Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
Construction Proxy
648_የኮንስትራክሽን_ብቃት_ማረጋገጫና_ምዝገባ_መመሪያ_2013.pdf
የ ሙያ ፍቃድ / professional license🪪 /ለማውጣት ምን ያስፈልጋል
http://www.eservices.gov.et 🌎
ከላይ በተቀመጠው ዋብሳይት በመግባት user Account በመክፈት የ ሙያ ፍቃድ ማውጣት ትችላላችሁ።
ይህ የ ሙያ ፍቃድ ዲዛይን ስታደርጉ Title block ላይ ከ ስማችሁ ጎን Registration Number / የምዝገባ ቁጥር ይያያዝላችኋል ።
https://constructionproxy.com/construction-certification-and-registration-regulation-directive-no-648-2021/
👍3422🙏5😁4👏3
2018 1st Q. CONSTRUCTION WORKS ONLY DIRECT COST 01.02.2018.pdf
24.2 MB
የ2018 1ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

2018E.C  1st Quarter Construction Works (Only Direct Cost)


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
👍5730👏4
Forwarded from Construction Et Market
በ70/30  የጋራ ህንፃ ማህበር ቤት በተጠባባቂነት መመዝገቢያ የኦንላይን ሊንክ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfPZUc1SrNdhK9sETiypT9cjZT7jebHtAWnLmP43EhXPDjwuQ/viewform
22👍9
Leadership Shake-Up at ECWC and ERA
ERA appoints new Deputy Director Generals, while ECWC CEO Yonas is replaced by Robel from EEC — a leader known for his dynamic style in the construction industry.
👍3118🥰2
ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሁለት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ተሾሙ !!

ኢንጂነር ብርሃኑ ተስፋዬ በግንባታ ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት እንዲሁም አቶ አለማየሁ ተረፈ በኮርፖሬት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ከጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማችንን እንዲያገለግሉ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተሾመዋል።
ሁለቱ አመራሮች ተቋማችን ከመንግስት የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ በተሻለ ብቃት እና በቁርጠኝነት በመከወን የዘርፉን ራዕይ ይበልጥ እንደሚያሳኩ በመተማመን በከፍተኛ አመራርነት እንኳን ወደ ተቋማችን ተቀላቀላችሁ በማለት መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን!
Source:
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
👍2620👎2
ECC welcomes its new CEO, Eng. Robel Tsegay, and we also wish him great success in his leadership journey.
👌6041👍15👏11💯6
ኢንጅነር ገላና ኮራ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የልዩ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች አስተዳደር ፕሮግራም አስተባባሪ ኾነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 12 ቀን 2018 ጀምሮ ተሹመዋል።

Congratulations to ኢንጅነር ገላና ኮራ ::
👍4617👎5👌5👏3
🚧 ኮንትራክተር ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሂደቶች

1. የንግድ አይነትና የመደብ ደረጃ መምረጥ
በህንፃ፣ መንገድ፣ ውሃ ወይም ኤሌክትሮ-ሜካኒካል ደረጃ መመዝገብ እንደሚፈልጉ ይወስኑ። የመደብ ደረጃው በሰራተኞች፣ ተሞክሮ፣ መሳሪያና ፋይናንስ አቅም ይወሠናል።

2. የንግድ መመዝገብና ታክስ መለያ (TIN) ማውጣት
በንግድ መዝገብ ቢሮ የንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር ያግኙ። ይህ ከECA ለመመዝገብ ከመጀመሪያ የሚፈለገው መሠረት ነው።

3. የአስፈላጊ ሰነዶችን ማዘጋጀት
ለአዲስ ኮንትራክተሮች የተከታታይ አዲቲድ ፋይናንስ ሪፖርት እና organization chart አያስፈልግም።

4. ግምገማ እና መደብ መመደብ (Evaluation & Grading)
ኢትዮጵያ ሥራ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን (ECA) የተላኩትን ሰነዶች በእያንዳንዱ መደብ መስፈርቶች መሠረት ይገምጻል።
ይህ ግምገማ የሚያካትቱት፡
የቴክኒክ ሰራተኞች ብቃትና ልምድ፣
የሥራ ዘመን (ተሞክሮ)፣
የመሳሪያ አቅም፣

የፋይናንስ አቅም እና የኩባንያው ድርጅት ተደራሽነት ናቸው።
ባለሥልጣኑ ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ፣ ቃለ መጠይቅ ወይም በቦታ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል።
መስፈርቱን ካሟሉ የኮንትራክተር ደረጃ ይመድባችሁ እና የመመዝገብ ምስክር ወረቀት ይሰጣችሁ።

5. በECA መድረክ ላይ መመዝገብ
በመስመር ላይ ይመዝገቡ፡
:
ECA መዝገብ መድረክ (registration.eca.et)

6. የክፍያ ክፍያና ፈቃድ መቀበል
ክፍያውን ካከፈሉ በኋላ የብቃት ምስክር ወረቀት ይወስዳሉ።

7. Etrade ላይ online በመግባት ንግድ ምዝገባ በማስገባት , የንግድ ፈቃዱን መውሰድ ::

8. በየመንግስት ጨረታ (e-GP) መመዝገብ
የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ለመተካት በe-GP መድረክ https://egp.ppa.gov.et/
መመዝገብ ያስፈልጋል።
57👍32👏1🤔1
Forwarded from Construction Et Market
Qorannoo_Gabaa_galteewwan_ijaarsaa_Marsaa_2ffa_Bara_201822222.pdf
18.9 MB
Oromia Construction Authority (OCA) የ2018 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት የግንባታ ሥራዎች የቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት ሰነድ

@ConstructionIE
👍3315🤔3
From ECA
ለተገልጋዮቻችን በሙሉ:-

ውድ ተገልጋያችን በተቋማችን ሥራ ክፍሎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና ለማሳደግ የእርስዎ አስተያየት ገንቢ ስለሆነ እባክዎ ከታች ባለው የአገልግሎት እርካታ መጠይቅ ማስፈንጠሪያ ወይንም QR Code በመጠቀም የተዘረዘሩትን መጠይቆችን በትክክልና በጥንቃቄ እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

Dear Customer,

Your feedback plays a vital role in improving and enhancing the services provided by our organization's departments. Therefore, we kindly ask you to complete the Service Satisfaction Survey form or use the QR code provided below accurately and carefully.

