Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
Forwarded from F҉.҉S҉.҉R҉ 😎 👊 via @like
የኮንሰልታንት ወርሀዊ ደመወዝ

በሀገራችን በየአመቱ የተለያዩ መንገዶች ግንባታቸው ተጠናቆ በመመረቅ ላይ ናቸው፨ ታዲያ እነዚህ መንገዶች በጥራት እንዲሰሩ ትልቁን አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት በሱፐርቪዥን የተመደቡ የኮንሰልቲንግ ሰራተኞች ናቸው፨ የዛሬ አስር አመት ለአንድ መንገድ የሚመደበው ከፍተኛው በጀት 600 ሚልዮን ብር አካባቢ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት 1.7 ቢልዮን ደርሱዋል፨ ነገር ግን በመንገድ ቁጥጥሩ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወጡት የኮንሰልቲንግ ሰራተኞች ከ 10 አመት በፊት የአንድ ሱፐርቫይዘር ደሞዝ 3,100 ብር የነበረው በአሁን ሰአት 3,800 ብር ነው፨ ሌላው የቀጣሪያቸው ዋና መስሪያ ቤት ለአንድ ሰው የሚጫረቱበት ደሞዝ የዛሬ 10 አመት ከነበረው አሁን በ 100 ፐርሰንት አድጉዋል፨ አብዛኛውን የጥራት ሀላፊነት ወስዶ የሚሰራው ሱፐርቫይዘር በ 10 አመት ውስጥ የ 800 ብር ለውጥ ብቻ አግኝትዋል፨
Do not do bet, but if you do make it scientifically.

https://t.me/betsprofessor
ከ6.1 ቢሊዮንብር በላይ በሆነ ወጪ 299 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍኑ የአራት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራ የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡


•1 የፕሮጀክቱ ስም፦ ኅሙሲት -እስቴ
የመንገዱ ርዝመት ፦ 76.6 ኪ.ሜትር
• የመንገዱ ደርጃ፡- አስፋልት ኮንክሪት
• ጨርታዉን ያሸንፈዉ ተቋራጭ ፦ Ningxia communication construction Co. Ltd.
• የማማከርና የቁጥጥር ስራ የሚሰራው፦ ኬቲም እና አላሚ አማካሪ መሐንዲሶች ከኮር አማካሪ መሐንዲሶች የግል ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ጋር በመተባበር
• የግንባታ ወጪ፦1,395,881,640.48(
• የግንባታዉን ወጪ የሚሽፈነዉ አካል፦ የአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት BADEA/OFID & GOV በመተባበር የሚሸፈን ይሆናል።
• ግንባታውን አከናውኖ ለመጨረስ የተሰጠው ጊዜ፦ የሶስት ዓመት

•2 የፕሮጀክቱ ስም፦ጩላሴ - ሶያማ (ሎት፦2)
• የመንገዱ ርዝመት ፦79.5 ኪ.ሜትር
• የመንገዱ ደርጃ፡- አስፋልት ኮንክሪት
• ጨርታዉን ያሸንፈዉ ፦ቻይና ሪል ዌይ 14 የተባለ የቻይና የስራ ተቋራጭ
• የግንባታ ወጪ፦1,800,000,000.00
• የግንባታዉን ወጪ የሚሽፈነዉ አካል፦በኢትዮጵያ መንግስት
ግንባታውን አከናውኖ ለመጨረስ የተሰጠው ጊዜ፦ ሶስት ዓመት


•3 የፕሮጀክቱ ስም፦ የአደሌ- ግራዋ
• የመንገዱ ርዝመት ፦ 55 ኪ.ሜትር
• የመንገዱ ደርጃ፡- አስፋልት ኮንክሪት
• ጨርታዉን ያሸንፈዉ ፦ሂቤ የስራ ተቋራጭ
• የግንባታ ወጪ፡- 1,436,300,000.00
• የግንባታዉን ወጪ የሚሽፈነዉ አካል፦ በኢትዮጵያ መንግስት
• ግንባታውን አከናውኖ ለመጨረስ የተሰጠው ጊዜ፦ የሶስት ዓመት

•4 የፕሮጀክቱ ስም፦ጎዴ - ቀላፎ (ሎት፦1)
• የመንገዱ ርዝመት ፦ 88.5 ኪ.ሜትር
• የመንገዱ ደርጃ፡- አስፋልት ኮንክሪት
• ጨርታዉን ያሸንፈዉ ተቋራጭ፦ ቻይና ሪልዌይ ሰቨንዝ ግሩፕ
• የማማከርና ቁጥጥር ስራውን፦ ስታዲያ የመሃንዲሶች አማካሪ ድርጅት ነው።
• የግንባታ ወጪ፦1,530,000,000 ( አንድ ቢሊየን አምስት መቶ ሰላሳ ሚሊየን )
• የግንባታዉን ወጪ የሚሽፈነዉ አካል፦ በኢትዮጵያ መንግስት
• ግንባታውን አከናውኖ ለመጨረስ የተሰጠው ጊዜ፦ ሶስት ዓመት ከግማሽ
It’s not just you Ethiopian Roads Authority website is down.
እኔ የምለው የመንግስት ባለስልጣናት ለምንድነው የኤክካቫቴር ኦፕሬተር ነን አሉ? PS dear government officials your people are not as idiots as you think they are, stop excessive show off in construction site.
📌 A team from the Ministry of Construction and the Office of the Auditor General traveled throughout the country to audit cobblestone projects that were started in 2005.
The World Bank supported the project financing close to 8 million USD for the construction audit.

