Dire-Dawa University
10.9K subscribers
5.75K photos
14 videos
86 files
542 links
An Official Channel of Dire-Dawa University
Download Telegram
ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትን ችግርን በዘላቂነት መቅረፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የፓናል ውይይቱን ኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን በፓናል ውይይቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማኅበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ  አቶ አብዱረህማን ሙሳ ሲሆኑ በንግግራቸውም  እንደ ሀገር ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህጻናት ቁጥር አሁን ላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመው በተለይ ድሬዳዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ መሆኗ በፍልሰት ወደ ከተማዋ በመግባት ውሎና አደራቸውን በጎዳና ላይ የሚያደርጉ ህፃናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣና ህጻናቱ የሚገጥማቸው ችግርም ውስብስብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይሄንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አብዱረህማን በተለይ ምሁራን በችግሩ ዙሪያ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር የሐረር የህፃናት መንድር ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አንዱአለም ጌታቸው ኤስ.ኦ.ኤስ  ከተመሠረተ  የ75 ዓመት ዕድሜን  ያስቆጠረ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደሆነና በሀገራችን ኢትዮጵያም ድርጅቱ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በቅርቡ ማክበሩን አስታውሰው ድርጅቱ ለአምስት አስርት ዓመታት በዘለቀው አገልግሎቱ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ አንዱአለም ገለጻ በአሁኑ ጊዜ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር ሀረር ፕሮግራም በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በሐረር ፣ በድሬዳዋ፣ በምስራቅና በምዕራብ ኦሮሚያ እንዲሁም በከፊል የሶማሌ ክልል ቁጥራቸው ከ57 ሺህ የሚበልጡ  የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉ ፕሮጀክቶች ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝና ድርጅቱ  ካለፈው 2 ዓመት ወዲህ ከፎረም ኦን ሰስቴነብል ችልድረን ኢንፓወርመንት ከተባለ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ውሏቸውንና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናትን ህይወት የሚቀይሩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ እንደሚገኝና በዚህም አጠቃላይ ቁጥራቸው ከ2700 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት እየተገበረ መሆኑን ገልፃዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት መምህር አለምስገድ ደጀኔ 'የህጻናት መብቶች ተጋላጭነትታቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች' በሚል ርዕስ እንዲሁም በኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር የድሬደዋ የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሚካኤል ስንታየሁ 'ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ህፃናት ተጋላጭነት ያለበት ደረጃ ፣ የተጋላጭነት ዋነኛ ምክንያት እና ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች' በሚል ርዕስ ጽሁፎችን አቅርበው  ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየች ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ተቋሙ እየሰራ ላለው ስራ አመስግነው ችግሩ ሥር የሰደደና በየግዜው ተለዋዋጭ በመሆኑ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብር ቅንጅትና ቁርጠኝነት የሚፈልግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም እንደ ባለድርሻ አካል ሃላፊነቱን እንደሚወጣና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተው  የፓናል ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw
ለስድስት ተከታታይ ቀናት ወደኢንኩቤሽን ማዕከል ለሚገቡ ሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው የስታርት አፕ ስልጠና ተጠናቀቀ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጲያ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ከዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ ወጣቶች ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው “Design Your Venture” የተሰኘ የስታርት አፕ ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስልጠናው ከኢትዮጲያ ልማት ኢንቲትዩት በመጡ በዘርፉ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን የተሻለ የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸው 40 ተማሪዎች ተመርጠው ተሳትፈውበታል፡፡

ስልጠናውን ያጠናቀቁት ወጣቶች በቀጣይ የፈጠራ ስራቸውን ወደገበያ ለማውጣት እንዲረዳቸው ወደኢንኩቤሽን ማዕከል የሚገቡ ሲሆን ሃሳባቸውን ወደተግባር አውርደው ውጤታማ እንዲሆኑ ተከታታይ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ይጠበቃል፡፡

ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች Like እና Subscribe በማድረግ ይከታተላሉ፡-
ድረ ገጽ: http://www.ddu.edu.et/
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/DDUniv/
ቴሌግራም: https://t.me/DDUniv/
ትዊተር፡ https://twitter.com/DDUniv/
ዩትዩብ:https://m.youtube.com/channel/UCwGK2TmnY4mbykkPE5c8bbw
Vacancy Announcement
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጲያ ናሽናል ሳይንስ አካዳሚና ጂአይዜድ ሲሰጡ የነበሩት ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ በሶስቱ ተቋማት ትብብር የተሰጠው ስልጠና ዩኒቨርሲቲው አፕላይድ ሳይንስ መሆኑን በማሰመልከት ለጀማሪ አመራሩና ለመምህራኑ አቅም መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ስልጠናው አምስት ቀናት የፈጀ ሲሆን እየተደረገ ባለው ሽግግር የመማር-ማስተማርና የአመራር ሂደቱ ምን መምሰል እንዳለበት ትኩረት ሰጥቶ የዳሰሰ እንዲሁም ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ ኢንደስትሪዎች ጋር በሁሉም መልኩ መተሳሰርን ያስገነዘበ ስልጠና ነበር፡፡
Dire Dawa University held a partnership expansion discussion with Heilbronn University of Applied Sciences, Germany. The discussion focused on the strength of Heilbronn University as an Applied Science University and how the collaboration could take place and complement the transformation of Dire Dawa University to an ASU. Prof. Tomas Benz stated that the two institutions could engage on staff and student exchange programs and joint projects mainly focusing on Engineering programs. It is to be noted that the two universities have currently active joint project and this helps to expand the current collaboration to a broader scope. In a zoom call discussion involving the top leadership, Strategic Partnership and Internationalization Director and project coordinator, agreement was established on specifics of the collaboration and Memorandum of Understanding will be signed shortly during the Heilbronn University’s delegate visit to Dire Dawa University.