DBU HUB||🇪🇹
406 subscribers
358 photos
2 videos
418 files
163 links
በዚህ ገፅ ስለ ግቢው እና ስለ ከተማዋ አሳማኝ መረጃዎች
👉ማስታወቂያዎች እንደወጡ
👉ለሁሉም ዲፓርትመንቶች ምጁል እና handout
👉አስፈላጊ ይሆናሉ ያልናቸውን ጥያቄዎች እና ሌሎችም ሌሎችም
👉 እንዲሁም እናንተን ያዝናናሉ ያልናቸውን መረጃዎች እናቀርባለን
☆ማንኛውም ጥቆማ ካላቹ 'ሀሳብ አለኝ' ይበሉን🙏
@samuliee
Download Telegram
ፈሶትን አያዙ: የተከማቸ ፈስ በአፍ ሊወጣ ይችላል

​አንድ ሰው የሆድ አየርን (ፈስን) ከልክ በላይ ይዞ ለመቆየት ሲሞክር አየሩ በጨጓራና አንጀት ውስጥ ታፍኖ አይቀርም።

በሰውነት ውስጣዊ መዋቅር ምክንያት አየሩ ወደ ደም ዝውውር ስርአት ውስጥ እንደገና በመመጠቅ በመጨረሻም በአፍ በሚወጣው ትንፋሽ በኩል ሊወጣ እንደሚችል የህክምና ጥናቶች ያሳያሉ።

​ይህ ሂደት የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ የታቀበው ጋዝ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ወደ አንጀት ግድግዳ የደም ስሮች በመግባት ነው።

ደም ወደ ሳንባ በሚሰራጭበት ወቅት እነዚህ ጋዞች ከደም ወጥተው ወደ ሳንባ አየር ከረጢቶች ስለሚሸጋገሩ፣ ግለሰቡ በሚተነፍስበት ጊዜ አየሩ በአፍ በኩል ይወጣል።

​ምንም እንኳን ይህ አጋጣሚ ለብዙዎች እንግዳና የሚያስቅ ቢመስልም፣ በተፈጥሮ የሚፈጠርን የሰውነት ጋዝ አፍኖ መያዝ የሆድ እብጠት፣ ህመም እና የአንጀት ምቾት ማጣት ስለሚያስከትል ተፈጥሯዊ ሂደቶችን አለመግታት ይመረጣል።

https://t.me/dbuhub
✅
🤣4❤2
ቀልድ መስለው ነገር ግን ወንጀል የሆኑ ድርጊቶች!
****
1. የሰውን ፎቶ/ቪዲዮ መለጠፍ
ድርጊቱ፦ መንገድ ላይ ያዩትን ጠብ ወይም አስቂኝ ነገር ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ቀርጾ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ።

ውጤቱ፦ የግል ነፃነትን መጣስ ተብሎ ያስከስሳል።

2. የሀሰት ወሬ ማሰራጨት
ድርጊቱ፦ "እውነት ይመስላል" ብለው መረጃን ሳያረጋግጡ "Share" ማድረግ።

ውጤቱ፦ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መጣስ እና የሰላም መታወክ ተጠያቂነት።

3. በኮሜንት መሳደብ
ድርጊቱ፦ በፖስት ስር ሰዎችን በብሄር፣ በሃይማኖት ወይም በግል ማንነታቸው መስደብ።

ውጤቱ፦ የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጥፋት ወንጀል።

4. ያለፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ
ድርጊቱ፦ "ለታመመ ሰው እርዳታ" በሚል የባንክ አካውንት እየለጠፉ በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ መለመን።

ውጤቱ፦ ያለፈቃድ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የማጭበርበር ጥርጣሬ።

5. የሰው ዲዛይን መስረቅ
ድርጊቱ፦ የሌላ ሰውን ሎጎ ወይም የፈጠራ ስራ "የእኔ ነው" ብሎ መጠቀም።

ውጤቱ፦ የቅጂ መብት (Copyright) ጥሰት ክስ።

6. የግል መልዕክትን ማጋራት (Screenshot)
ድርጊቱ፦ በ "Inbox" የተላከልዎትን ሚስጥራዊ መልዕክት ያለ ሰውየው ፈቃድ ለሰው እንዲታይ ፖስት ማድረግ።

ውጤቱ፦ የግል ሚስጥርን ማባከን (Privacy violation)።

ማሳሰቢያ፦ በኢንተርኔት የምንለጥፈው ነገር ሁሉ "ዲጂታል አሻራ" ስላለው በሕግ ፊት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።

https://t.me/dbuhub
✅
♡  ⌲        ✉️ 
ˡⁱᵏᵉ     ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
በዓሉን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የምናከብር ቢያንስ በዓሉን ለማክበር ለማይችሉ አቅም ለሌላቸው ማዕድ ብናጋራ👆

https://t.me/dbuhub
✅
🤣6👍2👏2
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)

