Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
በኢትዮጵያ ውስጥ በጥራት እና የጊዜው ማስረከብ ላይ የሚተማመኑት የሪል እስቴት ገንቢ ማን ነው?
Who is the most reliable real estate developer in Ethiopia in terms of quality and timely delivery?
For more,, check the link below: https://constructionproxy.com/real-estate/
Anonymous Poll
20%
NOHA
8%
DMC
20%
AYAT
6%
Century
4%
Dema
23%
Sunshine
11%
Temer
9%
Gift
27👍6🔥1
Forwarded from Construction Et Market
የምዝገባ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከደረጃ 1-7 ላሉ ሥራ ተቋራጮች ያወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የስራ ተቋራጮች ምዝገባ ከተለያዩ ተሳታፊዎች በቀረቡት አስተያየቶች መሰረት የስራ ተቋራጭ ምዝገባ ቀነ-ገደብ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ፣ በመሆኑም ምዝገባው ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ 5 ተከታታይ ቀናት እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ መራዘሙን ኮርፖሬሽኑ ያሳውቃል።

ስለሆነም፣ ሳትመዘገቡ ለዘገያችሁ ተቋራጮች፣ ይህንን የመጨረሻ ዕድል ተጠቅማችሁ በኦንላይን https://aahdcgeneral.et በመግባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በምዝገባው ሂደት እና ከምዝገባ በኋላ ለሚኖራችሁ ጥያቂ፣ ቅሬታ ०९६१° ১৯৮৮ ০২.৮ ০৭৯৮.৫০८९ https://aahdcgeneral.et/complaints/create ወይም በቴሌግራም https://t.me/aahdcsupport ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
19👍15😁1
አዲሱ ህግ
በቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ የሚገዙ ማሽነሪዎች፣
መመሪያ 1073/2025 አንቀጽ 138 ንዑስ አንቀጽ 7 ለአሸናፊው ተጫራች በሚፈቀድ የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለመንገድ ሥራና ለሕንጻ ግንባታ ሥራ የሚገዙ ማሽነሪዎች ዝርዝር፣
List of Machinery to Be Purchased with Advance Payment (Pursuant to Article 138(7) of the Directive).
👍2215
የነዳጂ ጭማሪ ይፋ ሆኗል
ቤንዚን 129.12
ናፍጣ 129.12

#fuel #ነዳጅ
👍2214🔥2👏1
ለግንባታ ግብዓት (የአርማታ ብረት እና የሬዲሚክስ ኮንክሪት አቅራቢዎች) የቀረበ ጥሪ!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በካፒታል ፕሮጀክት ቤቶችን እንደሚገነባ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በያዝነው በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ 100 ሺህ ቤቶችን በፍጥነትና በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ነድፎ ወደ ትግበራ ገብቷል ስለሆነም ለ100 ሺህ ቤቶች በቂ የሆነ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እንዲኖር ከብረትና አጠቃላይ የኮንክሪት ስራ ግብዓት አቅራቢዎች ጋር መወያየት የሚፈልግ በመሆኑ በስራው ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በሙሉ ግሪክ ክለብ አጠገብ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዉ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ማለትም እሁድ በ05/04/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:30 ላይ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ-የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
22👍14🔥1
ጥብቅ ማስታወቂያ ለጋራ መኖሪያ ህንፃ ግንባታ ለተመዘገባችሁ ስራ ተቋራጮች በሙሉ
👍1612👏2
ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣት ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አሸናፊዎች በተቋማችን በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ህዳር 20 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጥሪ ባስተላለፍነው መሰረት በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 በተቀመጠው የአስር ቀን ገደብ ውስጥ በርካታ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ቢሮ ቀርበው የሊዝ ዉል ፈጽመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች በደንቡ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርባችሁ ውል አልፈፀማችሁም።

በመሆኑም የሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 4 በግዜ ገደብ ዉል ያልፈፀሙ አንደኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል እንዲፈጽሙ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጣቸው በሚደነግገው መሰረት ከ06/04/2018ዓ.ም እስከ 08/04/2018 ባሉት 3/ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቀርባችሁ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 5 መሰረት አሸናፊነታችሁ ተሰርዞ ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች እድሉ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ታህሳስ 04/2018ዓ.ም
31👍13🤔2
ማስታወቂያ

ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ተመዝጋቢዎች
13👍13🥰2
7030(1).pdf
7.1 MB
List of applicants
👍219👏1
#ነዳጅ

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ከታሕሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በታሕሳስ ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል።

አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር

የሌሎች ምርቶችም ዋጋ በታሕሳስ ወር በነበረበት ይቀጥላል።
👍16🙏4👏3👌3🔥2
648_የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ.pdf
2.7 MB
የ ኮንስትራክሽን ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ መመሪያ
- ኮንትራክተር ከ ደረጃ 1 እስከ 10
- የአማካሪ መሃንዲስ ፈቃድ
- ባለሙያ ሁሉም አይነት
👍4519
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ዛሬ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀመሩ።
👍3114
2018 2nd Q Construction Works (Only Direct Cost)(1).pdf
22.7 MB
የ2018 ዓ/ም 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

2018E.C  2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost)t

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
👍4124🔥3
1997 እና ለ2005 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በሙሉ!
http://aahdab.et/saving
2👍2810🙏4
#ነዳጅ
#የካቲት

" ከአውሮፕላን ነዳጅ በቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

#ማስታወሻ ፦ አሁን ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር
👍18🙏4👏2🤔2👌1