Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
Forwarded from Construction Resources
2013 3rd quarter direct cost.pdf
25.1 MB
የ 2013 በጀት ዓመት #የ3ኛ_ሩብ_ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች #ቀጥተኛ_ዋጋ
የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ መጋቢት 30/2013 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ በህንጻ መደርመስ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጁፒተር ሆቴል አካባቢ በደረሰ የህንጻ መደርመስ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

በጅምር ላይ የነበረው ህንጻ ዛሬ ረፋድ አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት መደርመሱን ነው የተነገረው፡፡

በጊዜው በስራ ላይ 112 ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 108ኙ ከአደጋው መዳናቸው ተገልጿል፡፡
እንደዚሁም አራት ግለሰቦች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለጣቢያችን ያስታወቀው፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የአደጋውን ምክንያት በማጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ማሳሰቢያ

ሀሙስ ሚያዚያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን የስራ ማስታወቂያ በተመለከተ የፈተና ቀኑን ወደፊት በባለስልጣኑ የፌስቡክ ገፅ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
👍1
" The bridge over the Kebenà River built by Germany and Italy near their respective legations "
No dude, you don't get to use this formula , u just have to use ERA manuals.
List of contractors from grade 1 - 6
ከ ደረጃ 1 - 6 ያሉ ኮንትራክተሮች

https://constructionproxy.com/catalog/contractors-in-ethiopia
Chinese companies dominated the list of Top Construction contractors in #Africa

1. Sinohydro Corporation
2. China Civil Engineering Construction Corporation (CCECC)
3. China Henan International Cooperation Group Company Limited
4. China Communications Construction Company(CCCC)
5. China Harbour Engineering Company (CHEC)
6. China Road and Bridge Corporation
7. SOGEA-SATOM
8. Mota-Engil China
9. Geo-Engineering Corporation (CGC)

(Centum real estate)
መንግስት በሲሚንቶ ገበያ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እየሰራ ባለበት ወቅት ነጋዴዎች ኩንታል ሲሚንቶ እስከ 800 ብር በመሸጥ ቀድሞ የተረበሸውን ገበያ ማናጋታቸውን ቀጥለዋል ፡፡

በክፍት ገበያ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ እየጨመረ የመጣው የሲሚንቶ ዋጋ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ላይ ተግዳሮቶችን አስነስቷል ፡፡ መንግስት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሻሻል እና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ዋነኛው የሆነውን የሲሚንቶ ዋጋ ለመቆጣጠር በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ፡፡ ነገር ግን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በምሽት ሰዓት ሲሚንቶ ጅምላ ሻጮች በአንድ ኩንታል እስከ 800 ብር ሲሚንቶ እየሸጡ መሆናቸውን ካፒታል ታዝባለች ፡፡

ህገወጥ ደላሎችን ለመቆጣጠር መንግስት ከ 233 ብር እስከ 300 ብር ባሉት ለተዘረዘሩት 12 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የፋብሪካ ማምረቻ ዋጋ አስቀምጧል ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአንድ ወር ጀምሮ በገበያው ውስጥ የሚስተዋለውን የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት በመሞከር በፋብሪካዎች ውስጥ የበላይ ተመልካቾችን በመመደብ ሥራቸውን በመቆጣጠር ላይ እና በየከተሞቹ በከንቲባዎች የሚምራ ግብረ ኃይል አደራጅቶ እየሠራ ነው የሚሉት የሚኒስቴሩ ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሳ አላምረው ሆኖም ችግሩ ጥልቅ በመሆኑንና የአቅርቦት ችግሩ እስካልተፈታ ድረስ በቁጥጥር ስር ለማዋል አስቸጋሪ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

https://www.capitalethiopia.com/featured/cement-price-spike-stiffens-market/
Eid Mubarak
PROJECT MANAGER
WALIIF CONSTRUCTION SHARE COMPANY CIVIL ENGINEERING CONTRACT May 16, 2021 - May 21, 2021
Description
Job Requirement
Education: BSc in Civil Engineering or Construction Technology & Management
Related Experience: 10 years and above
Place of Work: Project Sites (out of Addis Ababa)

How to Apply
Closing Date:5 (five) consecutive days from the first date of announcement
Interested applicants who fulfill the above requirements can submit their application with non- returnable copies of the CV’s.
Address: Arat Kilo, Infront of Berhanena Selam Printing Press at Dink Sira Building 8th Floor Tel. 0118124767 Email: wcsc1002@gmail.com
1
% of urban households in Africa who can afford the cheapest newly built house in 2020

According to the research based on income data, 3.52% Ethiopians can afford US $17, 226 for houses.

@Businessinfoeth
የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫ እና ምዝገባ አዲስ መመሪያ ወጣ
*************
የኮስተባ ሕዝብ ግንኑነትና ኮሙኒኬሽን
ሰኔ 7 ቀን 2013 ዓ.ም
*************
የኮንስትራክሽን ባለሙያ፣ አማካሪ፣ የስራ ተቋራጭ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ምዝገባ መመሪያ 648/2013 በአዲስ መልክ ፀድቆ መውጣቱ ተመለከተ፡፡

በዚሁ መሰረትም የቀድሞው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችና ስራ ተቋራጮች የምዝገባ መመሪያ ቁጥር 19/2005፤የኮንስትራክሽን ዲዛይን ባለሙያዎችና አማካሪዎች ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 22/2005 ፣ እንዲሁም የቀድሞውን መመሪያ ተከትሎ ወጥተው የነበሩ መስፈርቶችም አዲስ በፀደቀው የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013መሰረት የተሻሩ መሆናቸው ተመልክቷል::

