Cheshire Ethiopia - Head Office
155 subscribers
236 photos
2 videos
2 files
9 links
Cheshire Ethiopia (CE) is a pioneer non-governmental disability and development organization registered as local civil society organization committed to the welfare and development of Persons with Disabilities mainly children in Ethiopia since 1962.
Download Telegram
Forwarded from 
In collaboration with Ali Birra foundation and Haramaya University a team of volunteers delivered a hands-on training on occupational therapy. The focus was specifically on autism, equipping participants with practical tools and techniques. The training, held at Cheshire Ethiopia-Harar, was both lively and enlightening, fostering a deeper understanding of occupational therapy practices.
ሁሉም ነገር ተጠናቆ እነሆ በነገው ዕለት ነሐሴ 18/2016 ዓም ልናስመርቅ ቀጠሮ ይዘናል👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
በድርጅታችን ቸሻየር ኢትዮጵያ-ሀዋሳ ተሃድሶ ማዕከል የሚሰጠው የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት አሰጣጥ ከነበረበት ደረጃ ከፍፍፍፍፍፍ የሚያደርግ ተጨማሪ መሰረት ልማት/የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆ በነገው ዕለት የሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አጋር ተቋማት፣ የተቋሙ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው የድርጅታችን አጋር አካላት በተገኙበት በይፋ ልናስመርቅ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ፈልገው ከተለያዩ ከተሞች ወደ ቸሻየር ኢት/ያ-ሀዋሳ ተሃድሶ ማዕከል የሚመጡ አካል ጉዳተኞች ጊዚያዊ የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ መጠናቀቁን በደስታ እየገለፅን ለዚህ ስኬት በገንዘበ፣ በቁሳቁስ እና በሙያቹ ድጋፍ ላደረጋችሁልን የድርጅታችን አላማ ደጋፊዎች/ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ድጋፋችሁ ፍሬ አፍርቶ በአካል የምታዩበት ደረጃ ላይ መድረሱን ልንገልፅላቹ ወደድን👏👏👏👏👏

በተለይም የዚህ የመኝታ ክፍሎች ግንባታ ከፍተኛውን ወጪ የተሸፈነው አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ/ICRC ሲሆን የመኝታ ክፍሎቹ የውስጥ ቁሳቁሶችን በማሟላት ደግሞ የተለያየ የግል ድርጅቶች ከፍተኛው ርብርብ አድርገው ለፍፃሜ አብቅተውናል።
ከዚህ በኋላ ለአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ወደ ማዕከላችን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ አካል ጉዳተኞች ጊዜያዊ የመኝታ አገልግሎት ያለክፍያ የሚያገኙ ይሆናል!!!!!
እንኳን ደስ አለን/ደስ አላችሁ!!!!!
በቸሻየር ኢትዮጵያ-ሀዋሳ ተሃድሶ ማዕከል የሚሰጠው የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው የታመነበት እና አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ፈልገው ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ማዕከላችን ለሚመጡ አካል ጉዳተኞች ጊዜያዊ የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆና አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተውለት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በግንባታው ምረቃ ስነ-ስረዓት ላይ የተለያዩ የድርጅታችን የስራ ሃላፊዎች፣ የድርጅታችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የድርጅታችን ተጠቃሚዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
የምረቃ መርዓ-ግብሩን በይፋ ያበሰሩት የድርጅታችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ግርማ አባቢ (የሊያና/ያኔት ሄልዝ ኬር መስራችና ባለቤት) እንደተናገሩት የዚህ ጊዜያዊ የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ፈልገው ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ማዕከሉ ለሚመጡ አካል ጉዳተኞች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በተለይም በማዕከሉ የሚሰጠውን አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት የተሟላ፣ የተጠቃሚዎችን የኢኮነኖሚ ችግር የሚፈታ፣ ደህንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ የሚቆዩበት የመኝታ ክፍሎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የቸሻየር ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ፋሲል አየለ እንደተናገሩት የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እያሻቀበ የመጣ ሲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመተባበር ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ ሁለንተናዊ የተሃድሶ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀው በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቃው የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ ድጋፍ ላደገሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