እለታዊ መረጃ Daily News
35 subscribers
46 photos
1 video
12 files
3 links
ሃቀኛና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ማድረስ። @dailynewset
Download Telegram
-5958521452909148830_120.jpg
52.1 KB
የሳምሪ ቡድን‼️
ሱዳን፤ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መካከል የትኛውም ታጠቂ ሃይል እንዳይንቀሳቀስ መወሰኗን ተከትሎ ሱዳን የሚገኘው የህወሓት አሸባሪ ቅርንጫፍ የሆነው የሳምሪ ቡድን እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። በዚህም ህወሃትን ጭንቅ ውስጥ ከቶታል ተብሏል።
-5960882671309667170_120.jpg
39.9 KB
በጋምቤላ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነሳ!

ሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ መነሳቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

በጋምቤላ ከተማ የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት 30 ድረስ ከሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አንስቶ መገደቡ እና ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

Via FBC
-5961045244411754489_121.jpg
114.2 KB
በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

Via Ethio FM
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን በዚህ ሳምንት ያሳወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)«ማናቸውም ንግግር በሰላም ጥረቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታን ማካተት አለበት» ብሏል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ «የድርድሩን ሂደት በሙሉ ለአፍሪቃ ኅብረት መስጠት ለኛ በጣም ሃላፊነት የጎደለው ነው የሚሆነው» ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ሁለቱን ወገኖች በተናጠል ሲያነጋግሩ የነበሩት የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርበት አላቸው የሚለው ህወሓት ድርድሩ በኬንያታ አስተባባሪነት እንዲካሄድ እንደሚፈልግ ከዚህ ቀደምም አስታውቆ ነበር።

የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ግን ማናቸውም ድርድሮች በአፍሪቃ ኅብረት ብቻ ነው ሊመሩ የሚችሉት ብሏል። ከህወሓት ጋር ለሚደረገው ድርድር የመንግሥት ተደራዳሪ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩን ባለፈው ሳምንት ተናግሯል።

@dailynewset
-5962885607833319160_121.jpg
100.5 KB
መረጃ‼️

ባልደራስ የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለህግ እንዲቀርቡ ጠየቀ!!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለህግ እንዲቀርቡ በዛሬው ዕለት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠይቋል።

ፓርቲው በመግለጫው ከንቲባዋ ከፍተኛ ሙስና ውስጥ እንደተዘፈቁ ሰሞኑን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለባለ እድለኞች ለመስጠት በወጣው የተጭበረበረ ዕጣ ወለል ብሎ ታይቷል ያለ ሲሆን በዚህ ሂደት፣ አዳነች አበቤ በከንቲባነታቸው ካለባቸው ሀላፊነት ባሻገር፣ በድርጊቱ መሪ ተዋናይ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች ተገኝቶባቸዋል ሲል ገልጿል፡፡

እንዲሁም የኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳይይሰቀል እና እንዳይዘመርም ፓርቲው አሳስቧል።

@dailynewset
-5962918670491563862_121.jpg
85.8 KB
#ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሐምሌ 21/2014ዓ.ም ተቀጠረ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ባለፈው ቀጠሮ የመልስ መልስ አለኝ ብሎ ባያመለክትም ጋዜጠኛ ተመስገን ባልቀረበበት ተቀብሎ ለዛሬ በችሎት አድርሶናል።

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሐምሌ 13/2014 ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

የዛሬው ቀጠሮ ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ በልዩ ሁኔታ ዋስትና ተከልክሎ በእስር ላይ ሊይቆይ ይገባል በማለት ላቀረበው ይግባኝ ወሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 13/2014 ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ሳይደርስለት ቀርቷል። ሆኖም አቃቤ ህግ በመሀል የመልስ መልስ ማስገባቱን ችሎቱ ተናግሯል። በስተመጨረሻም የፌደራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት በዋስትናው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በድጋሚ ቀጠሮ ለሐምሌ 21/2014 ጠዋት በ3:30 ሰጥቷል::

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከታሠረ 55 (ሃምስ አምስት) ቀኑን ይዟል::

