Construction Proxy
19.2K subscribers
525 photos
17 videos
74 files
282 links
#1 construction portal to get:
construction news
construction market
construction materials price
engineering estimates
Sub contract
https://constructionproxy.com
Address any comment to admin👨‍💼 @ConproxyBot
Download Telegram
40-60 Housing Name list.pdf
20.2 MB
የ40/60 ቤቶች በ2005 ዓ.ም ተመዝጋቢዎች ሙሉ ስም ዝርዝር ይመልከቱ።
ስሞትን መኖሩን ያረጋግጡ።የ40/60 ቤቶች በ2005 ዓ.ም ተመዝጋቢዎች ሙሉ ስም ዝርዝር ይመልከቱ።
ስሞትን መኖሩን ያረጋግጡ።
Not winners' list
20_80_ELIGIBLE_APPLICANTS Housing in Addis Ababa.xlsx
3.8 MB
#20_80_ተመዝጋቢዎች
የ20/80 ቤቶች #ብቁ #የ2005ዓ.ም ተመዝጋቢዎች ሙሉ ስም ዝርዝር ይመልከቱ።
ስሞትን መኖሩን ያረጋግጡ።
ይህ ማለት እጣው ውስጥ አሉ ማለት አይደለም ።
Hey Consultants!

Check out this list of all the registered consultants in Ethiopia! If you're not on the list yet, or your info needs an update, just shoot an email to constructionproxy@gmail.com (Heads up - full list is full visible on desktops but still you can use mobile too).
https://constructionproxy.com/consultants/
👏1
Typical Pavement Cross Section Design

- Carriageway & Shoulders:
- Main carriageway: 7,000 mm (3,500 mm each lane)
- Shoulders: 2,000 mm each side, 5% cross slope

- Pavement Layers:
- Surface:
- Shoulders: 6/10 surface dressing with pre-coated chippings
- Carriageway: 10/14 surface dressing with pre-coated chippings
- Asphalt: 50 mm Asphalt Concrete Type 1 (0/20)
- Base: 150 mm Cement Improved (Class A) GCS
- Sub-base: 175 mm Cement/Aima Improved Natural Gravel Sub-base
- Subgrade: 300 mm Improved subgrade (Class S3)

- Drainage:
- 1.5 m wide drain on one side

This cross-section ensures durability and efficient drainage, providing a reliable road structure.
👍1
የግንባታ ላይ አረንጓዴ ስፍራ ህግ።

በ100 ሜትር ካሬ ይዞታ ላይ 2 በ2 ሜትር ስፋት ያለው ከግንባታ ነጻ መሬት እንዲኖር የሚደነግገው ህግ ጽሁፍ ተያይዟል።
1
From Megenagn to CMC LRT line to be domlished.
Reportor
😱4
በአዲስ አበባ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ግምባታ “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናውን መሆኑ ተጠቆመ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምዕራፍ ሁለት የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በከተማዋ የፕላን እና ልማት ቢሮ አማካኝነት ጥናት አካሂዶ ማጠናቀቁ ተገለጸ።በአጠቃላይ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት፤ ቦሌ፣ ለሚ ኩራ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞችን እንደሚያካትት በጥናት ሰነዱ ላይ መመላከቱን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የኮሪደር ልማት” ሲል የጠራውን ዋና ዋና መንገዶችን የማስዋብ፣ የእግረኛ መንገድን የማስፋት፣ መዝናኛ ቦታዎችን የመገንባት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት እና ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስመሮችን በዘመናዊ መንገድ የመዘርጋት ሥራ የጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል።የከተማ አስተዳደሩ፤ በድምሩ 48 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍነው ለመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት፤ 33 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ ይታወቃል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በአምስት መስመሮች ላይ እንደሚከናወን የጠቆመው ዘገባው ከእነዚህ መስመሮች ውስጥ ከፍተኛ ዝርመት ያለው “ከአንበሳ ጋራዥ - መብራት ኃይል - ጎሮ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው መንገድ ሲሆን ይህ መስመር 14.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑ ተገልጿል።

“ከቦሌ ካርጎ - ቡልቡላ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው ሁለተኛው ረጅም መስመር ደግሞ 12.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መሆኑን ጠቁሞ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ የተካተተው ሌላኛው መስመር “ከቦሌ ድልድይ” ተነስቶ “በቦሌ ሆምስ - በአየር መንገድ ቪአይፒ መግቢያ” አድርጎ መዳረሻው “ጎሮ” አካባቢ መሆኑ ተጠቅሷል።

