Condominuim Market in Addis Ababa
3.66K subscribers
2.33K photos
56 videos
10 files
987 links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@natang2
Download Telegram
Condominuim Market in Addis Ababa
Photo
አቶ ግሩም ይልማ በኪይ ሃውሲንግ ያቀረቧቸው ተከታታይ የማሻሻያ ጥያቄዎችና ስጋቶች ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው ከድርጅቱ ስራ አስፈፃሚነት መልቀቃቸውን አስታወቁ

አቶ ግሩም ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከኪ ሃዉስንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ስራ አስፈፃሚነት ስራ በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስመልክቶ ለሚዲያ ይፋዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

እኔ አቶ ግሩም ይልማ በኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን (Key Housing Finance Solution) ውስጥ በባለአክሲዮንነት እና በሥራ አመራር አባልነት ሲያገለገሉ መቆየታቸውን በመግለጫው ላይ አስታውሰዋል።

"ይሁን እንጂ ከየካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስወጣው የቆየሁትን የድርጅቱን የአስፈጻሚነት ወይም በኃላፊነት መጠሪያው የምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሚናን በፈቃዴ መልቀቄን ለሕዝብና ለባለድርሻ አካላት በይፋ አሳውቃለሁ።" ብለዋል አቶ ግሩም።

የቀድሞ የኪይ ሃውሲንግ ምክትል ስራ አስኪያጅ "ይህንን ውሳኔ ለመወሰን የተገደድኩት፣ በተቋሙ ውስጥ ሊኖሩ ስለሚገቡ የአሠራር ግልጽነት፣ የፋይናንስ ቁጥጥር እና የአባላትን ንብረት ስለመጠበቅ ያቀረብኳቸው ተከታታይ የማሻሻያ ጥያቄዎችና ያነሳኋቸው መሠረታዊ ስጋቶች ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው እንደሆነ ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ።" ብለዋል።

አቶ ግሩም ይልማ "የእኔ ትልቁ ኃላፊነት ድርጅቱን አምነው ጥሪታቸውን ላስያዙ ደንበኞች እና አባላት በመሆኑ ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽንን የመሰለ ተቋም ከፍተኛ የሞራል ልዕልና እና ሕግን ባከበረ ግልጽ አሠራር መመራት አለበት ብለው እንደሚያምኑ አመልክተዋል።

"በተለይም ከድርጅቱ ምስረታ አንስቶ እስከ ዕጣ ማውጣትና የቤት ቁልፍ እስከማስረከብ ድረስ በነበሩ ሂደቶች ሁሉ ከደንበኞች ጋር በአካል የመገናኘትና የድርጅቱን ዓላማ በስብሰባዎች የማስረዳት ዕድል በማግኘቴ የደንበኞች እምነትና ቅቡልነት መውሰድ ችያለሁ።" ሲሉም በመግለጫው ላይ ጠቅሰዋል።

አቶ ግሩም "ድርጅቱን በሚመለከት ባደረግኳቸው በሚዲያ የተላለፉም ሆነ ያልተላለፉ ንግግሮች ለደንበኞች ቃሌን እንደምጡብቅና የእነሱን መብት አደጋ ላይ በሚጥሉ ጉዳዮች ላይ እንደማልደራደር ስገልጽ ነበር።" ያሉ ሲሆን የድርጅቱ መሠረታዊ ግድፈቶች እንዲታረሙ ለበላይ አመራር ያቀረቡት ማሳሰቢያ ባለመተግበሩ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

"የመጨረሻ ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት፣ ተቋሙ ሊያርማቸው የሚገቡ መሠረታዊ ግድፈቶችን በዝርዝር በመጥቀስ ለቦርዱና ለማንጅመንቱ ማሳሰቢያዎች አቅርቤ ነበር" ያሉት አቶ ግሩም በተለይም በአባላት መዋጮ የተገኘ ንብረት ለድርጅቱ የብድር ዋስትና (Collateral) ተደርጎ እንዳይወሰድ በግልጽ በመቃወም፣ የአባላትን የባለቤትነት መብት ለማስከበር ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ግሩም ከሀላፊነቴ መልቀቅ የተገደድኩባቸው ምክንያቶች እኔ በሀላፊነት ላይ ባልኖርም ሊስተካከሉና እርምት ሊወሰድባቸው የሚገቡ ናቸው ሲሉም አሳስበዋል።

"ከሥራ አስፈጻሚነት ብለቅም እንኳን፣ እንደ ድርጅቱ ባለቤት (20% ባለአክሲዮን) የአባላትን መብትን ለማስከበር ሕግ የሰጠኝን መብት በሙሉ መጠቀም እቀጥላለሁ" ያሉት አቶ ግሩም የኪ ሃዉስንግ ፋይናንስ ሶሉሽን የውሳኔ ስልጣን በቦርድ ሰብሳቢው አቶ ናደው ጌታሁንና እና በዋና ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማ እጅ እንደሚገኝም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለኪ ሃዉስንግ መልካሙን በመመኘት ተስፋቸውን የገለጹት አቶ ግሩም  "እኔ ሁሌም ቢሆን የአባላቱ መብትና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ባለኝ አቋም ላይ እጸናለሁ።" ሲሉ መግለጫቸውን ቋጭተዋል።
2
Condominuim Market in Addis Ababa pinned «አቶ ግሩም ይልማ በኪይ ሃውሲንግ ያቀረቧቸው ተከታታይ የማሻሻያ ጥያቄዎችና ስጋቶች ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘታቸው ከድርጅቱ ስራ አስፈፃሚነት መልቀቃቸውን አስታወቁ አቶ ግሩም ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከኪ ሃዉስንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ስራ አስፈፃሚነት ስራ በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አስመልክቶ ለሚዲያ ይፋዊ መግለጫ ሰጥተዋል። እኔ አቶ ግሩም ይልማ በኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን (Key Housing…»
#ነዳጅ📈 በመጋቢት 2018 ዓ/ም
በነጭ ናፍጣ ብቻ በሊትር 10 የዋጋ ብር ጭማሪ ተደርጎ 139.84 ብር ገብቷል።

