Cheshire Ethiopia - Head Office
136 subscribers
137 photos
2 videos
1 file
9 links
Cheshire Ethiopia (CE) is a pioneer non-governmental disability and development organization registered as local civil society organization committed to the welfare and development of Persons with Disabilities mainly children in Ethiopia since 1962.
Download Telegram
Forwarded from Fasil Gebreselasse
Forwarded from Fasil Gebreselasse
Forwarded from Fasil Gebreselasse
If you work at a screen, try what some people call the 20-20-20 rule. Every 20 minutes, look at something that's 20 feet away for 20 seconds. Keep blinking so your eyes don't get dry. Keep your hands clean when you put your contact lenses in.
Forwarded from Cheshire Ethiopia-Hawassa (ቸሻየር ኢትዮጵያ ሀዋሳ)Discussion (👏👏Dereje Getachew 👏👏)
የጤና ሚኒስትር  ዶክተር ሊያ ታደሰ አካታች የጤና አገልግሎቶች ዙርያ ከሚመለከታቸው የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረጉ።
____

ዉይይቱም ማሻሻያ በሚሹ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ በተለይም የተለያየ አይነት የአካልም ሆነ የአእምሮ ጉዳት ወይም
ዉሱንነት ላለባቸዉ አካታች የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶች፤ የአገልግሎቶች ተደራሽነት እና ተስማሚነት፣ የመልሶ ማቋቋሚያ አገልግሎቶችን እና የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን ጥራት፣ በዚህ ዙሪያ የሚፈለጉ የባለሞያዎች ስልጠና እንዲሁም ከመመርያዎች እና ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አኳያ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ እንደተናገሩት ጤና ሚኒስቴር ከሀገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ አጋሮች ጋር በመተባበር ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት፣ አቅምን ለመገንባት፣ ጥናትና ምርምርን እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ በመስጠት የጤና ተቋማት ግንዛቤን ከመፍጠር ጀምሮ የተሟላ፣ አካታች አገልግሎት የተለያየ አካል ጉዳትና ውሱንነት ላለባቸዉ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግና የተሟላ የተሀድሶ አገልግሎትን ጨምሮ አጋርነትን በማጎልበት  በትኩረት እየሰራ እንደሆነ እና በውይይቱ የተነሱትንም ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ዶ/ር ሊያ

በውይይቱ የቸሻየር ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ፋሲል አየለ ጨምሮ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ጨምሮ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት እና ፌዴሬሽን አስተባባሪዎች እና አባላት ተገኝተዋል።
A short documentary film presentation on sustainable livelihoods intervention project /SLIP/ to empower women with disability /women with disability families at Ahmara and Oromia regions Ethiopia .October 2023
አካል ጉዳተኛ የሆኑ ወይም አካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ያሏቸው ሴቶች በዘላቂነት የራሳቸው ገቢ እንዲኖራቸው በሚተገበረው ፕሮጀክት የተዘጋጀ አጭር ደኩመንታሪ ፊልም ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=teRSMd9Hdy8
Forwarded from Cheshire Ethiopia-Hawassa (ቸሻየር ኢትዮጵያ ሀዋሳ)Discussion (👏👏Dereje Getachew 👏👏)
የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ዋዜማ በቸሻየር ኢትዮጵያ ተሃድሶ ማዕከል የተሃድሶ አገልግሎት እያገኙ ያሉ አካል ጉዳተኛ ህጻናት (CwDs) መናገሻ ተሃድሶ ማዕከል End Polio now 2023 በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን ህጻናትን ፖሊዮን ቀን ማክበር ችለዋል።  ይህ ዝግጅት በታላቁ ሩጫ አዘጋጅነት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የፖሊዮ በሽታን ለማጥፋት የግንዛቤ ማስጨበጫ መረሃ-ግብር እንዲሆን ታቅድ የተከበረ ነው። አካል ጉዳተኞች በሩጫው ከመሳተፍ ባለፈ ውዝዋዜ በማሳየት ችሎታቸውን አሳይተዋል። በፎቶ የምትመለከቱት ስፍራ የቸሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ተሃድሶ ማዕከል በዓሉን ባማረ ሁኔታ ማክበር ተችሏል።