“ከጎሮ አደባባይ” የሚነሳው አራተኛው መስመር አምስት ኪሎ ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው በጥናት ሰነዱ ላይ የሰፈረ ሲሆን ይህ መስመር “ከጎሮ አደባባይ - በሰባ ሁለት አካባቢ - ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ አካባቢ - ፍየል ቤት - ሲ ኤም ሲ አደባባይ” አካባቢዎችን እንደሚሸፍን ዘገባው አመላክቷል።

“ከፍየል ቤት - ፊጋ - ሰሃሊተ ምህረት አደባባይ - ጃክሮስ” የሚደርሰው አምስተኛው መስመር ደግሞ 5.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መሆኑን አስታውቋል።

በከተማዋ የአስተዳደር ወሰን ማብቂያ አካባቢ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካተተው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ “በትግበራ ላይ ከሚገኙ የሸገር [ከተማ] ልማት ኮሪደሮች ጋር በማስተሳሰር የሚከናወን” እንደሆነ የጥናት ሰነዱ ማመላከቱን ዘገባው ጠቁሟል።
14👍1
ለ ነባርና አዲስ የኮንስትራክሽን (BC/GC) ፍቃድ ተመዝጋቢዎች


ከዚህ በላይ በሰፈረው አዲስ የተርን ኦቨር ባለሙያና  የኮንስትራክሽን መሳርያዎች መስፈርት መሰረት በማሟላት ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ::

ለእድሳትም ሆነ አዲስ ብቃት ማረጋገጫ ለማውጣት ሲመጡ ለሚፈልጉት ደረጃ ማንኛውም ማስረጃዎች ኦሪጅናላቸውን ከ2 ኮፒ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባችሁ

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል የምስክር ወረቀት/ላይሰንስ ሊኖረው ይገባል ካልሆነ ከተቆጣጣሪ ማሃንዲሱ ጋር በድርጅቱ ስራ አስኪያጅነት የተዋዋለበትን ማስረጃ ማቅረብ አለበት

ለስራ ዘመኑ ዓመታዊ ተርን ኦቨር የሚያሳይ ማስረጃ፤ የተሸከርካሪ ምርመራ (ዕድሳት)የተደረገለት መኪና ሊብሬ፤ ለስራ ዘመኑ የሚያገለግል (የታደሰ) የባለሙያ ፕሮፌሽናል ላይሰንስ፤ ህጋዊ የስራ ዉል፤ ቲን ነምበር(የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት)፤ የባለሙያው የትምህርት ዶክመንት፤ ባለሙያው ቀድሞ ሲሰራበት ከነበረው ድርጅት ስድስት ወር ያላለፈው የስራ መልቀቂያ፤ የቀበሌ መታወቂያ…) እና ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ

Via ሱራፌል አሸናፊ 👈👈
12
🤚ሰላም ቤተስቦች እንዴት ናቹ ተጨማሪ ሃሳቦች ለአማካሪዎች እና ለተቋራጮች ምዝገባ:-

በኮንስትራክሽን ቢሮ የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ለማግኘት ከሚመጡ ተገልጋዮች የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ ፅሁፍ ብ ፎቶ አያይዘንላቹዋል::
127👏4😁2👍1
➡️ በአዲስ አበባ በሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስምንት ኮሪደሮች
3
**ማስታወቂያ*
4👎2
Forwarded from Construction Resources
2017 1st QUARTER CONSTRUCTION WORKS ONLY DIRECT COST.pdf
22.3 MB
❇️ የ2017 የአንደኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት ይህን ይመስላል።
👏20👎21👍1
አዲሱ የይዞታ አስገዳጅ የ20 ሜትር የመንገድ አዋሳኝ ስፋት እና የአነስተኛው የ500 ካ.ሜ ስፋት የማይተገበርባቸው ቦታዎች
10👍1
ማህበራት መረጃ 2017 Latest.pdf
234.5 KB
**ማስታወቂያ ለማሕበራት*

❇️ ከ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በማህበር የተደራጅታችሁና በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ውስጥ በተለያየ የልማት ሥራዎች ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ ማህበራት ስማችሁ በቢሮው ይፋዊ የማሕበራዊ ሚዲያ ገፆች የተለቀቀ ሲሆን በዝርዝር ውስጥ የሌላችሁ ማህበራት 8 ኛ ፎቅ ምህንድስና ግዥ ዳይርክቶሬት ተገኝታችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 2 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲታደርጉ ያሳስባል ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

ጥቅምት 12/1017
👏121
አዲሱ_የቤት_ሽያጭ_ዋጋ_ተመን_አሰራር_እና_ታክስ_አገልግሎት_ክፍያ_ማንዋል_ቁጥር_01_2016_watermark.pdf
1017.2 KB
በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣

➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣

➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣

➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።
16🔥1😁1