Condominuim Market in Addis Ababa
3.62K subscribers
2.34K photos
60 videos
10 files
1K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@antget1
Download Telegram
ውድ የ2005 20/80 እና 40/60 ኮንደሚንየም ተመዝጋቢዎች
በ17/7/17 ዓ.ም. በነበረን ውይይት በቅርቡ የቅሬታ እና ውክልና ፊርማ ማሰባሰብ እንደሚኖር መግለፃችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ባገኘናቸው ፈቃደኛ የፊርማ አሰባሳቢ አባላት ከነገ ሃሙስ 25/07/17 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ ቦታዎች የፊርማ ማሰባሰብ ስለሚካሄድ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኙ አባላት በመሄድ እንድትፈርሙ እያሳሰብን፤ ፊርማ አሰባሳቢዎቹ በፈቃደኝነትና ካላቸው የስራ ጊዜ ላይ ቀንሰው የሚያገለግሉን በመሆናቸው ፊርማ ለማሰባሰብ ካስቀመጡት ሰዓት ውጪ ስልካቸው ላይ ባለመደወል የተለመደ ትብብራችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን፡፡
የ2005 20/80 እና 40/60 ኮንደሚንየም ተመዝጋቢዎች አስተባባሪ ጊዜያዊ ኮሚቴ

1. ሙሉቀን ገ/ወልድ---ሃይሌ ጋርመንትና አካባቢው ያላችሁ-0911300823- ቅዳሜና እሁድ 8:11:00
2.  ማርታ መርሻ-ከቤተል እስከ አለም ባንክ--- 0911923638-
3.  መስፍን ፍቅሬ --ጊዮርጊስ መቅደላ ሆቴል-0911389229- ቅዳሜ፣ሰኞና አርብ 8-11፡00
4.  ቤተልሄም ----- አያት 72(ለሚ ኩራ)----0946699786- ከአርብ- ቅዳሜ 7:30-10:30
5.  ኤደን እቁባይ -- ስድስት ኪሎ ሊደርሺፕ ህንፃ -0955328676-ሀሙስ-ቅዳሜ 9-11፡30
6.  እስራኤል ዋለልኝ ---አቃቂ ቃሊቲ ገበያው ውስጥ--0911669146- ከአርብ-ቅዳሜ በማንኛውም ሰዓት
7.  ወይንሸት ታደሰ -ገርጂና አካባቢው ላይ ያላችሁ- ቅዳሜ እና እሁድ ከ8፡-11፡00  0913126992
8.  ጥሩወርቅ ባስረሳው----(ሳሪስ-ጎተራ አካባቢ )-ሳሪስ ነጋ ቦንገር-0911186160-ቅዳሜና እሁድ
9.  ገረመው ታዬ----ሲኤምሲ ሚካኤል-0913549854- ቅዳሜና እሁድ-3-6፡00
10.  ፍሬህይወት ጌታቸው--ቦሌ ሻላ መናፈሻ---0911449026- ቅዳሜና እሁድ ከ9-11:30 ሰዓት
11.  ጌታመሳይ ኃ/ጊዮርጊስ- መርካቶንጋት ብርሃን ህንፃ-0902358337- ከሰኞ-ረቡዕና ቅዳሜ 4፡00-6፡00
12.  ገዛኸኝ ንጉሴ---ኩዬና ቃሊቲ አካባቢ ---0911089151- ቅዳሜና እሁድ

ለተጨማሪ መረጃዎች ሊንኩን ይጫኑ! የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ🙏
https://t.me//condoaddis
👍6
#ኮድ_1839
በላፍቶ በምርጥ የኮንዶሚኒየም ሳይት የሚገኝ ለሽያጭ የቀረበ ባለ1 መኝታ
💦51ካሬ
💦3ኛ ፍሎር
💦ፅድት ያለ ሙሉ ሴራሚክ..
💦ጂፕሰም ፍሬም የተሰራ
💦ቁምሳጥንና ኪችን ካቢኔት ያለው
💦ዲጂታል ካርታ የያዘ ስም የሚዞር
💦ለመኖሪያ ምቹ በሆነ ቦታ ላይ ይገኛል
👉👉.የመሸጫ ዋጋ 4.4 ሚሊየን ብር
☎️... +251920039447
👍2
የአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ ጨረታ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ሆነ
168 ተወዳዳሪዎች ከውድድር ውጪ ሆነዋል


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአምስት ክፍለ ከተሞች (የካ፣ ጉለሌ፣ ለሚ ኩራ፣ አራዳ እና ቂርቆስ) ያዘጋጀው የመሬት ሊዝ ጨረታ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ ሆኗል።


ቢሮው የህብረተሰቡን የመሬት ፍላጎት ለማሟላት በየሶስት ወሩ የመሬት ሊዝ ጨረታ እያወጣ ሲሆን፣ በአምስተኛው ዙር ጨረታ ላይ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች ለተዘጋጁ 427 ፕሎቶች ውድድር አቅርቧል።


በዚህም መሰረት 86 ፕሎቶች በአምስቱ ክፍለ ከተሞች ለጨረታ ቀርበው ነበር።


በጨረታው ሂደት 168 ተጫራቾች አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው ባለማቅረባቸው ከውድድር ውጪ ሆነዋል። በተጨማሪም 10 ቦታዎች በቂ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት መሰረዛቸውን ቢሮዉ አስታውቋል ።

T.me/condoaddis
ቃሊቲ ገብሬል 40/60 ኮንደሚኒየም ሽያጭ

❇️ ባለ3 መኝታ 156 ካሬ

❇️ ሙሉ ዕድሳት ያለቀለት

❇️ 4ኛ ወለል ላይ

❇️ ለትርፍ የሚሆን

❇️ ሁለት መፀዳጃ ቤት ያለው

❇️ ሊፍት የተገጠመለት

❇️ ዋጋ 12,500,000

📲 0913432274
📲 0938274717
👍2
በአዲስ አበባ ለጨረታ ለቀረቡ ቦታዎች በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር መሰጠቱ ታወቀ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ ለጨረታ ካቀረባቸው 427 ቦታዎች ውስጥ፣ የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር መሆኑና ቦታውም ካዛንቺ እንደሆነ ታወቀ፡፡

የመሬትና ልማት አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአምስተኛ ዙር እየተካሄደ በሚገኘው የመሬት ሊዝ ጨረታ 18 ሔክታር መሬት ቀርቧል፡፡

በሊዝ ለማጫረት ከቀረቡ ቦታዎች ውስጥ ካዛንቺስ የሚገኝ አንድ ቦታን በካሬ ሜትር 265 ሺሕ ብር ለመግዛት ከተጫራች ዋጋ መቅረቡን፣ እስካሁን በአምስት ክፍላተ ከተሞች በተደረገው የጨረታ ሒደት 76 ተጫራቾች በጊዜያዊነት ጨረታውን ማሸነፍ መቻላቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

ለጨረታው የቀረቡ ቦታዎች የሚገኙት በዘጠኝ ክፍላተ ከተሞች እንደሆኑ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በአጠቃላይ የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የተጫረቱት ብዛት 6,885 ተጫራቾች  እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

#
👍81
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። አጀንዳዎቹም ፦

1ኛ. ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።

2ኛ. የብርሃን አይሰውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ት/ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን  የቀረበዉን  ደንብ መርምሮ አጽድቋል ::

3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ አጽድቋል::
👍1
👍32🥰2
የቤቶች ቀውስ እየተባባሰ በመምጣቱ ብሔራዊ የቤቶች ባንክ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ጥሪ ቀረበ

በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የቤቶች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የሕግ አውጪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች በአስቸኳይ ብሔራዊ የቤቶች ባንክ እንዲቋቋምና ሥራ እንዲጀምር አሳሰቡ።

ይህ የታቀደው ተቋም በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች ለማግኘት ዘላቂ የፋይናንስ መፍትሔ ለመስጠት ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ2037 የኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር ከ42 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ለአዳዲስ ቤቶች ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ቤቶች እጥረት ያለ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃም በየዓመቱ የሚገነቡት ቤቶች ከሚያስፈልገው እጅግ አነስተኛ ነው።

ይህ ከፍተኛ የቤቶች እጥረት በተለይም በከተማ አካባቢዎች የሕገ-ወጥ ሰፈራዎች እንዲስፋፉና የኑሮ ደረጃ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል።

የፓርላማው የከተማ፣ የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሌሎች አገሮች እንደሚታየው የልማት ባንኮች ዓይነት የሆነ የወሰነ የቤቶች ባንክ የቤት ግንባታ የረጅም ጊዜና አነስተኛ የወለድ ምጣኔ ብድር በመስጠት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሸቱ ተመስገን እንዳሉት እንዲህ ዓይነት ተቋም ሳይቋቋም ከቀረ ለቤቶች እጥረት ዘላቂና ውጤታማ መፍትሔ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርም ይህንን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ ወደ ትግበራ እንዲገባ አሳስበዋል።

Read More

Source: capitalethiopia
@Condoaddis
2👍2
በአዲስ አበባ ለጨረታ የቀረቡት 1,735 የንግድ ቤቶች የት ነው የሚገኙት ?

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀዉ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1,735 የንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ ማሳወቁ ይታወሳል።

ኮርፖሬሽኑ የንግድ ቤቶቹ የሚገኙባቸውን ክ/ከተሞች ፣ ቤቶቹ የሚገኙባቸውን ሳይቶች እና የቤቶቹን ብዛት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በተለይም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገኙ ቤቶች ሲሆኑ በሻሌ ሳይት ላይ 622 ቤቶች፣ አያት ሁለት 309 ቤቶች ፣ አያት ሁለት ሳይት አራት 176 ቤቶች እንዲሁም አያት አንድ ሳይት ሶስት 140 ቤቶች ለጨረታ ከወጡት ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ።
1👍1