@dailynewset
@dailynewset
ማስታወሻ‼️

18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ረቡዕ በሦስት ውድድሮች የሚቀጥል ይሆናል።

👉ለሊት 8:25 የሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ :-
• ለተሰንበት ግደይ
• ዳዊት ስዩም
• ጉዳፍ ፀጋዬ የሚሳተፉ ይሆናል።

👉ለሊት 9፡20 በወንዶች 800ሜትር ማጣሪያ ፦
• ኤርሚያስ ግርማ
• ቶሎሳ ቦደና የሚሳተፉ ይሆናል።

👉ለሊት 11:45 የሴቶች 3000ሜትር መሠናክል ፍጻሜ :-
• መቅደስ አበበ
• ወርቅዉሃ ጌታቸው የሚሳተፉ ይሆናል።

መልካም እድል !!!
❗️"ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን"
ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

ዋና አዛዡ አክለውም እኛ የአየር ኃይል አባላቶች ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

በቀጣይም የሰራዊቱንና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለመደጎም በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተናግረዋል።
ዋልድባ‼️
አሸባሪዉ የህወ^^ት ቡድን አለም በቃኝ ብለዉ በዋልድባ ገዳም የሚገኙ የበቁ አባቶች ላይ ስቃንና እንግልት መፈፀሙንና ገዳሙን መዝረፉን ቀጥሏል ።
በትላንትናው እለት ወደ ገዳሙ በመግባት በርካታ ንዋያተ ቅድሳን ከመዝረፍ በተጨማሪ ስዕል አድኖዎችን ማቃጠላቸዉን  አባቶችን ባገኙት ነገር መደብደባቸዉን ክብረ ነክ ድርጊቶችን መፈፀማቸዉን  ከስፍራው ባገኘነው መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል ።
ይህ ገዳም በጣም ሰፊ ሲሆን የአራቱ ገዳማት መገኛ  ከሆኑ ከሰንሰለታማ ተራሮች  በጀርባ በኩል ባሉ ተራሮች የሚመጣዉ የህወሃት ቡድን በተደጋጋሚ እያጠቃዉ ይገኛል ።
❗️ቆቦ ስልክ ይሰራል
ወልዲያ ውዝግብ ውስጥ ናት የመከላከያ ሰራዊቱ በከተማዋ ውስጥ ይገኛል
ከቆቦ የሚመጣው ህዝብ ወልዲያ ይገኛል እንዲሁም የወልዲያ ነዋሪዎች ደግሞ መውጣት ጀምረዋል
❗️❗️ሕዝቡ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅና ለጥምር ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው።

የአካባቢው ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የወልድያ ከተማ አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም።

ሾልኮ ለማለፍ እና በወሬ ለመፍታት የተደረገው የጠላት ስልት እስከ አሁን ድረስ አልሰመረም።

ማሳሰቢያ፦

መረጃ ከመስጠት የዘገየነው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር እስከምናጣራ መሆኑን ሕዝባችን እንዲረዳን ስንል እናሳስባለን።

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

@
ከአፋር ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ‼️

አሸባሪው ህወሓት የጀመረውን ህዝባዊ እልቂት አለም አቀፉ ማሀበረሰብ ሊያወግዝ ይገባል!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል እና በአማራ ክልል በኩል በከፈተው በከባድ መሳሪያ ህዝብን በማሸበር የጀመረውን አረመኔያዊ ህዝባዊ እልቂት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዝ ይገባል። ቡድኑ ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ ለሶስት ዙር በአፋር ክልል በኩል በከፈተው ጦርነት ንፁሀን ሴቶችን፣ ህፃናት፣ አዛውንቶችን ያለምንም ርህራሄ በጅምላ ጨፍጭፏል፣ ህዝባዊተቋማትን፣ ሀይማኖች ተቋማትን አውድሟል፣ በርካታቁጥር ያላቸው ንፁሀን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል ለስቃይ፣ ለርሃብ፣ ለእንግልት እና ሞት ዳርጓል፡፡

