Construction Proxy
19.5K subscribers
530 photos
18 videos
77 files
284 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
This is Eyeruselam taking MSC in India 🇮🇳
The linked questioner prepared to assess the awareness on Green Building in Ethiopian construction sector.
https://forms.gle/jUYiKbY1GZpdVi2RA
Happy new Ethiopian year.
0 years experience in civil engineering
The above Invitation to bid in pdf
Construction Proxy
Photo
BRT coming up.
ባለስልጣኑ የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ሊያስጀምር ነው

አዲስ አበባ፡- መስከረም 19/2012 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ሊያስጀመር ነው::

በግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓቱ ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የባለስልጣኑ አመራሮች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ የአካባቢው ህብረተሰብና የስራ ተቋራጮች ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ በዓይነቱ ልዩ የሆነው የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት 3.8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ30-45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት ይኖረዋል፡፡ የዚህን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ የተባለ የስራ ተቋራጭ ይገነባዋል፡፡

የግንባታ ቁጥጥሩንና የማማከር ስራውን ደግሞ ቤስት አማካሪ ድርጅት የሚያከናውነው ሲሆን ለግንባታ ወጪውም ከቻይና መንግስት በተገኘ ብድር ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል፡፡
ይህን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ የዲዛይን ስራውን ጨምሮ ሁለት ዓመት ከ 6 ወራት ተይዞለታል፡፡

ይህ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት በሁለት በኩል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ(Tunnel) እና ተጨማሪ የፈጣን አውቶቢስ መተላለፊያ መስመር (Bus Rapid Transit)፣ ከስርና ከላይ መተላለፍ የሚያስችሉ ሁለት ትላልቅ ማሳለጫዎችም የሚኖሩት ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የዚህን የመንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከስራ ተቋራጩ ጋር መፈራረሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የወሰን ማስከበር ስራውም ከ85 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡

በርካታ የወሰን ማስከበር ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ መቻላቸው የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ያስችለዋል፡፡

በቀጣይም ከመንገዱ ግንባታ ጎን ለጎን የቴሌ እና የመብራት ሀይል ምሰስዎችን ጨምሮ ቀሪዎቹን የወሰን ማስከበር ስራዎች ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ ውስጥ የማንሳቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅም ከቂርቆስ፣ ከጎተራ፣ ከጎፋ፣ ከሳር ቤት፣ ከሜክሲኮ እና ከቄራ የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን ከማሳለጡም ባሻገር ለአካባቢውና አጠቃላይ ለከተማዋ የተለየ ገፅታን ያላብሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Construction 🚧 of bridge foundation