Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸውም በነፃ የስልክ ቁጥር 8588 በመደወል ጥቆማ እንዲያደርሱም ቢሮው ጠይቋል፡፡

በመሆኑም የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ፦ ደርባ 1 ሺህ 67 ብር ከ36 ሳንቲም፣ ዳንጎቴ 1 ሺህ 106 ብር ከ85 ሳንቲም፣ ሃበሻ ሲሚንቶ 1 ሺህ 305 ብር፣ ኢትዮ 1 ሺህ 56 ብር ከ80 ሳንቲም፣ ሙገር 1 ሺህ 16 ብር ከ52 ሳንቲም፣ ናሽናል ሲሚንቶ 1 ሺህ 169 ብር ከ98 ሳንቲም፣ ካፒታል 1 ሺህ 101 ብር ከ05 ሳንቲም መሆኑን ቢሮው አስታወቋል፡፡
Call for Project Managers and Resident Engineers Training (2 Round)
ማስታወቂያ

ቢሮው  ፍላጎትና አቅም ያላቸውን የ2005 ዓ.ም የ20/80 እና የ40/60 የቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎችን  በጋራ ህንጻ ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት እንዲሰሩ ለማድረግ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ቢሮው ባስነገረው ማስታወቂያ መሰረት 70 ከመቶውን የቆጠባችሁ የማህበሩ አባላት ወደ ማህበሩ አካውንት እንድታዛወሩ ገልፆ ነበር።

ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች 70 በመቶውን ወደ ማህበሩ አካውንት ያላዘወራችሁ ቆጣቢዎች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ቅዳሜ 15/11/15 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንድታዛውሩ እናሳስባለን።

ከቀነ ገደቡ ውጪ ወደ ማህበሩ አካውንት የሚያዛውር ቢሮው ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ያሳውቃል።


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የከተማ አስተዳደሩና ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነቡ ነው ተባለ

በዚህ ፕሮግራም ሥር እንዲሳተፉ 68 ሪል ስቴት አልሚዎችን የመረጠ ሲሆን፤ አልሚዎቹም በተቀመጠው 70/30 አጋርነት መሠረት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተጣምረው ግንባታውን ለማካሄድ ውል ገብተዋል።

ከእነዚህም አልሚዎች ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ኦቪድ ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ እንይ ኮንስትራክሽን፣ ጊፍት ሪል ስቴትና ሌሎችም ይገኙበታል ነው የተባለው።

የከተማ አስተዳደሩ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረብና መሠረተ ልማቶችን ማሟላት ኃላፊነት ሲኖርበት፤ አልሚዎቹ ደግሞ ያስገቡትን የመገንባት አቅም መሠረት ተደርጎ በሚቀርብላቸው መሬት ላይ ወጪውን በመሸፈን ቤቶቹን እንደሚገነቡ ተገልጿል።

Source:
https://www.ethiopianreporter.com/120823/
ለአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ አዲስ ተቋራጭ ጨረታ ሊወጣ ነው

ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመት እንደገና ለማስጀመር በጀት መያዙን ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። በቅርቡም ሥራ ተቋራጭ ለመምረጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ የሚወጣ መሆኑ ተመልክቷል።

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ በ48 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባውና 62ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ለማስቀጠል በ2016 ዓ.ም በጀት የተያዘለት በመሆኑ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ግንባታው ይጀመራል።

የብሔራዊ ስታዲየሙ ግንባታ በቻይናው ኩባንያ ይካሄድ እንደነበረ አስታውሰው፤ ግንባታው በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን ገልፀዋል።

በኋላም የግንባታ ተቋራጩ ለሥራው ያቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ከገበያ በላይ የተጋነነ በመሆኑ መንግሥት ከያዘው በጀት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም።

የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ግንባታውን የጎበኙ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች አስተያየትም ሥራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መከናወኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር በጀት ታህሳስ 2008 ዓ.ም እንደተጀመረ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በ5 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር በጀት መጋቢት 2012 ዓ.ም ተጀምሮ በዘጠኝ መቶ ቀናት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።

ዘገባው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው
👍1
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአንድ ሣምንት ታግዷል።
የተለያዩ ኩባንያዎች የአክሲዮን ሽያጭ በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት እያሉ ሚያስተዋውቁት ሀሰት ነው።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የአክሲዮን ሽያጭ መመዝገብ አለመጀመሩን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
Give everyone a way, built it that way.
ዋትሳፕ እንደ ቴሌግራም መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል የቻናል ስርዐት አስጀምሯል፣ በዋትሳፕ መረጃ ማግኘት ለሚቀላችሁ ይህን አዲስ ቻናል መቀላቀል ትችላላችሁ።


Follow the Construction Proxy channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaAwWvsGE56sqUJ5v02u