በንፁሀን ዜጎች የጭካኔ አይነቶችን እያፈራረቀ የፈፀመው አሸባሪው ህወሀት ለዘመናት ተጋምዶ የኖረው የአፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን አብሮነት የሚያሰናክለው ባለመሆኑ፣ አሸባሪ ቡድኑን እንደ ቡድን ነጥሎ በማየት፣ የተከበረው የትግራይ ህዝብን ለመታደግ መድረስ የሚገባቸው የሰብአዊ እርዳታ በአፋር በኩል እንዲያልፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለህዝብ እርዳታ እንዲደርስ የአፋር ህዝብና መንግስት ከፌዴራል ተቋማት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች እና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋር ሲሰሩ ቆይተዋል።

በቀጠናው አሸባሪው ህወሀት የከፈተው አስከፊ ጦርነት እንዲቆም መንግስት የሰላም አማራጭ ቢያቀርብም ሰላም የማይቸው አሸባሪው ህወሀት በመንግስት በኩል የቀረቡ የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው በአፋር ክልል በኩል በፈንቲረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ለአራተኛ ር በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል። በተመሳሳይም በአማራ ክልል በኩል ጦርነት ከፍቶ ህዝባዊ እልቂት በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡

አሸባሪው ህወሀት ከአሁን በፊት ጦርነት በከፈተባቸው ግምባሮች እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በከፈተው ጦርነት ንፁሀን ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የሰው ማዕበልን በጠቀም ጦርነት ከፍቷል። በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ ዞን በያሎ ወረዳ በኩል ከባድ መሳሪያ ወደ ንፁሀን አርብቶ አደሮች በመተኮስ ህፃናትና ሴቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል፣ ከባድ የሆነ ጉዳትም ድርሷል፡፡
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቡድኑ በአፋር ክልል እና በአማራ በኩል በከፈተው ጦርነት ከዚህ የከፋ ህዝባዊ እልቂትን ለማስከተል እየሰራ በመሆኑ ይህን ፈፅሞ ከሰብአዊነት የራቀ አረኔዊ በጭካኔ የተሞላ ድርጊት በማውገዝ ከሰብአዊነት ጎን ሊቆም ይገባል!
    
-5791913327830613614_121.jpg
254.1 KB
መንግስት ማሕበራዊ ሚድያውን ተጠቅመው መከላከያውን በወሬ ለመፍታት ሸሸ ፈረጠጠ እያሉ በ መከላከያ ሰራዊቱ በቤተሰቦቹ እንዲሁም በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሞራል ቁማር የሚጫወቱ አክቲቪስት ነን የሚል የአገር እና የሕዝብን ጠላት በቸልታ ሊያልፍ አይገባም ቴክኖሎጂው በተራቀቀበት ዘመን አገር ለማፍረስ ተከፍሎትም ሆነ ባንዳ የባንዳ ልጅ ሁሉ ከያለበት ሰብስቦ ወደ ስልጠና ማዕከላር በማስገባት ለሌሎች ትምህርት የሚቀስሙበትን ነገር ማድረግ አለበት::

በወያኔ ሰአት አይደለም የጦሩን እንቅስቃሴ ሊያንቋሽሽ ይቅርና ኢሳት እና ሌሎች የተቃዋሚ ቲቪዎችን ለማየት ምን ያክል በፍርሐት ተሸብቦ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ምንም እንኳን የሚዲያ ነፃነት የሚበረታታ ቢሆንም የአገርን ሉአላዊነት ለማፍረስ በ አክቲቪስትነት ስምም ሆነ በጋዜጠኝነት እንዲሁም በማህበራዊ ሚድያ የሚለቀቁ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ እና ሰራዊቱ እና አገር ወዳድ ኢትዩጳያዊያን መስዋዕትነት እየከፈሉ መሐል አገር ላይ ከቤተሰቡ ጋር የሞቀ ፍራሹ ላይ ሆኖ ወታደራዊ ትንታኔ የሚሰጥንም ሆነ እንደ ዘመድኩን በቀለ አይነቱን ስደተኛ ካምፕ ውስጥ ሆኖ የፈረንጅ ቀለብ የሚሰፈርለት ተከፋይ የሕወሓት ቅጥረኛ ላይላዩን አገር ወዳድ በመምሰል አንድጊዜ በሐይማኖት ሌላጊዜ ደግሞ በብሔር ስም እየነገደ መንግስትና ሕዝብ መሐል መተማመን እንዳይኖር የመንግስት አመራሮችን የጌታና የሎሌ አይነት ስም እየሰጠ ኢትዮ 360 ዎችንም ይጨምራል ክፍፍል ለመፍጠር የሚሰሩትን አካላት ምንግዜም የኢትዮጵያና መከላክያ ሰራዊት ጠላቶች እደሆኑ ልናውቅ ይገባል

