Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
ERA: 👍👍👍👍

የሞምባሳ - ናይሮቢ - አዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሀዋሳ - ጭኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ተጠናቀቀ።
#ነጻ_አስተያየት_20_80
1) በቅርቡ እንደሰማናው ክብርት ከንቲባዋ
<<እጣ የወጣባቸው የ 20/80 ቤቶች የቁልፍ ርክክብ እስከ ጥቅምት 12/2013 ዓ.ም ይጠቃለላል>> አሉ ።

2) የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው (ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ የ20/80 ዕጣ ከደረሳቸው 32,653 ነዋሪዎች ውስጥ ውላቸውን አጠናቀው የጨረሱት 7,000 ሲሆኑ ቁልፍ የተረከቡ ደግሞ 245።

እንደሆኑ በቀጣይም ከመስከረም 22 እስከ ጥቅምት 12 ቀን ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ርክክቡ እንደሚቀጥል አክለዋል፡፡ (ሪፓርተር እንደዘገበው።)

3) ሸገር ኤፍኤም ሬድዮ በተለያየ ጊዜ ከሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ሃላፊዎች ጋር ቃለመጠይቅ በማድረግ በሰራው ዘገባ የ13ተኛው ዙር የ20/80 ቤቶች ለዕድለኞች በቅርቡ ቁልፍ ተሰጥቶ የ 14ተኛው ዙር እጣ ግንባታቸው በተጠናቀቁ ቤቶች ላይ እንደሚወጣ ተዘገበ።

4) የታከለ ንግግር "ቁልፍ ሰጥተን አጠናቀናል" ማለቱን ስንረሳ

5) በቅርቡ አሐዱ ኤፍኤም ሬድዮ በቀጥታ ከ እድለኞች ጋር ባደረገው የስልክ ውይይት ከቤቶች የጥራት ጉድለት እስከ የመሰረተ ልማት አለማከናወን፤ እንዲሁም
" ታዲያ ምን ችግር አለው ሲገቡ አፍርሰው ይሰሩታል "
አይነት በሀገር ሀብት ላይ የመቀለድ አሰራር የውስጥ ክፍሎች የአጨራረስ ግድፈቶች።"

6) ተሻሻለ የተባለው እና በቀን የሚዋዋሉ ሰዎች ቁጥርም ጨመረ ቢባልም እንኳ አሁን ባለው ሂደት ከቀጠለ :-
#ሀ) በቀን 400 ሰው በሳምንት 2,000
በ ወር 4,000
አንድ ሳምንት ቅፅ 3
በሳምንቱ ደግሞ የሽያጭ ውል ስለሆነ።

ሌላ አማራጭ አሰራር ካልተፈለገ
32,653 - 7,000 = 25,653
ይህም ማለት 25,653/4,000= 6.4 ወር ያስፈልጋል ማለት ነው።

#ለ) ንግድ ባንክ በ 2012 እና በ 2013 ዓ.ም አዳዲስ ሰራተኞችን ባለመቅጠሩ እና በከፈታቸው አዳዲስ ቅርንጫፎቹ ከነባር ቅርንጫፍ ሰራተኞች ላይ ቀንሶ ወደ አዳዲሶቹ በመመደቡ በአራቱ የብድር ማዕከላት የሰራተኛ እጥረት ተፈጥሯል።

በዚህ ምክንያትም ወረፋ መጠበቁ ንግድ ባንክ ላይም ይቀጥላል።

* * *ስለዚህ በአንድነት ሆነን ነገሮች ሁሉ ትክክለኛ መፍትሄ ካልተፈለገላቸው :-
#ቁልፍ የተረከቡት መሰረተልማቱ ያልተሟላና ወና ቤት ይዘው ቢገቡ የሌባ ሲሳይ ሆነው የመከራ ኑሮ ይገፋሉ።
#የፊኒሽንግ ስራዎችን እንኳን ለመስራት ያለ ውሀና መብራት የማይታሰብ ነው።
#ዉል ተዋውለው የጨረሱ እና ቁልፍ ያልተረከቡት ደግሞ ባልኖሩበት ቤት ቋሚ ወለድ ከፋይ ይሆናሉ።

የተሰሩ ቤቶችን መሰረተልማት አሟልቶ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ እንዲህ ዳገት ከሆነ አዳዲስ ቤቶችን መገንባት ምን ሊሆን ነው?

ከተማዋ ፅድት ያሉ እራሳቸውን፣ ዘመዶቻቸውን ፣ የጥቅም ተጋሪዎቻቸውን እና......... ነፃ ለማውጣት (ከድህነት ) በሚታትሩ ግለሰቦች እጅ ወደቀች እንዴ?