The Cobblestone Project started in 2005 in a bid to create job opportunities for youth, and to provide attractive and long-lasting road and pavement in Ethiopian cities.

According to data from the Ministry of Construction and Urban Development, the cobble stone project has created close to half a billion jobs and more than 2,220 km of roads in over 140 cities between 2005 and 2014.
መንግሥት የሲሚንቶ ዋጋን ለማረጋጋት ከ100 ብር በላይ በመቀነስ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

በሩት ሙሴ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች የሲሚንቶ ዋጋ ለማረጋጋት ከአንድ መቶ ብር በላይ ቅናሽ በማድረግ ለሸማቾች ማቅረብ ጀመሩ።

በጥቅምት 7/2012 በንግድ ሚኒስቴር በተወሰነው መሰረት ግንባታ ለሚያከናውኑ እና ማስረጃ መቅረብ ለሚችሉ ነዋሪዎች የሚቀርብ ሲሆን፣ ለመንግሥት እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት የተሰጠ ኮታ መኖሩም ታውቋል።

በገበያ ላይ 330 ብር የሚሸጠው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት፣ በኢንዱስትሪ ግብአቶች አቅራቢ በኩንታል በ255 ብር እንደሚቀርብ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እመቤት ሙሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በገበያ ላይ 350 ብር የሚሸጠው ደርባ ሲሚንቶ፣ በማከፋፈያዎቹ ግን በ234 ብር ከ59 ሳንቲም ቀርቧል። ፋብሪካዎቹ ለገበያ ከሚያቀርቡበት ዋጋ ቅናሽ በማድረግ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት በአዲስ አበባ ለአብነት ኮልፌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ማቅረብ መጀመሩንም እመቤት ጨምረው ገልፀዋል።

ለግለሰብ ተጠቃሚ ደንበኞች በአንድ ጊዜ 100 ኩንታል ሲሚንቶ መግዛት የሚቻል ሲሆን፣ ይህንንም ለማግኘት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የፀደቀ የቤት ፕላን፣ ስድስት ወር ወይም የጊዜ ገደብ ያላለፈበት የግንባታ ፈቃድ፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና ከወረዳው ጽሕፈት ቤት የሚጻፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማሟላት እንደሚያስፈልግ መመሪያው ይደነግጋል። ለአጥርና ለጥገና ሥራዎች በአንድ ጊዜ እስከ 50 ኩንታል መግዛት እንደሚቻልም ተገልጿል።

ምርቱን ማግኘት ለሚፈልጉ አምራች ድርጅቶችም ከፍተኛው ማግኘት የሚችሉት የሲሚንቶ መጠን ከአራት መቶ ኩንታል የማይበልጥ ሲሆን፣ ይህም በየወሩ የሚሰጥ ነው። ድርጅቶቹ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ በተጨማሪ ፈቃዱን ከሰጠው አካል የማምረት አቅማቸውን እና ወርሃዊ የሲሚንቶ ፍጆታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ለመንግሥት እና ለሃይማኖት ተቋማት እስከ መቶ ኩንታል የሚሰጥ ሲሆን፣ ለግለሰብ ከተቀመጡት መስፈርቶች በተጨማሪ የተቋማቱ ኀላፊዎች የፈረሙበት የግዢ ጥያቄ ደብዳቤ መቅረብ እንዳለበት ተደንግጓል።

በአገሪቱ ዉስጥ በሚታየዉ የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ምክንያት ከሥራ የተስተጓጎለ የመንግሥትም ሆነ የግለሰብ ግንባታ ወደ ሥራ እንዲመለስ በማሰብ እና የገበያ ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የኢንዱስትሪ ግብአት ልማት እና የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የበኩላቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

የሲሚንቶው ቅናሽ እስከመቼ እንደሆነ የጊዜ ገደብ አልተወሰነም። ነገር ግን የገበያውን ዋጋ ለማረጋጋት አዲስ አበባ ከሚገኙ የሽያጭ ማእከላት ባሻገር በአማራ፤ በኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልል ለማስፋፋት እንደታሰበ እመቤት ተናግረዋል።

addismaleda.net - አዲስ ማለዳ