ኢትዩጵያ በአገር ወዳድ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብርና ሞገሰ ለመከላክያ ሰራዊት እና በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የክልልና የፌደራል ጸጥታ ሃይሎች
መረጃ‼️

ትላንት ለተኩስ አቁም ለሠላም ዝግጁ ነኝ ያለው ህወሓት ዛሬ መስከረም 2/2015 ዓ.ም ከማለዳው ጀምሮ ከሱዳን አቅጣጫ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት በመተማ ወረዳ ሽንፋ ቲሃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጦርነት ከፍቷል።
የፌዴራል መንግሥቱ እና የሕወሓት ተወካዮች በጅቡቲ ተገናኝተው መወያየታቸው ተዘግቧል!!

የፌዴራል መንግሥቱ እና የሕወሓት ተወካዮች በጅቡቲ መወያየታቸውን የዘገበው የፈረንሳዩ መንግሥታዊ ራድዮ፤ ራድዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል (አር ኤፍ አይ) ነው። አር ኤፍ አይ በድረ ገጹ ባስነበበው ዘገባ ተወካዮቹ የተገናኙት ሐሙስ ጳጉሜን 3፣ 2014 ነው።

እንደ ዘገባው ከሆነ ውይይቱን ያመቻቹት ከባለፈው ሳምንት አንስቶ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልኡኩ ማይክ ሐመር ናቸው።በውይይቱ ላይ ስለ ተኩስ አቁም፣ የትግራይ እርዳታ፣ የወልቃይት ጉዳይ እና በኢትዮጵያ ግዛት ስለሚገኘው የኤርትራ ጦር ተነስቷል ተብሏል።
ሰበር ዜና

ህወሓት አዲስ ጦርነት በሱዳን ድንበር ከፈተ
ህወሓት ሌሊቱን የከፈተው ጦርነት በመተማ አቅጣቻ ጀበል ስኳር አካባቢ ሲሆን ከባድ መሳሪያዎችን ከርቀት እየተኮሰች ነው።

ህወሓት ምሽት ላይ እደራደራለሁ ሰላም እፍልጋለሁ ቢልም በሰዓታት ልዩነት አዲስ ጦርነት ጀምሯል።

ህወሓት የተለመደ ማጭበርበሪያውን ተጠቅሞ ለማዘናጋት ሰላምና ድርድር ቢልም ወደ ተለመደ የውጊያና የሽብር ተግባሩ የገባው በሰዓታት ልዩነት ነው።

መንግስት የህወሓት ባህሪይ በመረዳት የሽብር ቡዱኑ የጀመረውን ጦርነት በፍጥነት ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።
ህወሓት ለመደረመደር መግለጫ ቢያወጣም ስራው ግን ሽብር ነውና ሽብር መፈፀሙን ቀጥሎ በአዲስ ግንባር ጦርነት በከፈተበት ሁኔታ መንግሰት የህወሓትን ሴራ ማጋለጥና የከፈተውን ውጊያ እስከ መጨረሻው ማሳረግ አለበት።

ህወሓት አዲስ በከፈተው ውጊያም ሆነ ባቀረበው የድርድር ሀሳብ እስካሁን መንግስት ያለው ነገር የለም።
መረጃ ‼️

በመተማ እንዲሁም በሁመራ በአከር በኩል ከባድ ዉጊያ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 7 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.