only share very few posts. Thank you, my dears

The writings I express through deep thoughts are, in general, my personal feelings, history, and reality. I deeply respect you. Your support for my posts of sadness and anxiety has made me realize that you too are in that same feeling ❤‍🩹
7💔3
“በዚህ ግዜ ደብዳቤዎቻችን ሳይቀር ጠበቃ ያስፈልጋቸዋል፤ እኛ በየዋህነት እንጽፍላቸዋለን ሌሎች በተሳሳተ መንገድ ያነቡታል!።”

                    ―ጋሳን ካንፋኒ
11
“እስኪ ንገሩኝ ሰው ሳይጮህና ሳይሰበር ስንት ስቃይ ይታገሳል?። ይህን ሁሉ ብቸኝነት፣ ይህን ሁሉ ፍርሃት በልቡ ተሸክሞ ምንም እንዳልተፈጠረ መቆም ይችላልንህ?።

ውስጣችን እየተቃጠለ ፈገግ ማለታችን አያስገርምም? ቀስ በቀስ እየሞትን እንዴት ነው ህይወትን የምንኖረው?።

ዙሪያችሁን ተመልከቱ.. ሁሉም ሰው ጭንብል ለብሷል፤ ሁሉም ሰው መናገር የማይደፍረው ታሪክ ማንም ሊሰማው የማይችለው ቁስል በውስጡ ተሸክሟል።

ወዳጆቼ  ሆይ የምንኖረው ሳይሆን እስከመጨረሻው ድረስ የሚገድለንን ጨዋታ በደማቁ እንጫወታለን። ይህ የሕይወት ትወናችን ሲያልቅና መጋረጃው ሲዘጋ ምንም አይነት ጭብጨባ የለም፤ ማንም አያስታውሰንም!።”

  
     ፦The Idiots 📖―Dostoyevsky
10


መልካም
አሸንዳ
ሻደይ/ሶለል
አሸንድዬ


ሩሑስ ባዓል ይግበረልክን
!❤️
10
❤️
🔥84
‹‹የምትፈልገውን ካላገኝህ ትሰቃያለህ፤ የማትፈልገውን ካገኘህ ትሠቃያለህ፤  በትክክል የምትፈልገውን ነገር ስታገኝም ትሰቃያለህ ምክንያቱም ለዘላለም ልትይዘው አትችልም። አእምሮህ ችግርህ ነው  ከለውጥ ነፃ መሆን ይፈልጋል። ከሕመም የጸዳ ከሕይወትና ከሞት ግዴታዎችም ነፃ መሆን። ነገር ግን ለውጥ ህግ ነው እና ምንም አይነት ማስመሰል እውነታውን አይቀይረውም!።››

                    ―ሶቅራጠስ
💯4
ከዚህ በፊት ብዙ የብቸኝነትንና የሀዘን መንገድ ተጉዣለሁ። የነገሮች ትርጉም በውስጤ ታፍኖ ነበር በዚህ መታፈን ውስጥ ህይወት መጀመሪያና መጨረሻ እንደሌላት ተረዳሁ።
ህይወት የተራመድንበትና ያለፍንበት መንገድ ውጤት ነው። በህይወት ውስጥ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። ሁሉም የህይወት አካል ሲሆን ህይወት ደግሞ የመንገደኛ ስብስብ ናት። በየመንገዱ ከማንነት፣ ልብ፣ ህሊና እና ህልም ጋር እገናኛለሁ።

አሁን እውነቱ ቀላል እንደሆነ አውቄያለሁ በህይወት የመኖር ትርጉም ደስታን ማግኘት እና እያንዳንዱን የሕይወት ቅጽበት መኖር ነው። ነገር ግን ብቸኝነት ና ሀዘን የህይወት ክፍል ይሆናሉ። ከነሱ ጋር እንዴት እንደምንኖር ግን እኛ ነን የምንወስነው። ደስተኛ ለመሆን የምንፈልገው ነገርም አሁን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ መረዳት አለብን ካልሆነ ግን ፍላጋው ማለቂያ የለሽ ይሆናል።
👌4