Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
#ሲሚንቶ

" ከዛሬ ጀምሮ በሚኒስትር መ/ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ቀርቷል " - ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።

በዚህም ወቅት " ከዚህ ቀደም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በኩል ይደረግ የነበረዉ የሲሚንቶ ግብይት ትስስር ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ቀርቷል " ብለዋል።

አምራቾች በራሳቸዉ ኃላፊነት በሚመርጧቸዉ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች በኩል ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

የሲሚንቶ ገበያዉን ለማረጋጋት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ያሉ ሲሆን የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማያቀርቡ በማናቸዉም የሲሚንቶ አምራች ላይ " የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሚኒስትሩ " አዲሱን ዉሳኔና አቅጣጫ ተከትሎ በግብይት ሰንሰለቱ የደላላ ጣልቃ ገብነት የከሰመ፣ ለመንግስት ፕሮጀክቶችና ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ አስተማማኝ የሲሚንቶ አቅርቦት የተረጋገጠ፣ አምራቾችም ተገቢዉን ትርፍ እያገኙ የከምፓኒዎቻቸዉን ዘላቂ ዕድገት የሚያስቀጥሉበት እንዲሆን " ብለዋል።

የግብይት ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ከካሽ ክፍያ ነጻ ሆኖ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እንዲፈጸም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በውይይት መድረኩ ወቅት አምራቾች የምርት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ተብሏል።

ሲሚንቶ አምራቾች አዲሱን ውሳኔ በማክበር እንደሚተገብሩ ተናግረው ነገር ግን የማምረቻ ግብዓት ፣ የኃይል አቅርቦትና ተያያዥ ችግሮች እንዲፈቱላቸዉ ጠይቀዋል፡፡
11👎2👍1
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራ በሚፈለገው ፍጥነት እየተሰራ መሆኑ ምልከታ ተደረገ።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራ በሚፈለገው ፍጥነት እየተሰራ መሆኑ እና ነዋሪው ወደ ቤቱ እንዲገባ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ ዛሬ ምልከታ ተደረገ።

በምልከታው በ40/60 እና በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበት  በአራብሳ ሳይት ሶስት  አምስት እና ስድስት  ፤  በበሻሌ እና  በአያት 2 ጨፌ ሳይት ያሉበትን የስራ እንቅስቃሴ ለማየት ተችሏል።

አቶ አብረሃም ታደሰ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባል  በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ቀንና ምሽት 7/24 እየሰሩ ያሉ ተቋራጮች ያሉበት አፈፃፀም ጥሩ ለውጥ ያለው መሆኑን በምልከታው ማየታቸውን ገልፀው ነገር ግን ሁሉም ጋር ተመሳሳይ ፍጥነት አለመኖሩን ተናግረዋል።

የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ማለትም የቤቶች ፣ የመንገዶች የውሀ እና የመብራት ስራ በየእለቱ እየቀረበ እንዲገመገም እና ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች በየቀኑ እንዲቀርቡ ኃላፊው አሳስበው በየቀኑ ለውጥ ያለው ስራ ለማየት የስራ ባህሉም 7/24 ሆኖ ይቀጥል ብለዋል።

በምልከታው የታዩ የበር ፣ የመስኮት፣ የሳኒተሪ ፣ የፍሳሽ ፣ የመንገድ እና ሌሎችም የሚጎሉ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ኃላፊው አሳስበዋል።

በጉብኝቱ አቶ አብረሀም ታደሰን ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከመንገድ ፣ ከውሀ ፣ ከመብራት የመጡ የመሰረተ ልማት ቅንጅት ተቋማት ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ።
5👏3👍1
በኢትዮጵያ ከሚያስፈልገው 20 ሚሊዮን የሲሚንቶ ምርት ዉስጥ እየቀረበ ያለዉ 7 ሚሊዮን ያህሉ ብቻ መሆኑ ተነገረ

በሀገሪቱ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት እየጨመረ ቢሄድም በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘዉ በአቅርቦት እጥረት ግን አሁን ችግር እየሆነ መምጣቱ ተሰምቷል።

በዚህም እንደ ሀገር የሚያስፈለገው 20 ሚሊዮን ቶን ሲሆን አሁን ላይ እየቀረበ የሚገኘው ግን 7 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ብቻ መሆኑን ያስታወቀው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር " ትልቁ ችግር የሆነዉ የአቅርቦት እና የፍላጎት ያለመጣጣም መሆኑን ጠቁሟል ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን የስራ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት እንደገለፀው ከሲሚንቶ አቅርቦት ስርጭት ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ችግር እንዲፈታ ማሳሰቢያ መስጠቱም ተሰምቷል።

Source: capitalethiopia
👏6👎32👍2
New Traffic Control Regulation 557-2016.pdf
64.5 MB
የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ 557/2024
👏11👎3👍1
The best yet to come 🙌
👎16👏114👍1
የመፅሀፋ ርእስ -ህይወቴ እና በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መሰረተ ልማት አውታሮች ዕድገት ትውስታዬ
ደራሲ- ዘርኦም ገ|ክርስቶስ(አርኪቴክት.)
የገፅ ብዛት - 247
የመፅሀፋ መገኛ - ዶ|ር ውብሸት ዥቅአለ ቢሮ (ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ፣አለሙ ወ|ፃዲቅ ህንፃ፣3ኛ ፍቆ ቢሮ ቁ 17)
የደራሲው ስልክ-0911113696
👏10👍1👎1🥰1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ።

የህ/ተ/ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ዛሬ በምክር ቤት የፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የሪል ስቴት አልሚ ድርጅት ያለደንበኛው ፍላጎትና ፈቃድ አጠቃላይ ግንባታው ቢያንስ 80 በመቶ ያልተጠናቀቀ ቤት ለደንበኞች ሊያስተላልፍ እንደማይችል አስቀምጧል።

በተጨማሪ በሪል ስቴት ልማት ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል #የውሸት_ማስታወቂያ ማስነገር እንደማይችልም አስቀምጧል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ትላንት ያያዝነውን ሙሉ ሰነዱን በዚህ ያገኙታል👇
https://t.me/tikvahethiopia/92613

@tikvahethiopia
😁83🥰3👎1🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ " ድሮና ዘንድሮ"
የቦሌ - መገናኛ የኮሪደር ልማት እውነታዎች
• መንገዱ የ68 ሜትር ስፋት ያለው ሰፊ መንገድ ነው
• በሁለቱም አቅጣጫ በአንዴ 10 መኪኖችን ማስተናገድ ይችላል
• 5 ሜትር የሚሆን በኮንክሪት የተሠራ የእግረኛ መንገድ አካቷል
• 3 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ ይዟል
• ለመንገዱ ውብት ከመጨመር ባሻገር በቴክኖሎጂ የተደገፈ ካሜራ፣ ስክሪኖችን እና የመኪና ቻርጅ ያሟላ ነው
• ለ450 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል
• አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 4 ነጥብ 3 ኪሎሜትር ይረዝማል
👎128👏5🥰2👍1