Condominuim Market in Addis Ababa pinned «https://youtu.be/KG-bd-TN_SA?si=ZuU4GbO39vEb5cfk»
በአዲስ አበባ ከተማ “የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለንግድ ስራ አውለዋል” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በሶስት ቀናት ገደብ ውስጥ እስከ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ነዋሪዎቹ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለሌላ አገልግሎት ለማዋል የሚያስችላቸውን የሊዝ ውል ለውጥ ለማድረግ ከመቶ ሺህዎች እስከ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ክፍያ መጠየቃቸውንም ገልጸዋል።
በመዲናይቱ በሚገኙት በአቃቂ ቃሊቲ፣ በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ ባለፉት ቀናት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች እንደደረሷቸው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጣለች። በአንዳንዶቹ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የንግድ ቤቶች እና አገልግሎት መስጪያዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች መለጠፋቸውንም የየአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ዓለም ባንክ አዲሱ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ ከክፍለ ከተማ መምጣታቸውን የገለጹ ሰራተኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤውን ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ፤ ነዋሪዎቹ መሬት የወሰዱት ለመኖሪያ አገልግሎት ለመዋል እንደሆነ ይጠቅሳል።
ሆኖም ነዋሪዎቹ “በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ለተፈቀደላቸው አገልግሎት ብቻ እየተጠቀሙ አለመሆኑን” በመስክ ክትትል ማረጋገጥ መቻሉን ያትታል። ነዋሪዎቹ ማስጠንቀቂያው ከተሰጠበት አሊያም ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ፤ ካርታቸውን፣ የሊዝ ውላቸውን፣ ለመጨረሻ ጊዜ የከፈሉበትን የሊዝ ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም የንግድ ፍቃዳቸውን በመያዝ ለክፍለ ከተማ እንዲያቀርቡም ቀነ ገደብ ያስቀምጣል።
🔴 ዝርዝር ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16343/

❤4
ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች ዝርዝር.pdf
1.7 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ በጉለሌ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
#ለማስታወስ፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300 በlandleasedocument.aalb.gov.et:(https://www.lndleasedocument.aalb.gov.et) በመግባት በኦን ላይን በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
ሰነዱ ከላይ ተያይዟል ።

❤1👏1