Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
ማስታወቂያ ለማህበር ቤት online ተመዝጋቢዎች በሙሉ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
👍132🔥2👏1
Forwarded from Tender ጨረታ
ጨረታ
ሪፖርተር  ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ
👍225🔥3
#ለመረጃ፦ ከሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ተለውጧል! ቤንዚን ከ112.67 ወደ 122.53 ብር አድጓል!
👍15👎15🔥62🥰1
አህያ በኮሪደር መንገዶች ላይ መንዳት ተከልክሏል
በመዲናዋ በተለይም በዋና ዋና መንገዶች ላይ የኮሪደር ልማቱን ከመጠበቅ አንፃር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የገለጸው የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፤ ወደፊት ምንም አይነት የእንስሳት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ለማድረግ ተጠናክሮ እንደሚሰራበት አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት በከተማዋ አገልግሎት ላይ ከሚውሉ እንስሳት አንዷ የሆነችውን አህያን በተመለከተ፤ በኮሪዶር መንገዶች ላይ መንዳት የተከለከለ መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።
"ዘመን እየተሻሻለ ነው፣ ድሮ በአህያ ነበር ጭነቶቻችንን የምንጭነው፤ አሁን ደግሞ በተሽከርካሪ ነው" ሲሉ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ አሁን ላይ ከተሽከርካሪም ደግሞ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መምጣታቸውን አንስተዋል።
ከዚህ አንጻር ከተማ ከቴክኖሎጂ ጋር የተቀናጀ አሰራር እንጂ ወደ ኋላ ተመልሶ የቀሩ የትራንስፖርት አማራጮችን የሚጠቀምበት ሁኔታ እንደሌለ አፅንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም የኮሪደር ልማቱን አጠቃቀም በተመለከተ ለማህበረሰቡ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰራቱን ገልጸው፤ አውቆ የሚያጠፋ ካለ ግን የሕግ ማስከበር ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
(አሃዱ)
👍22😁12🤔3😱3👏1
Call for paper
👍193
በአዲስ አበባ በብስክሌት ትራንስፖርት መጋራት አገልግሎት መስራት ለሚፈልጉ ፈቃድ መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በደንብ ቁጥር 183/2017 የብስክሌት መጋራት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ አፅድቆ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

ደንቡን መሰረት በማድረግ በብስክሌት መጋራት አገልግሎት ላመለከቱ ዘጠኝ ድርጅቶች እውቅና እና ፈቃድ መስጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

Source: Fana
👍133👏1
የቤቶች የግንባታ ዋጋ ግምት ሠንጠረዥ (በየሩብ ዓመቱ ሊሻሻል ይችላል)
በአ.አ. የቤቶች ልማት ዋጋ ግምት መሰረትም G+9 - G+21 ያሉ ቤቶች 35,000 ብር በካሬ ይገመታል :: ይህም የመሬት ዋጋ ወይም የሊዝ ዋጋ ን አይጨምርም::
በዚህም ግምት በባለ 1 መኝታ 72 ካሬ ታስቦ 2.5 ሚሊዬን ብር ይሆናል ማለት ነው::
🙏17👍85👌1
Last year Senegal🇸🇳 launched an ambitious Bus Rapid Transit (BRT) project in Dakar to revolutionise its notoriously congested traffic.

The buses, which run on dedicated lanes, are 100% Electric are designed to serve 300,000 Senegalese daily. They offer a fast, comfortable and safe alternative to existing means of transport.

In East Africa only Tanzania🇹🇿 has successfully implemented it's BRT system and is set to expand.

Kenya 🇰🇪 and Ethiopia 🇪🇹 continues to face challenges and resistance in implementing its BRT system.

Very impressive 👏
👍194👏3
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ እና በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ዛሬ የተካሄደው የስምምነት ሰነድ፦

☑️ከ41 ሺ በላይ በአዲስ አበባ ውስጥ
     ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን የቤት
     ባለቤት ያደርጋል፡፤

☑️ ለመምህራን ቅድሚያ ይሰጣል፤

☑️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቤቶቹ
     ግንባታ የሚሆን 120 ቢሊዮን ብር
     አዘጋጅቷል፤

☑️ የመንግስት ሰራተኛው 25 በመቶ
     የሚቆጥብ ሲሆን ባንኩ 75 በመቶ
     ብድር በማመቻቸት በ20 አመት
     ተከፍሎ  የሚያልቅ ነው ።

☑️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቤቶቹ
     ግንባታ ወጪ 75  በመቶ ብድር
     ለማህበራቱ የሚለቀው ማህበራቱ 25
    በመቶውን ሲቆጥቡ ነው።

☑️ቤቶቹ በሶስት ዓመታት ውስጥ
    ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ...
   የሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮችን እና
   ሌሎችንም  የያዘ ነው።
👍279😁6
China has transformed a 157.79 km section of the Beijing–Hong Kong–Macao Expressway in
Hubei Province using AI-controlled pavers, rollers, and support vehicles. Advanced algorithms,
leveraging centimeter-level GPS and obstacle detection, enabled seamless, jointless paving
with zero trimming errors, remotely managing SANY SAP200C-10 pavers and robotic rollers
without onboard crews, marking a leap in automated construction.
#AIConstruction #BeijingHongKongMacao #SmartPaving #RoboticTechnology
#InfrastructureInnovation
👍24🤔97👏2🤯1
አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION

በአማራጭ ቴክኖሎጂ ግንባታዎችን የሚያከናውኑ ተቋራጮችን ለመጋበዝ የቀረበ የጥሪ ማስታወቂያ
👍158😁2
Forwarded from Construction Resources
የአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ
የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ በስኔ ወር የሚቀጥል ሲሆን የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ በቀጣይ በሥራ ላይ የሚቆይ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሠረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት የተወሰነ መሆኑን እየገለፅኩ የህዝብ ማስታወቅያና የሁሉም ከተሞች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ መደረጉን አሳዉቃለሁ፡፡
👍97👏1
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ኢድ-ሙባረክ!
እንኳን ለ1,446 ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ConstructionProxy.com
🙏1511
የጨረታ ማስከበሪያ ከፍተኛው መጠን ከ500ሺ ወደ 2 ሚሊየን ከፍ ተደረገ::

የመንግስት መ/ቤቱ የጠቅላላ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከ0.5% ያላነሰ እና2% ያለልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ወስኖ በጨረታው ጥሪው እና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ መግለፅ ይኖርበታል፡፡ በዚህ መሠረት የሚወሰነው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከብር 2,000,000 (ሁለትሚሊዮን ብር) የበለጠ መሆን የለበትም፡፡ 

አዲሱ የፌደራል የግዥ መመሪያ 1073/2017 ወደ ስራ ገብቷል። ዝርዝሩንና መመሪያውን 👇ያገኙታል::
@procinsightet/60
👍1910🙏3😁2🔥1
ከአንድ ትርሊዮን በላይ የሚገመት ሀብት የሚፈልጉት የተጀመሩ መንገዶች

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትርሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል ።

የገንዝብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

ሚኒስትር ዴኤታው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ከተለያዩ የብድር አቅራቢ ተቋማት በተገኘ ብድርና ከልማት አጋሮች በተገኘ ድጋፍ በርካታ መንገዶች እየተሰሩ ነው ።

እንደሀገር የተጀመሩትን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከአንድ ነጥብ ሶስት ትሪሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል ዘገባው የጋዜጣ ፕላስ ነው ።
26👍7🤔4👌2💯2
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions
👍246👏2
የብረት ዋጋ ስንት ገባ, ቆርቆሮ ስንት ገባ: ብለው አሁንም ይደውላሉ, በዚህ በቴክኖሎጅ ዘመን በ ነፃ ሁሉንም ገብተው ይመልከቱ
Construction Proxyን የማያውቅ መሃንዲስስ አለ? 11 አመት የሞላው ብቸኛው የኮንስትራክሽን ዌብ ሳይት ነው::
constructionproxy.com
👍2411💯4
ዜና እረፍት።
አልቤርቶ ቫርኔሮ።

ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ስራቸው የሀገራችንን የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው።

ከታሪካዊ ስራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል።

የሥራ ውርሳቸው በነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል። ለነፍሳቸው ረፍትን፣ በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ምንጭ። ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ
😭319😱9👍3
በአያት ሪል እስቴት በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ

ሰኔ 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል።

አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል።

በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል።

የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሐዱ ያነጋገራቸው የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል።

እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።


ምንጭ: አሐዱ ራድዬ
22😭17😱5