ቤንዚንም የ3 ብር ጭማሪ ተደርጎ በሊትር 132.18 ብር ሆኗል።

በደብዳቤው በተገለጸው መሰረት በሊትር፦
- ነጭ ናፍጣ 139.84 ብር
-​ ቤንዚን 132.18 ብር
-​ ኬሮሲን 146.14 ብር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 137.03 ብር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 133.45 ብር
-​ የአውሮፕላን ነዳጅ 145.23 ብር ሆኗል።

በዚህም ነጭ ናፍጣ ላይ የ10 ብር፣ ኬሮሲን ላይ የ7 ብር፣ ቤንዚን ላይ የ3 ብር፣ በመጋቢት ወር በሊትር ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ በየካቲት 2018 ዓ/ም ቤንዚን 129.12 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር፣ ኬሮሲን 129.12 ብር ይሸጡ ነበር።
ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች

የካቲት 27/2018 ዓ.ም

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጠዋል፡፡

እነኚህ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው
Geji taxi tera for sale
Floor 1
Two bed room
Price 11M
84sq
☎️0986014573
☎️0934981573
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ቦሌ : መድሃንያለም – 36,499,000
-
3 Beds | 4 Baths + 2 Kitchen + MaidsR + Laundry | ?F | 207 sqm
-
#ቤቱ
የሚገኘው ቦሌ መድሃንያለም ሰላም ሲቲ ሞል ጀርባ በሚገኝ የመኖሪያ ሰፈር ውስጥ B+G+8+T ሆኖ በተገነባ እና በወለል 2 ቤቶች ብቻ ባሉት የመኖሪያ ህንፃ ላይ ነው።

ህንፃው ለነዋሪው ሊፍት፣ ቴራስ፣ መኪና ማቆሚያ፣ እንግዳ መቀበያ፣ ቆሻሻ ማስወገጃ ሲስተም እና የህንፃ አስተዳደር በአገልግሎት ያቀርባል።

አሁን ላይ ሙሉለሙሉ ያለቀ እና አዲስ (ከ1.5 ዓመት በታች) ሲሆን ነዋሪዎች እየኖሩበት ይገኛል።

#Financial_Information
• Asking Price: 36,499,000 ብር
• Estimated Monthly Rent: 308,000 ብር ($2,000 @ 154)
• Rental Tax (50% method): 51,850 / month
• Property Tax: 1,681 / month
• Current Status: Vacant / Ready
• Net Monthly Income: 254,469 ብር
• Net Annual Income: 3,053,624 ብር

#Investment_Analysis
• Gross Yield: 10.1%
• Net Yield: 7.3%
• Payback Period: ~13.5 years

#Affordable_Price
• Based on rent (~308k): 30,000,000 – 34,000,000
→ Current price slightly above investment range (End-user + long-term hold)

#Replacement_Cost = 15,525,000 ብር

#Price_Position
• Price per sqm: ~176,000
• Compared to Bole Medhanialem Market: Mid–High Range

#Price_History
• Current Asking Price: 36,499,000
• Status: Active Listing

#ዶክመንት
ዲጅታል ካርታ አለው

#አከፋፈል
Cash | Bank (የገዢው አቅም ለባንኩ አቅርበን ፣ ከጠቅላላ ዋጋ ውስጥ እስከ 10M ብር የባንክ ብድር እናመቻቻለን።)

#STATUS
Active @ April 1

#Agent_Commission
70% of 4 ~ 1,022,000 birr (Net)

#Open_Time
የአንድ ሰአት የቀደመ ቀጠሮ ለጉብኝት ቀጠሮ ለመያዝ። 0913587955☎️
5🤣2
በከተማ አስተዳደሩ ቀጥተኛ በጀት በነሀሴ 2017 ዓ/ም በመዲናዋ በ18 ሳይቶች ውስጥ ከተጀመሩ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ውስጥ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ስር የሚገኝው ግዙፉ የቤት ልማት ግንባታ የሚከናወንበት የገላን ጉራ ሳይት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በልዮ ትኩረት ግንባታው በአዲስ እይታ በተለወጠ የስራ ባህል 7/24 በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን የግንባታ አፈፃፀሙ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ ።:

በመዲናዋ የተጀመሩ ግዙፉ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አማራጭ የቤት አቅርቦት መጨመር ላይ ትኩረት ባደረገ መልኩ በመንግስት ቀጥተኛ በጀት የሚገነቡ ቤቶች፣ በግሉ ሴክተርና በመንግስት ትብብር የሚገነቡ፣ ዜጎች በማህበር ተደራጅተው የሚገነቧቸው እና በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚገነቡ በአራት ዋና ዋና የቤት ልማት ማዕቀፎች በመለየት ግንባታው በስፋት እየተገነባ ይገኛል ።

በአሁን ሰዓት እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎች የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (A.A.S.T.U) አማካሪነት የቤቶቹ ጥራት ሳይቀንስ፣ የግንባታ ፍጥነትን በመጨመርና ዲዛይኖችን በማሻሻል ለመኖር ምቹ የሆኑ ቤቶች እየተገነቡ እንደሚገኝ ተገልጿል ::

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን