Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
እኔ የምለው የመንግስት ባለስልጣናት ለምንድነው የኤክካቫቴር ኦፕሬተር ነን አሉ? PS dear government officials your people are not as idiots as you think they are, stop excessive show off in construction site.
📌 A team from the Ministry of Construction and the Office of the Auditor General traveled throughout the country to audit cobblestone projects that were started in 2005.
The World Bank supported the project financing close to 8 million USD for the construction audit.

The Cobblestone Project started in 2005 in a bid to create job opportunities for youth, and to provide attractive and long-lasting road and pavement in Ethiopian cities.

According to data from the Ministry of Construction and Urban Development, the cobble stone project has created close to half a billion jobs and more than 2,220 km of roads in over 140 cities between 2005 and 2014.
መንግሥት የሲሚንቶ ዋጋን ለማረጋጋት ከ100 ብር በላይ በመቀነስ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

በሩት ሙሴ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሲሚንቶ ዋጋ ለማረጋጋት ከአንድ መቶ ብር በላይ ቅናሽ በማድረግ ለሸማቾች ማቅረብ ጀመሩ።

በጥቅምት 7/2012 በንግድ ሚኒስቴር በተወሰነው መሰረት ግንባታ ለሚያከናውኑ እና ማስረጃ መቅረብ ለሚችሉ ነዋሪዎች የሚቀርብ ሲሆን፣ ለመንግሥት እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት የተሰጠ ኮታ መኖሩም ታውቋል።

በገበያ ላይ 330 ብር የሚሸጠው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት፣ በኢንዱስትሪ ግብአቶች አቅራቢ በኩንታል በ255 ብር እንደሚቀርብ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እመቤት ሙሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በገበያ ላይ 350 ብር የሚሸጠው ደርባ ሲሚንቶ፣ በማከፋፈያዎቹ ግን በ234 ብር ከ59 ሳንቲም ቀርቧል። ፋብሪካዎቹ ለገበያ ከሚያቀርቡበት ዋጋ ቅናሽ በማድረግ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት በአዲስ አበባ ለአብነት ኮልፌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ማቅረብ መጀመሩንም እመቤት ጨምረው ገልፀዋል።

ለግለሰብ ተጠቃሚ ደንበኞች በአንድ ጊዜ 100 ኩንታል ሲሚንቶ መግዛት የሚቻል ሲሆን፣ ይህንንም ለማግኘት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የፀደቀ የቤት ፕላን፣ ስድስት ወር ወይም የጊዜ ገደብ ያላለፈበት የግንባታ ፈቃድ፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና ከወረዳው ጽሕፈት ቤት የሚጻፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማሟላት እንደሚያስፈልግ መመሪያው ይደነግጋል። ለአጥርና ለጥገና ሥራዎች በአንድ ጊዜ እስከ 50 ኩንታል መግዛት እንደሚቻልም ተገልጿል።

ምርቱን ማግኘት ለሚፈልጉ አምራች ድርጅቶችም ከፍተኛው ማግኘት የሚችሉት የሲሚንቶ መጠን ከአራት መቶ ኩንታል የማይበልጥ ሲሆን፣ ይህም በየወሩ የሚሰጥ ነው። ድርጅቶቹ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ በተጨማሪ ፈቃዱን ከሰጠው አካል የማምረት አቅማቸውን እና ወርሃዊ የሲሚንቶ ፍጆታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ለመንግሥት እና ለሃይማኖት ተቋማት እስከ መቶ ኩንታል የሚሰጥ ሲሆን፣ ለግለሰብ ከተቀመጡት መስፈርቶች በተጨማሪ የተቋማቱ ኀላፊዎች የፈረሙበት የግዢ ጥያቄ ደብዳቤ መቅረብ እንዳለበት ተደንግጓል።

በአገሪቱ ዉስጥ በሚታየዉ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ምክንያት ከሥራ የተስተጓጎለ የመንግሥትም ሆነ የግለሰብ ግንባታ ወደ ሥራ እንዲመለስ በማሰብ እና የገበያ ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የኢንዱስትሪ ግብአት ልማት እና የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የበኩላቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

የሲሚንቶው ቅናሽ እስከመቼ እንደሆነ የጊዜ ገደብ አልተወሰነም። ነገር ግን የገበያውን ዋጋ ለማረጋጋት አዲስ አበባ ከሚገኙ የሽያጭ ማእከላት ባሻገር በአማራ፤ በኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልል ለማስፋፋት እንደታሰበ እመቤት ተናግረዋል።

addismaleda.net - አዲስ ማለዳ
ብቃታቸው ተረጋግጦ በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ማሽነሪዎች ውስን መሆናቸው ተመለከተ
****************
የኮስተባ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች
ታህሳስ 16 ቀን 2012 ዓ.ም
****************
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ማሽነሪዎች በአገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ለማድረግ እንዲቻል የወቅቱን የኮንስትራክሽን ስራዎች ዘመኑ የሚጠይቀውን ግብዓቶች በመጠቀም የሚሰሩ ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁና በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ የማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታመናል፡፡
ይህንን እውን ለማድረግም የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ምዝገባ ዳይሬክቶሬት በ2012 ኣ.ም እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ምዝገባ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
በዚሁ መሰረት 571 ለሚሆኑ ባለ ጎማ እና ባለሰንሰለት ተንቀሳቃሽ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አዲስ ምዝገባ በማካሄድ ብቃት ማረጋገጫ ተስጥቷል፡፡
እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ (አስፓልት ባቺንግ ፕላንት፣ ኮንክሪት ባቺንግ ፕላንት፣ ክሬሸር፣ ታወር -ክሬን እና የመሳሰሉ ማሽነሪዎች ) 64 አዲስ ምዝገባ በማካሄድ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም ለ824 ተንቀሳቃሽ፣ እንዲሁም ለ 94 ተንቀሳቃሽ ላልሆኑ ማሽነሪዎች የዕድሳት / የቦሎ/ አገልግሎት በመስጠት የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡
በሌላም በኩል ለ1211 ማሽነሪዎች ለዋስትና መያዣነት፣ የዕግድ ጥበቃ፣ የስም ዝውውር እና ዕገድ ላይ አገልግሎት መሰጠቱን ከተቋሙ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ምዝገባ ዳይሬክተሬት ተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲያም ሆኖ በርካታ ማሽነሪዎች ሳይመዘገቡ እና ብቃታቸው ሳይረጋገጥ በግንባታ ስራ ላይ እንደተሰማሩ የሚገመት ሲሆን፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍም የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ባለንብረቶች እንዲያስመዘግቡና በህጋዊነት እንዲሰማሩ ማስታወቁ ተመልክቷል፡፡
ብቃታቸው ያልተረጋገጠ ማሽነሪዎችን በግንባታ ስራ ላይ ማሰማራት ለግንባታ መጓተት፣ ለጥራት ጉድለት፣ ለዋጋ መናር እና ለአካባቢ ደህንነት ስጋት ምክንያት እንደሚሆን ከዳይሬክቶሬቱ የተገኘው መረጃ አስታውቋል፡፡
ብቃታቸው ያልተረጋገጠላቸውና ያልተመዘገቡ ማሽነሪዎችን በስራ ላይ አውሎ መገኘት በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በመገንዘብ ምዝገባ ያላካሄዱ አካላት የሕጋዊነት መስመርን መከተል እንደሚገባቸው ተሰምሮበታል፡፡
Foreign_Contractors_Performance.pdf
313.3 KB
More than 30 Chinese Contractors working on road projects with value of more than 60billon birr, only 2 Chinese companies have “pass” performance, all others failed.
Chinese ..... again ....

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረዋ - ሶሞዶ - ሰቃ - ሲሞዶ - ሊሙ መንገድ ግንባታን ለማስጀመር ነው ወደ ስፍራው ያቀኑት።

የማና፣ ሊሙ ኮሳ እና ሊሙ ሰቃ ወረዳዎችን የሚያቋርጠው መንገድ፥ 94 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው ግንባታው በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ለመንገድ ፕሮጀክቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ የቁጥጥር ስራውን ጨምሮ ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል።

ግንባታውን የቻይናው ቱ ሲ ጁ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሲያከናውነው ኋይት ናይት ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ደግሞ የቁጥጥር ስራውን የሚሰራ ይሆናል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ በወረዳ 21 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር ከ8 እስከ 10 ሜትር ስፋት ይኖረዋል።
Caption this, happy Monday
#Chinese_again
ቢሮው ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ(CCCC) ጋር የግንባታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከቻይናው የኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ(CCCC) ጋር የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሰረተልማቶች የተሟሉለት የትራፊክ ማኔጅመንት ማዕከል የሚያገለግል ዘመናዊ ህንፃ ለመስራት የግንባታ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ፕሮጀክቱም 831,843,924.43 እንደተመደበለትና በ18 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ በፊርማ ስነ-ስርዐቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም ይህ ግንባታ ሙሉለሙሉ የሚከናወነው ከምድር በታች ሲሆን ወደታችም 4 ወለሎች ይኖሩታል፡፡

የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ሐሙስ ታህሳስ 23/2012 ዓ/ም