2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)

https://t.me/dbuhub
✅
❤4
4_5857216900655751823.xlsx
187.4 KB
#DBU male students dormitory placement
https://t.me/dbuhub
✅
4_5857216900655751821 (1).xlsx
174.1 KB
#DBU FEMALE STUDENTS DORMITORY PLACEMENT
https://t.me/dbuhub
✅
የዩኒቨርሲቲ ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ምደባ ውጤትን ይፋ አድርጓል።

📌 የምደባው ዋና መስፈርቶች
• የተማሪው አጠቃላይ ውጤትና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
• የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም
• የክልል፣ ዞን፣ ወረዳና ትምህርት ቤት ስርጭት
• የፆታ ሚዛን

🌍 የክልል ስርጭት

➡️ 70% ተማሪዎች ከተወለዱበት/ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች

➡️ 30% ተማሪዎች በራሳቸው ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ታሳቢ ተደርጓል።

⭐️ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች

ከ600 ውስጥ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለውጤታቸው ልዩ ታሳቢነት ተደርጎላቸው፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ባስቀመጡት ዩኒቨርሲቲ እንዲመደቡ ተደርጓል።

♿️ ልዩ ታሳቢነት
የዓይነ ስውራን እና የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች ተገቢውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ልዩ ታሳቢ ተደርጓል።
🔎 የምደባ ውጤት ለማየት
👉 የምደባ ውጤት: https://student.ethernet.edu.et/view-placement
📝 ቅሬታ ለማቅረብ
የምደባ ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን በኦንላይን ሥርዓቱ ብቻ ማቅረብ ትችላላችሁ።
⏰ የቅሬታ ጊዜ፦ 5 ተከታታይ ቀናት ብቻ
👉 ቅሬታ ማቅረቢያ: https://student.ethernet.edu.et/complaints
⚠️ ማሳሰቢያ
በቅሬታ ሂደት ሐሰተኛ መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ የተከለከለ ነው። የቀረበው መረጃ ይረጋገጣል፤ ሐሰተኛ መረጃ ያቀረበ ተማሪ ምደባው ሊሰረዝ ይችላል።

🎉 ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

የትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/dbuhub
❤7
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በጠየቁት መሠረት፣ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ፣ የትምህርት ሒደታችሁ እንዳይስተጓጎል እና ደኅንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል በጊዜያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ" ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

"ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን" ብሏል ሚኒስቴሩ ባጋራው አጭር መልዕክት፡፡

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል የሚፈልጉ #ነባር እና #አዲስ ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤
ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@dbuhub
❤2
#Remedial #ምደባ

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።

የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences

https://t.me/dbuhub
❤3
​📌 ለFreshman ተማሪዎች በሙሉ!
​ለእናንተ ይረዳ ዘንድ ካለፉት ዓመታት የወጡ በርካታ የ Mid Exam እና Final Exam ጥያቄዎችን ከነመልሶቻቸው አዘጋጅተንላችኋል።
​በውስጡ ምን ምን ይዟል?
​✅ General Physics and Chemistry &Biology
​✅ Mathematics for Natural/Social Science
​✅ Psychology
​✅ Communicative English
​✅ Critical Thinking
​✅ እና ሌሎችም ሞጁሎች...
​📚 እነዚህን የፈተና ጥያቄዎች ደጋግማችሁ በመሥራት ውጤታችሁን አሻሽሉ!
​👇 ፈተናዎቹን ለማግኘት ቻናላችንን ተቀላቅለው ይጠብቁን፦
https://t.me/+bJVumECkHWhiMzk0
https://t.me/dbuhub
✅
​
#Freshman #University_News #MidExam #FinalExam #Ethiopia #Education #Modules #Dbu
♡   ⌲        ✉️ 
ˡⁱᵏᵉ     ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
❤5
ወጣትነት ማለት...."

ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም!

ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም!

ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!

ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም!

ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!


ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም!

ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም!

ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...!

ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ።

ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ።

ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው ።

ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ።


ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ።

ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ።

ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።

✍️አዘርግ

♡   ⌲        ✉️ 
ˡⁱᵏᵉ     ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
https://t.me/dbuhub
✅
👍5❤2🥰2😁2🔥1👏1🎉1💯1🫡1
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ላይ በመግባትና የፋይዳ ቁጥራችሁን በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
በተመሳሳይ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/view-placement ላይ በመግባት መመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል መርሐግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ
https://student.ethernet.edu.et/view-placement በመግባት መመልከት እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
 

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በ https://student.ethernet.edu.et/complaints አማካኝነት ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
 
https://t.me/+bJVumECkHWhiMzk0
ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።
https://t.me/+bJVumECkHWhiMzk0
❤2
#Vacancy

Debre Birhan University
❤2
እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

✨ መልካም የደመራ በዓል!

@dbuhub
❤9