ይህ የተመለከተው የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የህግ ዝግጅት ኮድና ስታንዳርድ ዳይሬክቶሬት ለተቋሙ የምዝገባና ሰርተፊኬሽን ስራ ክፍል ሀላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም በዘርፉ የሚመለከታቸውን የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎችና ባለሙያዎችን አዲስ በፀደቀው የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ሰሞኑን ባተዘጋጀ የስልጠና መርሃግብር ነው፡፡
በስልጠናው ላይ እንደተመለከተው አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 648/2013 ከረቂቅ ዝግጅቱ አንስቶ አስከ ፀደቀበት ድረስ የተከናወኑ ተግባራት፣ መነሻ መርሆዎቹና አስፈላጊነቱ ተብራርቷል፡፡

በዋናነትም ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተሳታፊዎችን በጥራት እና በብዛት ለማሳደግ ብሎም ውድድሩን ለማስፋት ዕድል የሚፈጥር መመሪያ ሆኖ መዘጋጀቱ ነው የተመለከተው፡፡

በተያያዘም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ሀገርንና ህዝብን ወደ ብልፅግና የሚያሸጋግር መደላድል እንዲሆን የሚስችለውን የአፈፃፀም ሚና ማሳደግ ፣ የምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥንና የመረጃ አያያዝን ምቹና ዘመናዊ ማድረግ፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ የተንሰራፋውን ብልሹ አሰራር ማስወገድ፣ ዘርፉ ዕውቀት መር እንዲሆን ማስቻል የመመሪያው አበይት መርሆዎች እንደሆኑም ተገብራርቷል፡፡

ኢንዱስትሪው በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ማለትም በጊዜ፣ በዋጋ፣ በጥራት እና በደህንነት ረገድ ያሉበትን አሉታዊ ገፅታው እንዲለወጥ የሚያስችል ምቹ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋትም ሌላው መርህ ነው፡፡
እንዲሁም ኢትዮጵያን በቀጣይ አስር ዓመታት ውስጥ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የላቀ ሚና እንዲጫወት ማስቻልም ትኩረቱ ነው፡፡

አዲሱ የኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያው ከረቂቅ ጀምሮ እስከ ፀደቀበት ድረስ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየታየ ያለፈባቸውን ሂደቶች፤ በዝግጅት ሂደቱ ውስጥም የተገኙ ግብዓቶች ተካትተው በጠቅላይ አቃቤ ሕግ አማካኝነት ግብዓት ተሰጥቶ የጸደቀ መሆኑም ተብራርቷል፡፡

በመመሪው የሚካተቱ የግንባታ ተዋናዮችና ዘርፎች፣ የመመሪያው ይዘቶች፣ የሚጠበቁ መስፈርቶች፣ የብቃት አረጋጋጭ እና መዝጋቢዎች ኃላፊነቶች የሚሉና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ ሰነዶች ለሰልጣኞች ቀርበዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለስራ አፈፃፀም ተግዳሮት ናቸው እንዲሁም መሻሻል ይገባቸዋል ያሏቸውን አስተያየቶች ሰጥተዋል፤፡ በዋናነትም ከፍትሃዊ አሰራር፣ ሚዛናዊነት ከመጠበቅ፣ ከመረጃ ነፃነት፣ ከመመሪው አስገዳጅነት እና ከአሻሚነት አንፃር ይሻሻሉ ሏቸውን ሃሳቦች አካፍለዋል፡፡
በአጠቃላም ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከፍ ከማድረግ አኳያ በመመሪው ውስጥ መካተት ያሉባቸው እንዲሁም እርምት ያስፈልጓቸዋል ያሏቸውን አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡

በቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይም መመሪያው እንደገና እርማት የሚወሰድበት አግባብ በቀጣይ የሚታይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በዋናነት ግን መመሪው በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ፣ ተወዳዳሪነቱ እንዲያድግ፣ ሙያ እና ዕውቀት ተኮር እንዲሆን፣ የተሳለጠና አስተማማኝ መረጃ እንዲፈጠር፣ የአሰራር ስርዓቱ እንዲዘምን፣ ከፍተኛ የሆነ የስራ ዕድልን እንዲፈጥር፣ ሙዊ ስነምግባር እና ሕጋዊነት እንዲሰፍን፣ ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግንባታ ስርኣት እውን እንዲሆን ለማስቻል ወሳኝነቱ ተሰምሮበታል፡፡
ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን በ4.2 ቢሊዮን ብር መንገድ ሊገነባ ነው

ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን የሚያስተሳስረው 160 ኪ.ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ፡፡

የግንባታ ስራውን የሚያካሂደው ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኋ/የተ/የግ/ማ የተባለ አገር በቀል የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡

የመንገዱን ጥራት ቁጥጥር እና የማማከር ሥራዎችን የሚያከናውነው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ነው።

የግንባታዉ ወጪው የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።
መንገዱ በገጠር ከ8-10 ሜትር ߹ በቀበሌ 12 ሜትር፣ በወረዳ የእግረኛ መንገድን አካቶ ከ19-24 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ይገነባል።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ።

በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው በሙያቸው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እያገለገሉ የነበሩ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች በታጣቂዎች ተገደሉ።

#አሥራት_ሺካ እና #ሮቤል_ልደቱ የተባሉት ወጣት ኢንጂነሮች ትላንት ሰኔ 8/2013 ለሥራ ጉዳይ "አማሮ ልዩ ወረዳ" ሲጓዙ "ጀሎ" በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል።

ሁለቱም ወጣት ኢንጂነሮች ባላቸው እውቀት ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት።

የወጣቶቹን ግድያ የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቀናል ብሏል።

በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን ባወጣው የሀዘን መግለጫ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ባልስልጣኑ 'ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት' ብሎ ከመግለፅ በዘለለ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስለግድያው ፣ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ተያያዥ መረጃ እንዲሰጠን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

@tikvahethiopia