አዲስ አበባ ቤቴ
በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተጠቃሽ ከነበሩት የግል የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አኪር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ንብረት የነበረው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ በነበረበት የባንክ ዕዳ ምክንያት ከ203 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ በጨረታ ተሸጠ፡፡
የሕንፃ ስር ፓርኪንግ ቦታዎችን ለሌላ አገልግሎት ላዋሉ የሕንፃ ባለቤቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
**********
ኤጀንሲው ከከተማዋ ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመገናኛ ጎላጉል ቦሌ መድኃኒዓለም፣ ከጎላጉል ኡራኤል ቦሌ መድሃኒዓለም፣ ከኡራኤል እስጢፋኖስ በሚገኙ 200 ሕንፃዎች ስር የተዘጋጁ የፓርኪንግ ቦታዎች አጠቃቀም ላይ ፍተሻ ማድረጉን ገልጿል፡፡

በዚህም 30 ሕንፃዎች ቦታዎቹን ሙሉ በሙሉ በመቀየር ከታለመላቸው ውጭ ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ሲሆን፣ 30 ሌሎች ደግሞ ቦታዎቹን በከፊል ለሌላ አገልግሎት ማዋላቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል፡፡

የፓርኪንግ ቦታዎቹን ለሌላ ዓላማ ላዋሉ የሕንፃ ባለቤቶች የቃል እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም ኤጀንሲው ጠቅሷል፡፡
water%20works%20permit%20license.docx
13 MB
Water works license permit requirements.
የውሃ ስራዎች ስራ ተቆራጭ ማሞላት ይለባቸው መስፈርት
2
And Ethiopia is _________________?
እስኪ ወሪ አምጡ፣ ስራው እንኮን በዘመድ ነው።
Chinese companies dominated the list of Top Construction contractors in Africa

1. Sino-hydro Corporation
2. China Civil Engineering Construction Corporation (CCECC)
3. China Henan International Cooperation Group Company Limited
4. China Communications Construction Company(CCCC)
5. China Harbour Engineering Company (CHEC)
6. China Road and Bridge Corporation
7. SOGEA-SATOM
8. Mota-Engil China
9. Geo-Engineering Corporation (CGC)

Via - Centum real estate
Nine contractors have won a bid to build 118 kitchens and dining halls in public schools that are included under the School Feeding Programme across nine districts for 765 million Br. The bid for 38 schools has failed to materialise.

Via - AddisFortune
አስቀልዱብን !!!
building cost estimate excel.xls
1.1 MB
Building items cost estimate in excel
Forwarded from Construction Resources
Corrugated iron sheets with different thicknesses
35GAUGE.......170-200 Birr/pc
32 GAUGE.....285birr
30gauge........380birr
28Gauge.......450birr

Colored and galvanized
EGA SHEETS.... 240/LM

Roofing Nails.....73Birr/kg
Normal Nails.....53 Birr/kg
For more infos and special offers contact us
👍31
Addis Abeba, November 03/2020 – Four civilians were killed in Southern Oromia in Gujii Zone Gumi Eldalo Wereda on November 01, 2020. The victims were construction workers who were working on a bridge that connects Gujii to Borana. The assailants threw a grenade at the construction workers according to the Gujii Zone Administrator.
RIP
የፕሮጀክቶች መጓተት በ4 ቢሊየን ብር የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እስከ 16 ቢሊየን ብር ወጪ እንዲጠይቁ እያደረገ ነው

ከአፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን ባሻገር አብዛኛዎቹ መሰረተ ድንጋይ ከማስቀመጥ ያለፈ ተጠናቀው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ሲያደርጉ አለመታየቱን የቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተው በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ለውሃ ልማት ፈንድ የሚሰጠው ተዘዋዋሪ ብድር እንዲመለስ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ባለመመለሱ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንቅፋት መሆኑን የጠቆመው ቋሚ ኮሚቴው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገነቡ ንዑስ ጣቢያዎች የመብረቅ መከላከያ ባለመሰራቱ አብዛኛዎቹ ከሳምንት በላይ እያገለገሉ አለመሆኑም ተነስቷል።
2
የሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከህዳር 1ቀን 2013 ጀምሮ 85 በመቶ እንደሚሆን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሲሚንቶ አምራቶችና አከፋፋዮች ጋር በሲሚንቶ ምርት ግብይት እና ስርጭት ሰንሰለት ላይ የሚታዩ ችግሮች እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ወቅት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሼቴ አስፋው እንዳሉት የሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከህዳር 1ቀን 2013 ዓም ጀምሮ አሁን ከደረሰበት 63 በመቶ የማምረት አቅም 85 በመቶ ለማድረስ ስምምነት መደረሱን ጠቁመዋል፡፡

የብረታብረት የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ በበኩላቸው÷ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

አሁንም የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የማምረት አቅምን በማሳደግ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን ድርሻ በተሻለ መጠን ለማስቀጠል ይሰራል ማለታቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via - Ebc
👍1