Condominuim Market in Addis Ababa
3.62K subscribers
2.34K photos
60 videos
10 files
1K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@antget1
Download Telegram
Condominuim Market in Addis Ababa pinned «https://youtu.be/W35EGMG_o00?si=qp9iNVNuYjISH4Kq»
ማስታወቂያ በ @condoaddis (Omni-Channel)

​በአዲስ አበባ የሪል ስቴት እና የኮንዶሚኒየም ገበያ ውስጥ ተሰሚነት ካላቸው ቀዳሚ የመረጃ መረቦች አንዱ በሆነው CondoAddis ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ!

ለምን በእኛ ያስተዋውቃሉ?
ሰፊ ተደራሽነት: በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን (Telegram, TikTok, YouTube, FB) ከ 42,000 በላይ ንቁ ተከታዮች።

ታማኝነት: በሪልስቴት እና በባንክና በፋይናንስ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚመራ።

ቀጥተኛ ደንበኞች: ቤት ለመግዛት፣ ለመሸጥ ወይም ለመከራየት የሚፈልጉ ባለሀብቶችን እና ዳያስፖራዎችን በቀጥታ ያገኛሉ።


የምናቀርባቸው አገልግሎቶች:
Telegram Blitz: በ 3.6k+ አባላት ባለው ቻናላችን የሚለጠፍ (Pinned options ይገኛሉ)።

Video Showcase: በ TikTok (16k) እና YouTube (13k) ለሚገኙ ተከታዮቻችን የሚቀርብ ምርጥ የቪዲዮ ማስታወቂያ።

Omni-Package: በአንድ ጊዜ በሁሉም ገጾቻችን የሚለቀቅ ሙሉ ማስታወቂያ።

Contact for Rates / ለዋጋ ዝርዝር በውስጥ መስመር ያነጋግሩን:
📩 @natang2
1
Real Estate vs Stocks in Ethiopia: Finding the Right Investment Path

Introduction: Ethiopia’s Investment Crossroads
Ethiopia is stepping into a new financial era. With the launch of the Ethiopian Securities Excxhange (ESX) and booming property development in Addis Ababa, investors now face more choices than ever.

For years, real estate was the go‑to option for protecting wealth. But today, stocks are emerging as a powerful alternative — offering flexibility, liquidity, and the chance to grow alongside Ethiopia’s economy.

So the big question is: Should you put your money into property or stocks?

1. Ethiopia’s Changing Investment Landscape

Read more👇👇
https://condoaddis.etsecurities.com/2026/04/14/real-estate-vs-stocks-in-ethiopia-finding-the-right-investment-path/
ለበለጠ መረጃ 👉💰💰💰💰
1
ስልክ ይህን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇
☎️☎️☎️☎️☎️☎️
የቤቱን ቪዲዮ ይመልከቱ
👇👇
https://youtube.com/shorts/wJvFhovonEI?si=Ujunq8yyJonWUnz5
1
Condominuim Market in Addis Ababa
Photo
በአዲስ አበባ በተከራዮች ላይ የኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ !

በአዲሰ አበባ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች ላይ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ ለሁለት ዓመት ተጥሎ ሲተገበር የቆየው የኪራይ ውል ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ቀርቶታል።

ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቤቶች ላይ እጅግ ከፍተኛ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሁኔታ አስቀድሞ በኑሮ ውድነትና በዋጋ ግሽበት ክፉኛ እየተማረረ ለሚገኘው ማኅበረሰብ ተጨማሪ ከባድ ጫና ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ፥ " በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫናና በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በየቀኑ ሰማይ እየነካ የሄደው የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም በእጅጉ አዳክሞታል፤ ለዚህም መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል " ብሏል።

በተለይ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች እየተደረገ ነው ይህንንም አረጋግጫለሁ ሲል አሳውቋል።

የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን አቀዝቅዞታል፤ በተጨማሪም በነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ብሏል።

የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ ድርጅቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ጥናት ማድረጉንና ለኪራይ ንረቱ አሉታዊ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች መታዘቡን እንዲሁም ጭማሪም መደረጉን መመልከቱን ገልጸዋል።

አብዛኛው ተከራይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው በመሆኑ ካለው የኑሮ ውድነት ጋራ ተደምሮ በተለይ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ከኢኮኖሚና የተረጋጋ ማህበረሰብ ከመገንባት አንጻር አስተዋጽኦ ስላለው ልዩ ትኩረት ይሻል ማህበረሰቡ ላይ ምስቅልቅል እየፈጠረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በአከራዮች ላይ የተጣለው ከፍተኛ የታክስ መጠን፣ አከራዮች ይህንኑ ታክስ ወደ ተከራዩ እንዲያስተላልፉ እና ከውል ውጭ ተጨማሪ ክፍያ እንዲጠይቁ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለዚህም ከመንግስት መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።

ድርጅቱ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ፦
- የኑሮ ውድነቱን፣
-የዋጋ ግሽበቱን፣
- የነዳጅ ዋጋ ጭማሬውንና እጥረቱ በማዕቀፍ ለመፍታት እንዲያስችል ከዚህ በላይ የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

የቤት ኪራይ ውድነትን ለመከላከል ምን መፍትሄ አለ ?

ድርጅቱ፣ መንግስት በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት አቅም በፈቀደ መጠን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው የማድረግ የፖሊሲ ዓላማና ኃላፊነት አለበት ብሏል።

የመኖሪያ ቤት አቅርቦት መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ በመሆኑ አቅርቦቱን ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በከተሞች ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማኅበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ተመጣጣኝ እንዲሆን የማድረግ፣ የመቆጣጠርና የማስተዳደር ሕጋዊ ግዴታን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክቷል።

ይህ አስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የአከራዮችንና የተከራዮችን መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞች ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት ወሳኝ እንደሆነ ገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ውሉ በመጪው ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የሚያበቃ መሆኑን ገልጿል። ይህን አስመልክቶ ጥናት እያስጠና መሆኑን ተናግሯል።

በጥናቱ መሰረት የኪራይ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል፣ አሊያም ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት የሚጨምር ወይም የሚቀንስ መሆኑን ለማህበረሰቡ ያሳውቃል።

ሸገር ኤፍ ኤም 102 .1
Condoaddis.etsecurities.com
1