Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን በ4.2 ቢሊዮን ብር መንገድ ሊገነባ ነው

ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የሚያስተሳስረው 160 ኪ.ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ፡፡

የግንባታ ስራውን የሚያካሂደው ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኋ/የተ/የግ/ማ የተባለ አገር በቀል የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡

የመንገዱን ጥራት ቁጥጥር እና የማማከር ሥራዎችን የሚያከናውነው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ነው።

የግንባታዉ ወጪው የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።
መንገዱ በገጠር ከ8-10 ሜትር ߹ በቀበሌ 12 ሜትር፣ በወረዳ የእግረኛ መንገድን አካቶ ከ19-24 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ይገነባል።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ።

በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው በሙያቸው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እያገለገሉ የነበሩ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች በታጣቂዎች ተገደሉ።

#አሥራት_ሺካ እና #ሮቤል_ልደቱ የተባሉት ወጣት ኢንጂነሮች ትላንት ሰኔ 8/2013 ለሥራ ጉዳይ "አማሮ ልዩ ወረዳ" ሲጓዙ "ጀሎ" በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል።

ሁለቱም ወጣት ኢንጂነሮች ባላቸው እውቀት ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት።

የወጣቶቹን ግድያ የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቀናል ብሏል።

በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን ባወጣው የሀዘን መግለጫ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ባልስልጣኑ 'ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት' ብሎ ከመግለፅ በዘለለ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስለግድያው ፣ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ተያያዥ መረጃ እንዲሰጠን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

@tikvahethiopia
Several cement plants in #Ethiopia will undergo maintenance beginning next month, aggravating fears that shortages in supply will send retail prices through the roof.

Via - AddisFortune
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ።

• 10 ሰዎች ተገድለዋል።
• የሟቾች አስክሬን ዛሬ አርብ ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል።

ከቀናት በፊት በደቡብ 'አማሮ ልዩ ወረዳ' አካባቢ ታጣቂዎች የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ህይወት በግፍ ማጥፋታቸውን ከሰማን በኃላ ዛሬ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ሰምተናል።

ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ነው።

ጥቃት ተፈፅም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ያረጋገጡ ሲሆን ጥቃቱ በዞኑ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ "ሎያ ጎዳኔ" ቀበሌ ውስጥ ረቡዕ ሰኔ 09/2013 ዓ.ም አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ መፈፁም ገልፀዋል።

በታጣቂዎች የተገደሉት የፌደራል እና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ባለሙያ የሆኑ 9 ሰዎች እና የቀበሌው ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ናቸው ብለዋል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት መኪና ውስጥ ከነበሩ 11 የመንገድ ሥራ ባለሙያዎች በሕይወት የተረፉ መኖራቸውንም አክለዋል።

በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ጠቅሰው አስከሬናቸው ዛሬ አርብ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ዲሪርሳ ፥ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አስራ አንድ የመንገድ ግንባታ ባለሙያዎች መካከል ከግድያው ያመለጡት ሁለቱ "በአካላቸው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ ደህና ናቸው" ብለዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ጥቃቱን የፈጸመው "ኦነግ-ሸኔ" የተባለው ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-06-18

@tikvahethiopia
#EthiopiaCheck Scam Alert

አሁንም ራሳችንን ከአታላዮች እንጠብቅ--- ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን

ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ እና የንግድ ሥራ ት/ቤት በታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም በየሙያ መስኩ እና በየደረጃው ተመዝግበው መስፈርቱን ላሟሉ አመልካቾች ሰጥቶት በነበረው ፈተና ከማለፊያ ውጤት በታች ያገኙ ማለትም ከ 60% በታች ውጤት ያላቸውን ተወዳዳሪዎችን ስልክ እየደወሉ ገንዘብ ክፈሉና እናስቀጥራችኋለን በማለት የሚያታልሉ እና የኮርፖሬሽኑን መልካም ስም የሚያጎድፉ አጭበርባሪዎች እንዳሉ ወደ መ/ቤታችን በመምጣት ካመለከቱ ተወዳዳሪዎች መረዳት መቻሉን በመግለፅ የሚመለከታቸው አካላት ከመሰል አታላዮች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ኮርፖሬሽናችን ቀደም ሲል ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅትም ይህ የማታለል ድርጊት በሌለ መልኩ ቀጥሎ ስልክ እየደወለ ገንዘብ ከከፈላችሁኝ ከኮርፖሬሽኑ አንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላው እንድትዛወሩ አደርጋለሁ የሚል ግለሰብ ስለመኖሩ ይኸው የማታለል ሙከራ ደረሰብን ካሉ ግለሰቦች መረጃ ደርሶናል፡፡

በመረጃው መሠረት ይህን የማታለል ሙከራ እያደረገ ያለው ከዚህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ በሰጠው ማሳሰቢያ ላይ ረቡኒ ኢሳያስ በሚል ስምና የስልክ ቁጥር 0966459226 በባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000338403422 ገንዘብ አስገቡ እና ሥራ አስቀጥራችኋለው እያለ የማታለል ሙከራውን የቀጠለው ይኸው ግለሰብ ገንዘብ ክፈሉና ትዛወሩበታላችሁ በሚል የሚጠቅሰው ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ ሥራ ላይ የሌለ እና ቀደም ብሎ የተዘጋ ነው፡፡

