DCDE - Insights
116 subscribers
271 photos
4 videos
11 links
Defence Construction Design Enterprise - DCDE
| መከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት - መ.ኮ.ዲ.ድ |
dcde.gov.et
facebook.com/dcde.gov.et
x.com/dcde_et
linkedin.com/company/dcde-et/
pinterest.com/dcde_et
Download Telegram
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አማካሪነት ተገንብቶና ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ በቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
----------------

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማውን ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የ6 ወራት አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አማካሪነት ተገንብቶና ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ ጣቢያ ነው፡፡

የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ ከቋሚ ኮሚቴው ጋር በነበራቸው አጭር ውይይት ጣቢያው ቀድሞ በግለሰብ የጫማ ፋብሪካ መጋዘን ውስጥ ባልተመቸ ሁኔታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ አስታውሰው አሁን የተገነባው አዲስ ጣቢያ በየወሩ ለኪራይ ይወጣ የነበረውን ሀብት ከማዳኑም ባሻገር እጅግ ማራኪ ከባቢ ዕውን በማድረጉ በሰራዊቱ ዘንድ የላቀ የስራ መነሳሳት እና የአገልጋይነት ስሜትን ጨምሯል ብለዋል፡፡
👍1
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አማካሪነት እየተገነቡ ያሉ የአቅመ- ደካሞች መኖሪያ ቤቶች መጎብኘቱ ተገለፀ።
****************

ፍትህ ሚኒስቴር ሰላም ሚኒስቴር እና መከላከያ ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የ2017 ዓ.ም የክረምት የበጎ አድራጎት ተግባራት ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በኮልባ ሎሚ ወረዳ የአቅመ-ደካማ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡት መሰረት የቤቶቹን ግንባታ ሂደት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ሲሆን አማካሪው ደግሞ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ነው። ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የወጣበት ይህ የቤቶች ግንባታ 88% ያህል የግንባታ ስራው መጠናቀቁን የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድዛይን ድርጅት ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ሌተናል ኮሎኔል ደበበ እሸቱ ተናግረዋል፡፡

በግንባታው 16 ባለሁለት መኝታ መኖሪያ ቤቶች መንገድ እና አጥር የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ ከነመፀዳጃ እና ማብሰያ ቤቶች በመሰራት ላይ ሲሆኑ ለአንድ አበዋራ 67 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የቤት ግንባታ መከናወኑንም ተናግረዋል። ከተጀመረ 3ወራትን ያስቆጠረው ግንባታው ከበዛ ከአንድ ወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ርክክብ እንደሚደረግ ሌተናል ኮሎኔል ደበበ እሸቱ ገልፀዋል።

በዚህ ግንባታ እና በሠራዊቱ ህዝባዊነት የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ አመራሮች ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ክብርት ሚኒስትሯም በግንባታው ሂደት እና ጥራት ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የሰራዊቱ ቁልፍ ተግባር የሀገርን ዳርድንበር ማስጠበቅ ቢሆንም ጀግናው ሰራዊታችን ሀገርን በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ከሚከፍለው ውድ መስዕዋትነት ባሻገር ይህ በጎ ተግባርም ሰራዊቱ ህዝባዊነቱን እያረጋገጠ ከሚገኝባቸው በጎ ተግባራት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የቀሩት ትንንሽ የፊንሺንግ ስራዎች ተጠናቀው ቤቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለነዋሪዎች እንዲተላለፍም መልዕክት አስተላልፈዋል።
2👍1
Forwarded from mndaye feysa
1
በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የአድዋ ካፕ ስፖርታዊ ውድድር እየተካሄደ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም

በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዘጋጅነት የአድዋ ካፕ ስፖርታዊ ውድድር በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ዘጠኝ የሰራዊታችን ዋና ዋና ክፍሎች በአምስት የስፖርት አይነቶች እንደሚወዳደሩ ተጠቁሟል። ውድድሩ የተዘጋጀው 130ኛ የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ነው።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጅ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን ሁሉ የነፃነት ፣ የአንድነት እና የብርታት ምልክት ነው ሲሉ ገልፀውታል።

ዛሬም ያንን መንፈስ በስፖርት መድረክ ላይ በመድገም እና በመዘመን የአድዋ ካፕ የስፖርት ፌስቲቫልን በደስታ ነው የምከፍተው ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን  እያከናወናቸው ካሉ በርካታ ስራዎች ጎን ለጎን የመከላከያ ዋና ዋና ክፍሎችን የሚያስተሳስረውን የአድዋን ድል ለመዘከር እንዲህ አይነት  ስፖርታዊ ውድድር በማዘጋጀቱ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስም ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ  ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በበኩላቸው  መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በሚንስትሮች ምክር ቤት ከተቀመጠለት ዓላመዎች መካከል በዋናነት የሠራዊቱን አባላት ኑሮ ለማሻሻል የሚረዱ ተግባርትን በማከናውን የሠራዊቱን ሞራል መጠበቅና ማጎልበት እንደሆነ ግልፀዋል።

በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን እና በመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ መካከል በተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ፋውንዴሽን ጤና ዋና መምሪያን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በዚሁ የአድዋ ካፕ ስፖርታዊ ውድድር መክፈቻ ስነ - ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ ፣የመከላከያ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄነራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ፣የጦር ኃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ዶክተር ኃይሉ እንዳሻው ፣ ጄነራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶ ግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official