DBU info Center
5.59K subscribers
323 photos
62 videos
23 files
282 links
ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋመ
Download Telegram
ሦስት ባህላዊ መድኃኒቶችን ለገበያ ለማቅርብ እየሰራሁ ነው - ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአስር ባህላዊ የመድኃኒት ዕፅዋቶች ላይ ምርምር በማድረግ ሦስቱን ለገበያ ለማቅርብ እየሰራሁ ነው አለ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በአስር የመድኃኒት ዕፅዋቶች ላይ ምርምር ሲያደርግ መቆየቱን በዩኒቨርሲቲው የአንኮበር መድኃኒታዊ ዕፅዋትና ሀገር በቀል ዕውቀት ማበልፀጊያ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ አያሌው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ34 ሄክታር መሬት ላይ የመድኃኒታዊ ዕፅዋቶች ምርምር እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

እስካሁን በአስር መድኃኒቶች ላይ ምርምር መከናወኑን አንስተው÷ ሦስቱ የመፈወስ አቅም ሙከራ ሂደትን አልፈው ወደ ገበያ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ባህላዊ ህክምናን በማዘመን ከመጀመሪያ ደረጃ የጤና ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር ዩኒቨርሲቲው ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።

በሰላም አሰፋ


@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
15👍8
#to_remedial

ፈተናውን ያለፋችሁ ከዚ በኋላ All DBU Freshman Student ሆነናችኋል ማለት ነው ።👊


እንኳን ደስ አላችሁ 👌

@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
🔥224👍4🙏2😁1
Info for health science student

ለ Coc exam ምዝገባ ተጀምሯል !!
coc ባለፈው ያልመጣላችሁ ድጋሜ በመመዝገብ በዚህ ወር መውሰድ ትችላላችሁ።


መረጃውን ለጤና ተማሪዎች share ያደርጉላቸው ❗️


@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
11
በደብረ ብርሐን ዩኒቨርስቲ መሐል ሜዳ ካምፓስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የሪሜዲያል ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 94.13% ማለፋቸውን ከካምፓሱ ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል::

" እንኳን ደስ አላችሁ!!"


@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
13
የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ የሥራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሮ ቁምነገር አለሙ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ሃምሌ 15/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በተወለደች በ40 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ።

ወ/ሮ ቁምነገር አለሙ ባለትዳር ስትሆን የአንድ ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች እናት ነበረች።

ወ/ሮ ቁምነገር ከዚህ በፊት በበረኸት ወረዳ በመጥተህ ብላ ከተማ በሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት የሰራች ሲሆን አርቆ አሳቢ፣ሰው አክባሪ ፣ፍልቅልቅ፣ በስራዋ ትጉህ ታታሪና በሩህሩህነቷም ትታወቃለች በተለይ ካላት ላይ በማካፈል የህፃናቶችንና የሴቶችን እንባ አብሳለች በስራ ባልደረቦቿ፣ በጓደኞቿ ምስጉን ተወዳች ነበረች።
የተወለደቺው ከማይጠገቡት ከደጋጎቹ መንደር ደቡብ ወሎ ተንታ ፣ የኖረቺው ከሚተዛዘኑበትና በፍቅር ከሚኖርባት የበረሃዋ ገነት መተሐራ አባድር ሥራ የጀመረችውና በስስት የቆየችው ከለጋሶቹ መንደር ተካፍለህ ከምትኖርባት ምድር በረኸት መጥተህ ብላ እራሷን በትምህርት አብቅታ እስከለተ ህልፈቷ የነበረችው ከደጋማዋ የሸዋ ብርሃን ደብረብርሃን ታዲያ እንዴት ሳቂታና ለሰው ልጆች መልካም ስብእና አይኖራት ፈጣሪም ለራሱ ይመርጣልና ወሰዳት😭😭😭😭
ሞት ፊትና ኋላ የማይቀር እዳ ነውና ቁሜ ከዚህ አለም ድካም አርፋለች።
ዛሬ ሃምሌ 16/2017 ዓመተ ምህረት ከቀኑ 6:00 ሰዓት በአንሳስ ማርያም ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት የቀብር ስነ-ስርአቷ ይፈፀማል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለልጆቿ፣ ለጓደኞቿ እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቿ እና ለወዳጆቿ መጽናናትን እንመኛለን ፡፡

እግዚአብሔር ነፍሷን በአጸደ ገነት ያኑራት፤



@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
😭327🕊5😢3😁1
#ministry_of_health


የብቃት ምዘና ፈተና የሚወስዱ የጤና ባለሙያዎች የኦንላይን ምዝገባ ከሐምሌ 15-24/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ይመዝገቡ👇
http://hple.moh.gov.et/hple



@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
🔥32
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Gyokeresh 🥰

Goal machine 👌

Look the 2nd & 4th goal what an amazing it was 😎

Gunners 🤝


@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
🔥15😁75👎3🍌2👍1
#NGAT

NGAT ወይም ለማስተር እና phd መማር ለምትፈልጉ ሁሉ
ለNGAT ምዝገባ ፋይዳ መታወቂያ ግደታ አስፈላጊ እንደሆነ Website ላይ አረጋግጠናል።

ስለዚህ ፋይዳ መታወቂያ ያላወጣችሁ አሁኑኑ አውጡ!

ምዝገባው በይፋ ሲጀመር የምናሳውቃችሁ ይሆናል ተከታተሉን።


@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
13🥰3👎1
ለማጭበርበር እየተጋለጠ የመጣው የመውጫ ፈተና‼️
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2017 የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ጋር በተያያዘ የሰባት (7) ባለሥልጣናት ሚስቶች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ባለቤት ጨምሮ፣ ባልተለመደ ሁኔታ 100% ውጤት ማምጣታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል።

ይህ ፈተና ከትምህርት ሚኒስቴር አሰራርና ከዩኒቨርሲቲው እውቅና ውጪ በወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ውስጥ በልዩ ሁኔታ መሰጠቱ ተጋልጧል። የኮሌጁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ በላይ ባልጉዳ በማመቻቸት፣ ተፈታኞች ስልክና ChatGPT (AI) በመጠቀም በልዩ ክፍል ውስጥ ፈተናውን እንደወሰዱ ተጠቁሟል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ባደረጉት ማጣራት፣ ሁለት (2) የICT ባለሙያዎች (አቶ አስፋው አሻንጎ እና አቶ አዱኛ ጌታቸው) ከሥራ ሲታገዱ፣ የአቶ በላይ ባልጉዳ እና የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ተሻለ ወ/አማኑኤል ጉዳይ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
በመውጫ ፈተና ሙሉ ተማሪዎችን ማሳለፍ ለዩኒቨርስቲዎች እንደ አንድ የስኬት መለኪያ ተደርጎ በትምህርት ሚኒስቴር መቀመጡ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ለማሳለፍ ሲሉ የማጭበርበር ሥራ ውስጥ እንዲገቡ እየገፋፋ መሆኑን ምሁራን እየነቀፉ ይገኛሉ።
አዩዘሀበሻ

@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
@dbuinfocenter12
👍1813😁6🥱3