Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
ለግንባታ ግብዓት (የአርማታ ብረት እና የሬዲሚክስ ኮንክሪት አቅራቢዎች) የቀረበ ጥሪ!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በካፒታል ፕሮጀክት ቤቶችን እንደሚገነባ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በያዝነው በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ 100 ሺህ ቤቶችን በፍጥነትና በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ነድፎ ወደ ትግበራ ገብቷል ስለሆነም ለ100 ሺህ ቤቶች በቂ የሆነ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እንዲኖር ከብረትና አጠቃላይ የኮንክሪት ስራ ግብዓት አቅራቢዎች ጋር መወያየት የሚፈልግ በመሆኑ በስራው ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በሙሉ ግሪክ ክለብ አጠገብ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዉ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ማለትም እሁድ በ05/04/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:30 ላይ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ-የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
22👍14🔥1
ጥብቅ ማስታወቂያ ለጋራ መኖሪያ ህንፃ ግንባታ ለተመዘገባችሁ ስራ ተቋራጮች በሙሉ
👍1612👏2
ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣት ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አሸናፊዎች በተቋማችን በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ህዳር 20 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጥሪ ባስተላለፍነው መሰረት በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 በተቀመጠው የአስር ቀን ገደብ ውስጥ በርካታ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ቢሮ ቀርበው የሊዝ ዉል ፈጽመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች በደንቡ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርባችሁ ውል አልፈፀማችሁም።

በመሆኑም የሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 4 በግዜ ገደብ ዉል ያልፈፀሙ አንደኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል እንዲፈጽሙ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጣቸው በሚደነግገው መሰረት ከ06/04/2018ዓ.ም እስከ 08/04/2018 ባሉት 3/ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቀርባችሁ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 5 መሰረት አሸናፊነታችሁ ተሰርዞ ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች እድሉ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ታህሳስ 04/2018ዓ.ም
31👍13🤔2
ማስታወቂያ

ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ተመዝጋቢዎች
13👍13🥰2
7030(1).pdf
7.1 MB
List of applicants
👍219👏1
#ነዳጅ

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ከታሕሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታሕሳስ ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል።

አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር

የሌሎች ምርቶችም ዋጋ በታሕሳስ ወር በነበረበት ይቀጥላል።
👍16🙏4👏3👌3🔥2
648_የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ.pdf
2.7 MB
የ ኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ
- ኮንትራክተር ከ ደረጃ 1 እስከ 10
- የአማካሪ መሃንዲስ ፈቃድ
- ባለሙያ ሁሉም አይነት
👍4519
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ዛሬ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀመሩ።
👍3114
2018 2nd Q Construction Works (Only Direct Cost)(1).pdf
22.7 MB
የ2018 ዓ/ም 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

2018E.C  2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost)t

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
👍4124🔥3
1997 እና ለ2005 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በሙሉ!
http://aahdab.et/saving
2👍2810🙏4
#ነዳጅ
#የካቲት

" ከአውሮፕላን ነዳጅ በቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

#ማስታወሻ ፦ አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር
👍18🙏4👏2🤔2👌1
It would be better if the new road section were planned strictly as an NMT (Non-Motorized Transport) route, with no motorized traffic allowed, i am just saying .
አዲሱ የመንገድ ክፍል ለNMT (ለእግረኞችና ለብስክሌት) ብቻ እንዲዘጋጅ እና የሞተር ተሽከርካሪ እንዳይፈቀድ ቢሆን ይሻላል ነበር።
21👍21😁5🔥3🤔3
ዜና ሹመት
ዶ/ር ኢንጅነር መኮንን ጥበቡ ከየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሸሙ፡፡

ዶ/ር ኢንጅነር መኮንን ጥበቡ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ ኃላፊነቶች በመስራት ልምድ ያካበቱ ሲሆን በከተማው የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
👍3820