በአያት ሪል እስቴት በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ
ሰኔ 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል።
አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል።
በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።
የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።
በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሐዱ ያነጋገራቸው የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል።
እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።
በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።
ምንጭ: አሐዱ ራድዬ

❤22😭17😱5
የብረት ዋጋ ስንት ገባ, ቆርቆሮ ስንት ገባ: ብለው አሁንም ይደውላሉ, በዚህ በቴክኖሎጅ ዘመን በ ነፃ ሁሉንም online ገብተው ይመልከቱ
Construction Proxyን የማያውቅ መሃንዲስስ አለ? 11 አመት የሞላው ብቸኛው የኮንስትራክሽን ዌብ ሳይት ነው:: visit the website
constructionproxy.com

❤9💯8👍7
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የጎርፍ አደጋ ቅድመ-መከላከል ሥራ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ገለፀ
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ይህን ችግር ለመቅረፍ ባለፉት 11 ወራት ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመር ጽዳት እና ጥገና ሥራ ተከናውኗል።
በበጋው ወራት ሲከናወን የቆየው የጎርፍ አደጋ ቅድመ-መከላከል ሥራ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሳምንት የድሬኔጅ መስመር ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ገዳመ እየሱስ የሚጠቀስ ነው።
የክረምቱን ወቅት የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቀነስ ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚገኙት ክፍት የመንገድ ዳር የውሃ መውረጃ መስመሮችን በጋራ በማፅዳት የበኩሉን አውንታዊ ሚና እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ጥሪውን ያቀርባል።
ምንጭ: የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

❤12👍10🙏1
ደሞዝ አልከፈልከኝም በሚል ምክንያት አሰሪውን የገደለ ወንጀለኛ በ21አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሹ ጌቱ መስፍን ይባላል፤ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሀሴ 27 ቀን 2014 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ30 ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለገሃር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ኖህ ሪል ስቴት ከሚያሰራው ህንፃ 16ኛ ጅምር ፎቅ ላይ ነው።
ሟች ሀጂብ ያሲን የተባለው ግለሰብ ከኖህ ሪል እስቴት ኮንትራት በመውሰድ ከስሩ በርካታ ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ነው።
ነሀሴ 27 ቀን 2014 ዓ/ም የዘወትር ስራውን ለማሰራት ሰራተኞችን ወደ የስራቸው ያሰማራል። ተከሳሽም ሟች የነበረበት ቦታ ጭር ማለቱን እና ማንም አለመኖሩን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ደሞዜን ከለከልከኝ በሚል ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ሟች ሀጂብ ያሲንን ስራ እየሰራ ባለበት 16ኛ ፎቅ ላይ በፌሮ ብረት ግንባሩን በመምታት እና አንገቱን በሽቦ ገመድ በማነቅና በማሰር ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ሟችን ከህንፃው ተሸክሞ በማውረድ የህንፃው መሰረት ስር የሚገኝ የተጠራቀመ ውሃ ውስጥ አስከሬኑን በመጣል ከአካባቢው ይሰወራል።
የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ በተደረገ ጥረት ተከሳሽ ጌቱ መስፍን ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ምንም እንዳልተፈፀመ በኔጌሌ ቦረና ከተማ በአንድ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ በመስራት ላይ እንዳለ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
በተከሳሽ ጌቱ መስፍን ላይ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ እንደተመሰረተበት የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ተከሳሽ ጌቱ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በ21 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት ገልጿል።
አዲስ አበባ ፖሊስ

❤30👌6🙏4😱3😭1
Construction Resources
የአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ በስኔ ወር የሚቀጥል ሲሆን የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ በቀጣይ በሥራ ላይ የሚቆይ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሠረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት የተወሰነ መሆኑን እየገለፅኩ የህዝብ ማስታወቅያና የሁሉም ከተሞች…
" የነዳጅ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - ሚኒስቴሩ
የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።
የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።

👍12❤3👏3
Forwarded from Tender ጨረታ
New Document(7).PDF
5.7 MB
የ6ኛው ዙር የ40/60 ንግድ ቤቶች የጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር
https://t.me/constructiontenders
https://t.me/constructiontenders
👍5❤3🙏2
Forwarded from Construction Et Market
Granite Direct from Factory!
All Products at Wholesale Prices 🔥🔥🔥
Starting from just 4800 Birr! ⚡⚡⚡
Contact Us:
Phone: +251-9444-888-88
Telegram: @granite_ethiopia
Delivery Available Across Ethiopia 🚛🚛🚛
Cut SIze
Window Sill
Tread & Riser
60x60 CM
40x40 CM
Tiles
Manufacturing Location:
Teja Granite, near ECF School, Aleltu Woreda (15 KM from Sendafa)
Call : +251-9444-88-888

❤9👍9
የህንፃ ግንባታ ደህንነትን ባለማስጠበቅ የ142 ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ
#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር የህንፃ ደህንነትን ባለመጠበቅ የአካል ጉዳት እና የህይወት ማጣት እንዲከሰት ምክንያት የሆኑ የግንባታ አማካሪ፣ ተቋራጮችና የህንፃ ባለቤቶች ላይ ከእስራት እስከ ገንዘብ ቅጣት እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
ለአራዳ ገለፃ ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር አበበ እሸቱ 2 ሺህ 667 ህንፃዎችን ላይ ባደረግነው ምልከታ 1 ሺህ 557ቱ የሰራተኛን እና የአጎራባችን ደህንነት እንዳልጠበቁ ተረድተናል ብለዋል።
የችግሩን ምንጭ ስንመለከትም ለህንፃ ደህንነት ሥራዎች ትኩረት አለመስጠትና በጀት አለመመደብ መሆናቸውንም ተገንዝበናል ነው ያሉት።
ስለ ህንፃ ግንባታ ደህንነት ስራ ተቋራጩ፣ አማካሪውና አጠቃላይ በስራው የሚሳተፉ አካላት ይህንን ከግንዛቤ አስገብተው እንዲሰሩ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አጽንዖት ሰጥቷል።
#aradaFm

❤13👍13😱3
Forwarded from Construction Resources
2017 4th Quarter Constraction Works Item Direct Cost (1).pdf
22.3 MB
የ2017 4ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
You can compare with
https://t.me/ConstructionResources/227
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
You can compare with
https://t.me/ConstructionResources/227
👍24❤20