Dire-Dawa University
16K subscribers
7.59K photos
42 videos
97 files
663 links
An Official Channel of Dire-Dawa University
Download Telegram
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ሃገራዊ የትግበራ እቅድን አፀደቀ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ሃገራዊ የትግበራ እቅድ / “Digital Skill Country Action Plan for Higher Education and TVET 2030” የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ግብ ትኩረት ያደረገባቸውን ኢኮኖሚ ደጋፊ ዘርፎችና በብሔራዊ ደረጃ የተያዙ የስራ እድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማሳደግ እና አካታች ብልጽግና የማረጋገጥ ግቦችን እዉን ለማድረግ የሚያስችሉ በመካከለኛና በከፍተኛ የዲጂታል ክህሎት የሰለጠኑ ምሩቃንን በማውጣት እንዲደግፉ ያስችላል፡፡

እቅዱ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ ትምህርት የስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ባለዳርሻ አካላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ከተካሄደበት በኃላ ወደስራ ገብቷል፡፡ በመድረኩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እቅዱ ለሁሉም ሴክተሮችና ለአራተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት (4th industrial revolutions) የሚያስፈልጉ በዲጂታል ክህሎት ብቃታቸው የተረጋገጠ ምሩቃንና ዜጎችን ለማፍራት እንዲቻልና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት የትምህርት፣ ምርምርና አስተዳደር ስራዎችን በኢንፎሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ እንዲቻል ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም የዲጂታል ክህሎት ሃገራዊ እቅዱ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ፣ ከሀገሪቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ፣ ከአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ የዲጂታል ስትራቴጂ እና ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲጸድቅ፣ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከእቅዱ በመነሳት የራሳቸውን ዘርፍ ማስፈጸሚያ እቅድ እንዲያዘጋጁ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የራሱን ድርሻ በመውሰድ እቅድ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ሃገራዊ የትግበራ እቅድ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ላይ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት የሚተገበር መሆኑን ገልጸው በኢትዮጵያ ያለዉን ዝቅተኛ የዲጂታል ክህሎት ለማሻሻል እንደሚያግዝም አብራርተዋል፡፡ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተማሪዎችንና መምህራንን ለዚህ ክህሎት ለማዘጋጀት አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡

እቅዱ በሃገራቸን ትኩረት ተደርጎ እየተሰራባቸው ለሚገኙት አካታች ብልጽግናን የሚያረጋገጡ ግቦችን ለማሳካት የሚያስፈልጉ የሰዉ ሃይል ለማፍራትና የዲጂታል ዕውቀትን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን አምስት የዲጂታል አስቻይ መሪ ግቦችን አካትቷል፡፡ እነዚህም፡-
1. በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ለመፍጠር የሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ ስታንዳርዶችና ማዕቀፎች በማውጣትና በመተግበር ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖሩ ማድረግ፣
2. በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ፕሮግራሞች ላይ በየጊዜዉ አስፈላጊ የሆኑ ለዉጦችን በማድረግ፣ ከዘመኑ ጋር ሊሄድ በሚችል መልኩ አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የተጠናከራ ስራ መስራት፣
3. በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚደረጉ የመማር ማስተማር፣ የምርመርና የአስተዳደር ስራዎች በአይ.ሲ.ቲ እንዲታገዙ በማድረግ የትምህርትና የምርመር ጥራትን መደገፍና የአሰራር ስርዓትን ማዘመን፣
4. የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ከፍተኛ ፍጥነት ያለዉ ብሮድባንድ እንዲያገኙና ከኢተርኔት ጋር በኔትዎርክ እንዲተሳሰሩ በማድረግ የተማከለ የክላዉድ አገልግሎት በኢተርኔት በማልማት የትምህርት፣ ምርምርና አስተዳደር ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ ማደረግ፣
5. በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የዲጂታል ክህሎታቸዉን ሊያዳብር የሚችል ቀጣይነት ያለዉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠትና የሚሰሩ ስራዎችና የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ ማድረግን የያዘ ነዉ፡፡
https://www.facebook.com/1958396367800151/posts/2532051430434639/
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎች የመልሶ ቅበላ ፕሮግራም በዛሬው እለትም ቀጥሏል።
ውድ የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በድጋሜ እንኳን በደህና መጣችሁ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስልጠና መርሐ ግብር