Daniyal books
497 subscribers
527 photos
3 videos
2 files
103 links
ለሆድ ምግብ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጭንቅላት ፊደል ወሳኝ ነው።
Download Telegram
📣📣የዓዲስ መጽሐፍ ጥቆማ📣📣
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

🔔 Homo deus(ሆሞዲዩስ 🔔

መጽሐፍትን ወደ አማርኛ መተርጎም ቀላል አይደለም ።ቴክኒካል ቃላቶች እና የተወሳሰቡ ጽንሰ-ሐሳቦች ይኖሩታል ። እንግዲህ ተርጓሚው ይሄንን ተልዕኮ ለራሱ ሰጥቶ ነው መጽሐፉን ወደ አማርኛ የተረጎመው። እኔም የዋናውን እና የትርጉም መጻሕፍቱን ተራ በተራ አንብቤያለሁ።

ለዘመናት በሽታ፣ ረሃብ፣ ጦርነት የሰው ልጅ ትልቅ ራስምታቶች ነበሩ። በየአመቱ ሚሊየኖች በወረርሽኝ፣ በግጭትና በእርዛት ይረግፋሉ። ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት ግን የሰው ልጅ ቀንደኛ ጠላቶቹን በከፊል አሸንፏል ። በሽታዎች መድሃኒት እየተገኘላቸው፤ ምርት ተትረፍርፎ ረሃብ ታሪክ እየሆነ፤ ጦርነቶች እየቀሩ መጥተዋል። በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የሚሞቱት ሰዎች በተፈጥሯዊ አደጋ የሚሞቱትን ሺህ እጥፍ አስከንድተዋል። እንግዲህ እነዚህ እጅ ከሰጡ ወዲህ ቀጣይ የሰው ልጅ አጀንዳ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ምን ይሆናል?!

መጽሐፉ መልሱ ሞትን ማሸነፍ ነው ይለናል። ሳይንስ ሞትን እንደ ማንኛውም "በሽታ" ነው የሚቆጥረው። ስለዚህ በሽታው መድሃኒት ሊገኝለት፣ ሞትም ሊቀር ይችላል። ከሩቅ የተቀዳ፣ የማይመስል፣ የማይሆን ሃሳብ ሊመስላችሁ ይችላል። ደራሲው በጄ አይልም። "የሰው ልጅ ቀጣይ እጣ ፈንታ ከ'Homo sapiens' ወደ 'Homo deus' ወይንም ከሰውነት ወደ አምላክነት መሸጋገር ነው ይኼንንም በ300 ገፅ አብራራላችኋለሁ ተከተሉኝ" ይለናል። በመጀመሪያው መጽሐፍ ወደ ኋላ እንደመለሰን በዚህኛው ደግሞ ወደፊት ያስፈነጥረናል። መጪው ግዜ ብሩህ ነው።

ተርጓሚው ዳግም ጥላሁን መጽሐፉን በጥንቃቄ ወደ አማርኛ መልሶታል። ቁምነገሩን ሳይለቅ ለዛ ባለው ቋንቋ እንካችሁ ይለናል። የትርጉም መጽሐፍት ወዳጅ ባልሆንም ይህ መጽሐፍ አመለካከቴን እንደገና እንድፈትሽ ጋብዞኛል።

( በቴዎድሮስ ሸዋንግዛው )

📚#Homo deus(ሆሞዲዩስ

ዳግም ጥላሁን

መጽሐፉ በመደብራችን በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ዳኒያል መጻሕፍት ።
+251919154815
+251991183031
አድራሻ፦ሜክሲኮ መንገዶች ባለስልጣን ፊት ለፊት

@danubok
" እኛ ሰዎች ከተወለድንበት ቀን ይልቅ ሞታችን የሚታወስ ፣ የመጣንበት ሳይኾን የሄድንበት ቀን የሚሞገስ ፣ ከሕይወታችን ይልቅ ሞታችን ዋጋ ያለው ፣ ለምን ኖረ ሳይኾን  እንዴት ሞተ? የምንባል ፍጡሮች ነን ። ይህን ደግሞ ለማሸነፍ ቆም ብለን ማሰብና ወደ ፈጣሪ መጠጋት አለብን ። የሕይወታችን አላማ እዚያ እናገኛለን ። ልክ የአገራችን ሰው ሲተርት <  ሞት አይቀርም እቱ ምንም ቢታክቱ > እንደሚለውም  ሞትን እያሰብን መልካም ሥራ እንድንሠራ ነው ። "
 ሜሎሪና ገፅ 177
" መንገደኛ የተሰኘውን መጽሐፍ አንብቤ ተደንቄአለሁ፡፡ መጽሐፉ የጥልቅ ጥናት ውጤት ከመሆኑ ባሻገር በተዋበ ግልፅ ቋንቋ የቀረበ እጅግ አስፈላጊ ስራ ነው፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስለሚሰደዱ ሰዎች የደቡብ አፍሪካ ዜጋ ያልሆነ ሰው ምርምርና ጥናት አድርጎ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡ መጽሐፉ የስደተኞቹን ቅድመ-ስደት ሕይወት ይዳስሳል፤ ከደቡብ አፍሪካ ደርሰው የሚጋፈጧቸውን የኑሮ ተግዳሮቶችም ወለል አድርጎ ያሳያል፡፡ ከዚያም አልፎ የደቡባዊ አፍሪካ አገሮችን የፖለቲካና ማሕበራዊ ጭብጦችን ይነካካል፡፡ ወደፊት የስደት ጉዳይን በተመለከተ ሊደረግ የሚገባውን የጥናት አቅጣጫም ይጠቁማል፡፡ "

ዶክተር ጌታቸው ተድላ፤ የገጠር ልማት ባለሙያና ደራሲ
" ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች ”የለውጥ ኩርባ” አለችው። አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ አሊያም ድርጊቱ የሚቀየርባት ። ወደ ዐዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት። ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ ውድቀትም ሊሆን ይችላል። ያች የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዐረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንድት ደቂቃ መታቀፍ ወይም.... "

- ከ'ጠበኛ እውነቶች ' መጽሐፍ ገፅ 116

ደራሲ :- ሜሪ ፈለቀ
The 10 X Rule

በሽያጭ ላይ
ለሀብታሙ አለባቸው ወዳጆች :-

የሀብታሙ አለባቸው አራቱም መጻሕፍት በመደብራችን ይገኛሉ ::

በልዩ ቅናሽ ::

Daniyal books
Forwarded from Jafer Books 📚
ዓለም ላይ እጅግ ዝናን እና ተወዳጅነትን ካተረፉ የራስ - አገዝ ጸሐፍት እንዲሁም የሕይወት መርህ መምህሮች አንዱ ሮቢን ሻርማ መጽሐፍ የሆነው " The Everyday Hero Manifesto " መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል ::

ሽያጭ ላይ ነን !!

@jafbok
Forwarded from Jafer Books 📚
የዓለማየሁ ዋሴ " ሚተራሊዮን " የተሰኘው አዲስ መጽሐፉ ለንባብ በቃ ::

ዓለማየሁ ዋሴ

እመጓ
ዝጎራ
መርበብት
ሰበዝ

በተሰኙት መጻሕፍቱ ይታወቃል ::

ሽያጭ ላይ ነን !!

@jafbok
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ንባብ_ለሕይወት_2017

ዝግጁ ናችሁ ?

ከሐምሌ 24 - ሐምሌ 27 - በኤግዚብሽን ማዕከል ::