በመሆኑም የሚመለከታችሁ አካላት ይህንኑ በመገንዘብ ከመሰል የመጭበርበር ጥቃት ራሳችሁን እንድትጠብቁ ኮርፖሬሽኑ በጥብቅ እያሳሰበ ጉዳዩን በሕግ አግባብ እየተከታተለው መሆኑን በድጋሚ ለማስታወስ ይወዳል፡፡
Reporter, Seni 13, 2013 EC
The_Addis_Ababa_City_Government_Construction_Professionals_Ethics.pdf
14.3 MB
The-Addis-Ababa-City-Government-Construction-Professionals-Ethics-Regulation-No-1022018.pdf
የአመልካቾች ዝርዝር.pdf
2.4 MB
All applicant for Addis Ababa city Roads Authorities
AACRA:
በጁኒየር ሲቪል መሀንዲስ ክፍት የስራ መደብ ላይ መስፈርቱን ያሟሉ ተወዳዳሪዎች በዕጣ ለመለየት በስማቸው የመጀመሪያ ፊደል የተለዩበት ዝርዝር

1 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ሀ ፊደል እና ለ ፊደል ቤቶች የሆነ 6/11/13 - ጠዋት
2 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል መ ፊደል ቤቶች የሆነ 6/11/13 - ከሰዓት
3 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ሰ/ሠ ፊደል እና ረ ፊደል ቤቶች የሆነ 7/11/13 - ጠዋት
4 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ሸ፣ቀ እና በ ፊደል ቤቶች የሆነ 7/11/13 - ከሰዓት
5 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ተ፣ ቸ እና ነ ፊደል ቤቶች የሆነ 8/11/13 - ጠዋት
6 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል አ ፊደል ቤቶች የሆነ 8/11/13 - ከሰዓት
7 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ከ፣ ወ፣ ዘ እና የ ፊደል ቤቶች የሆነ 9/11/13 - ጠዋት
8 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ደ፣ ጀ እና ገ ፊደል ቤቶች የሆነ 9/11/13 - ከሰዓት
9 የስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ጠ፣ ጨ፣ ፀ፣ ፈ እና ፐ ፊደል ቤቶች የሆነ 13/11/13 - ጠዋት

ማሳሰቢያ

1. አመልካቾች እጣ ለማውጣት በሚመጡበት ቀን ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
2. ዕጣ በምታወጡበት ቀን የስም ዝርራችሁ ያለበትን ተራ ቁጥር አይታችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
3. ዕጣማውጣት የምትችሉት በወጣው ፕሮግራም ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ከዛ ውጪ የሚመጣ አመልካች የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
#የአባይ_በረሃ መንገድ የመንሸራተት አደጋ አጋጥሞታል።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር የሚወስደው ዋናው መንገድ በአባይ በረሀ ውስጥ የመሸራተት አደጋ ስለደረሰበት ለተሽከርካሪዎች ዝግ ሆኗል።
#Update

የሲሚንቶ ግብይትን የሚወስነው እና በንግድና ኢንዱስትሪ ተግባራዊ ሲሆን የቆየው መመሪያ መሻሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዛራ አስታወቀ።

በዚህም ሲሚንቶ ከዛሬ ጀምሮ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ ተወስኗል።

ለዚህ ዋና ምክንያት ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራዎች ስለሚቀንስና ከሱ ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ስለሚቅንስ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪ የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንዳይኖር መንግስት ከውጪ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁና ፋብሪካዎች ምርታቸው እንዲጨምር በመደረጉ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አብራርቷል።

መረጃው የኢቢሲ ነው።

@tikvahethiopoa
ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ በሐራጅ ሊሸጥ ነው

ታዋቂው ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ በባንክ ሐራጅ ሊሸጥ መሆኑ ተሰማ።

በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የኮንስትራክሽን ድርጅቱን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ለመሸጥ የወሰነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሆነ ታውቋል።

በሐራጅ የሚሸጠው ህንፃ ለድርጅት አገልግሎት መዋል የሚችልና በ13,203 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው መሆኑም ታውቋል።

ባንኩ ይህንን ህንፃ ለመሸጥ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ 111.6 ሚሊዮን ብር መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

ሪፖርተር
The government hopes to see the construction industry create 3.3 million jobs in the next decade. But it is an industry besieged by a web of constraints such as cost escalation, forex shortage, lack of financing, and cash flow problems.

Via - AddisFortune
We can't just stop a construction project, we have to finish in time," he said, adding that he recently paid 900 Br for a quintal of cement. The high prices and shortage might lead to project delays, according to Addis, and this will mean even more costs incurred.
ሀገር_በቀል_ስራ_ተቋራጮች_የኮንስትራክሽን_ካፒታል_እቃዎች_በማንኛውም_ግዜ_ከቀረጥ_ነፃ_2013.pdf
2 MB
ሀገር በቀል ስራ ተቋራጮች የኮንስትራክሽን ካፒታል እቃዎች በማንኛውም ግዜ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የካቲት 2013 የተላለፈዉ ዝርዝር ስለመተካቱ