Application Link: https://forms.gle/cB6dFcQfrDS6ZFPf8
39🔥3🥰1
AAHDC.pdf
1.9 MB
▶️ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚያከናውናቸው አዳዲስ የጋራ  የመኖሪያ  ህንፃዎች  ግንባታ ተሳታፊ የሚሆኑ ስራ ተቋራጮችን ለመመልመል የሚያስችለው ማስታወቂያ  ይፋ ማድረጉ ይታወሳል ፤

▶️ ለመሆኑ ይህንን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ተቋራጮች መመልመያና የስራ ስምሪት መመሪያ ቁጥር 180/2017 ምን ይላል ?

▶️ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት መመሪያውን ታገኙት ዘንድ  አያይዘናል።
ሊንኩን ይከተሉ
Source: chamber of Commerce
👍2617
በኢትዮጵያ ውስጥ በጥራት እና የጊዜው ማስረከብ ላይ የሚተማመኑት የሪል እስቴት ገንቢ ማን ነው?
Who is the most reliable real estate developer in Ethiopia in terms of quality and timely delivery?
For more,, check the link below: https://constructionproxy.com/real-estate/
Anonymous Poll
20%
NOHA
8%
DMC
20%
AYAT
6%
Century
4%
Dema
23%
Sunshine
11%
Temer
9%
Gift
27👍6🔥1
Forwarded from Construction Et Market
የምዝገባ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከደረጃ 1-7 ላሉ ሥራ ተቋራጮች ያወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የስራ ተቋራጮች ምዝገባ ከተለያዩ ተሳታፊዎች በቀረቡት አስተያየቶች መሰረት የስራ ተቋራጭ ምዝገባ ቀነ-ገደብ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ፣ በመሆኑም ምዝገባው ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ 5 ተከታታይ ቀናት እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ መራዘሙን ኮርፖሬሽኑ ያሳውቃል።

ስለሆነም፣ ሳትመዘገቡ ለዘገያችሁ ተቋራጮች፣ ይህንን የመጨረሻ ዕድል ተጠቅማችሁ በኦንላይን https://aahdcgeneral.et በመግባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በምዝገባው ሂደት እና ከምዝገባ በኋላ ለሚኖራችሁ ጥያቂ፣ ቅሬታ ०९६१° ১৯৮৮ ০২.৮ ০৭৯৮.৫০८९ https://aahdcgeneral.et/complaints/create ወይም በቴሌግራም https://t.me/aahdcsupport ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
19👍15😁1
አዲሱ ህግ
በቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ የሚገዙ ማሽነሪዎች፣
መመሪያ 1073/2025 አንቀጽ 138 ንዑስ አንቀጽ 7 ለአሸናፊው ተጫራች በሚፈቀድ የቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለመንገድ ሥራና ለሕንጻ ግንባታ ሥራ የሚገዙ ማሽነሪዎች ዝርዝር፣
List of Machinery to Be Purchased with Advance Payment (Pursuant to Article 138(7) of the Directive).
👍2215
የነዳጂ ጭማሪ ይፋ ሆኗል
ቤንዚን 129.12
ናፍጣ 129.12

#fuel #ነዳጅ
👍2214🔥2👏1
ለግንባታ ግብዓት (የአርማታ ብረት እና የሬዲሚክስ ኮንክሪት አቅራቢዎች) የቀረበ ጥሪ!!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በካፒታል ፕሮጀክት ቤቶችን እንደሚገነባ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በያዝነው በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ 100 ሺህ ቤቶችን በፍጥነትና በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ነድፎ ወደ ትግበራ ገብቷል ስለሆነም ለ100 ሺህ ቤቶች በቂ የሆነ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እንዲኖር ከብረትና አጠቃላይ የኮንክሪት ስራ ግብዓት አቅራቢዎች ጋር መወያየት የሚፈልግ በመሆኑ በስራው ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በሙሉ ግሪክ ክለብ አጠገብ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዉ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ማለትም እሁድ በ05/04/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:30 ላይ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ-የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
22👍14🔥1
ጥብቅ ማስታወቂያ ለጋራ መኖሪያ ህንፃ ግንባታ ለተመዘገባችሁ ስራ ተቋራጮች በሙሉ
👍1612👏2
ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣት ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አሸናፊዎች በተቋማችን በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ህዳር 20 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጥሪ ባስተላለፍነው መሰረት በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 በተቀመጠው የአስር ቀን ገደብ ውስጥ በርካታ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ቢሮ ቀርበው የሊዝ ዉል ፈጽመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች በደንቡ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርባችሁ ውል አልፈፀማችሁም።

በመሆኑም የሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 4 በግዜ ገደብ ዉል ያልፈፀሙ አንደኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል እንዲፈጽሙ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጣቸው በሚደነግገው መሰረት ከ06/04/2018ዓ.ም እስከ 08/04/2018 ባሉት 3/ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቀርባችሁ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 5 መሰረት አሸናፊነታችሁ ተሰርዞ ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች እድሉ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ታህሳስ 04/2018ዓ.ም
31👍13🤔2