On November 18, 2023, the eve of the Ethiopian Great Run, children with disabilities (CwDs) who are receiving rehabilitation services at Cheshire Ethiopia Menagesha rehabilitation center joined the End Polio now 2023 children races. This event was organized by the Great Run in collaboration with the Ministry of Health and its partners to raise awareness and support for polio eradication. The CwDs not only participated in the race but also showcased their talents by performing dances.
Theme for IDPD 2023
አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ክብረ በዓል መሪ ቃል ለ2016:

"United in action to rescue and achieve the SDGs for, with and by persons with disabilities"
ለአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ትርጉም ያለዉ ትብብር!
ቸሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ተሃድሶ ማዕከል አካል ጉዳኛ ልጅ ላላቸው እናቶች የተሃድሶ ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
_______
የስልጠናው ለ3 ቀናት የተሰጠ ስሆን አላማውም እናቶች ለልጆቻቸው ጥራት ያለው እንክብካቤ እንዲሰጡ አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት ማስጨበጥ ነው። መርሃ ግብሩ እንደተጠናቀቀ ተሳታፊዎች በተሃድሶ ማዕከሉ የሚሰጡትን አገልግሎቶችን ጎብኝተዋል።

Cheshire Ethiopia Menagesha Rehabilitation Center conducted Rehabilitation skill training for the mothers of children who have polio and other developmental disabilities.
_______
The training was given for three days and aimed at empowering mothers with the necessary knowledge and skills to provide quality care for their children. Upon completion of the training, the participants visited the facilities of the rehabilitation center and shared their feedback.
Forwarded from Life
የ 2023/2016 ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ደረሰ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን (International Day of Person with Disabilities) በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ዲሴምበር 3 የሚከበር ቀን ነው።

ቀኑ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ደህንነት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ ለመፍጠር፤ የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ በሁሉም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ህይወት ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።

እኢአ Dec 3/2023 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ህዳር 23/2016 ዓም የሚከበረውን አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ለማክበር ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
የ ዘንድሮው/2016 አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን መሪ ቃል/Theme for IDPD 2023፦
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
"United in action to rescue and achieve the SDGs for, with and by persons with disabilities"
🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑
'ለአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ትርጉም ያለዉ ትብብር!'

በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ታውቋል።
Forwarded from Cheshire Ethiopia-Hawassa (ቸሻየር ኢትዮጵያ ሀዋሳ)Discussion (👏👏Dereje Getachew 👏👏)
ድርጅታችን ቸሻየር ኢትዮጵያ-ሀዋሳ ተሃድሶ ማዕከል በሲዳማ ክልል በተዘጋጀው GO-CSO ፎረም ላይ ተሳትፎ አድርገናል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች/Go-CSO forum 3ኛ ዙር የጋራ ምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ አካሄደ።

"መተባበራችን ለዕድገታችን" በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት 3ኛ ዙር የጋራ ምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደተናገሩት የሲቪል ማኅበረሰብ መንግሥትን በማገዝ ለህብረተሰቡ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮች በመሥራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ገልፀው በዘንድሮው ብቻ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ በማውጣት እየደገፉ ይገኛሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ መተባበር፣ መተጋገዝ፣ መረዳዳት ካለ የማይፈታ ጥያቄ እንደሌለ የገለጹ ሲሆን እነዚህ ድርጅቶች በክልላች የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ ለሚያደርጉት ርብርብ አመስግነው የጀመሩትን ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ እንዲያስቀጥሉ እና ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ሁሉ የክልሉ መንግስት ከጎናቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የፎረሙ አካል ከነበረ ኩነት አንዱ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን ስራዎች የሚያቀርቡበት exhibition የነበረ ሲሆን ድርጅታችን ስራዎቹን በፎቶ በቀረበው መልኩ ለዕይታ አቅርቧል።

ድርጅታችን በሲዳማ ክልል እና አጎራባች አካባቢዎች ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ላይ በሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች ምክንያት በሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ እና በክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አራርሶ ገረመው የተፈረመ የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶልናል።