Condominuim Market in Addis Ababa
Photo
በአዲስ አበባ በተከራዮች ላይ የኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ !
በአዲሰ አበባ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች ላይ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አስታወቀ ።
በአዲስ አበባ ለሁለት ዓመት ተጥሎ ሲተገበር የቆየው የኪራይ ውል ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ቀርቶታል።
ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቤቶች ላይ እጅግ ከፍተኛ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሁኔታ አስቀድሞ በኑሮ ውድነትና በዋጋ ግሽበት ክፉኛ እየተማረረ ለሚገኘው ማኅበረሰብ ተጨማሪ ከባድ ጫና ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ፥ " በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫናና በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በየቀኑ ሰማይ እየነካ የሄደው የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም በእጅጉ አዳክሞታል፤ ለዚህም መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል " ብሏል።
በተለይ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች እየተደረገ ነው ይህንንም አረጋግጫለሁ ሲል አሳውቋል።
የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን አቀዝቅዞታል፤ በተጨማሪም በነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ብሏል።
የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ ድርጅቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ጥናት ማድረጉንና ለኪራይ ንረቱ አሉታዊ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች መታዘቡን እንዲሁም ጭማሪም መደረጉን መመልከቱን ገልጸዋል።
አብዛኛው ተከራይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው በመሆኑ ካለው የኑሮ ውድነት ጋራ ተደምሮ በተለይ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ከኢኮኖሚና የተረጋጋ ማህበረሰብ ከመገንባት አንጻር አስተዋጽኦ ስላለው ልዩ ትኩረት ይሻል ማህበረሰቡ ላይ ምስቅልቅል እየፈጠረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በአከራዮች ላይ የተጣለው ከፍተኛ የታክስ መጠን፣ አከራዮች ይህንኑ ታክስ ወደ ተከራዩ እንዲያስተላልፉ እና ከውል ውጭ ተጨማሪ ክፍያ እንዲጠይቁ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለዚህም ከመንግስት መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።
ድርጅቱ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ፦
- የኑሮ ውድነቱን፣
-የዋጋ ግሽበቱን፣
- የነዳጅ ዋጋ ጭማሬውንና እጥረቱ በማዕቀፍ ለመፍታት እንዲያስችል ከዚህ በላይ የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
የቤት ኪራይ ውድነትን ለመከላከል ምን መፍትሄ አለ ?
ድርጅቱ፣ መንግስት በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት አቅም በፈቀደ መጠን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው የማድረግ የፖሊሲ ዓላማና ኃላፊነት አለበት ብሏል።
የመኖሪያ ቤት አቅርቦት መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ በመሆኑ አቅርቦቱን ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በከተሞች ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማኅበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ተመጣጣኝ እንዲሆን የማድረግ፣ የመቆጣጠርና የማስተዳደር ሕጋዊ ግዴታን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክቷል።
ይህ አስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የአከራዮችንና የተከራዮችን መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞች ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት ወሳኝ እንደሆነ ገልጿል።
ከተማ አስተዳደሩ ምን አለ ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ውሉ በመጪው ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የሚያበቃ መሆኑን ገልጿል። ይህን አስመልክቶ ጥናት እያስጠና መሆኑን ተናግሯል።
በጥናቱ መሰረት የኪራይ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል፣ አሊያም ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት የሚጨምር ወይም የሚቀንስ መሆኑን ለማህበረሰቡ ያሳውቃል።
ሸገር ኤፍ ኤም 102 .1
Condoaddis.etsecurities.com

❤2
Mechare condominium sale
48 sqm
2nd floor
1 bedroom
5.8 million
0913587955
https://bit.ly/4nL0s4x
@condoaddisbot
48 sqm
2nd floor
1 bedroom
5.8 million
0913587955
https://bit.ly/4nL0s4x
@condoaddisbot
❤3
የጋራ መኖርያ ቤቶችን በሚያስተዳድሩ ማህበራት ላይ አስገዳጅ የዲጂታል ክፍያ ስርዐት እየዘረጋ ያለው 'እፎይ ፕላስ' የተባለው የግል ድርጅት ውዝግብ አስነሳ
አሰራሩ አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ኮንዶሚኒየሞች እና አፓርትመንቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደ ሲሆን የጋራ መኖርያ ማህበራት ይህንን አሰራር ካልተቀበሉ የባንክ ሂሳባቸው እንደሚታገድ ክፍለ ከተሞች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ
https://bit.ly/4nL0s4x
አሰራሩ አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ኮንዶሚኒየሞች እና አፓርትመንቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደ ሲሆን የጋራ መኖርያ ማህበራት ይህንን አሰራር ካልተቀበሉ የባንክ ሂሳባቸው እንደሚታገድ ክፍለ ከተሞች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ
https://bit.ly/4nL0s4x
የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ የተራዘመ መሆኑን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ
ተቋማችን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን እና በካፒታል ፕሮጀክት የተገነቡ ንግድ ቤቶችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ 8ኛ ዙር እና 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በተመሳሳይ ቀን በአንድ የጨረታ ሰነድ ማውጣቱ እና የጨረታው 1ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሽያጭ ውል ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከሲስተም መቆራረጥ እና ተጫራቾች ካነሱት ከባንክ የገንዘብ ዝውውር መዘግየት አንፃር የባከኑ የስራ ቀናትን ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከግንቦት 25 እስከ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ ቀደም ሲል በተገለፀላችሁ የመዋዋያ ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ በኩል የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በተገለጸው የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈጸም እንድትችሉ ጥሪ የቀረበላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም