Condominuim Market in Addis Ababa
3.62K subscribers
2.34K photos
60 videos
10 files
1K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@natang2
Download Telegram
Forwarded from House market in Addis (G Y)
የሚሸጥ ቤት ምርጥ ቦታ
ሳሪስ አደይ አበባ ሳይደርስ
ሙለጌ ሕንፃ ጀርባ

የቦታው ስፋት 250 ካሬ

ዋና ቤትና ሰርቪስ ክፍሎች ያለው
የሚከራይ መጋዘን አለው

ዋጋ 55 ሚልየን
ይደውሉ 0913587955
3
#ቅሬታ #ምላሽ

“ ... ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኞች ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ የባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው ” - የኪ ሃውሲንግ የቤት ዕጣ ቆጠቢ

“ ... ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ጽፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ” - አቶ ቸርነት መንግስቱ (ከድርጅቱ)

ከሰሞኑን  " Key Housing Finance Solution " የተሰኘ ተቋም የቤት ባለቤት ለመሆን ሲቆጥቡ ለነበሩ ሰዎች ዕጣ አውጥቶ ነበር።

ከተለያዩ ሴክተሮች በሚገኙ ልምድ ባላቸው አካላት ተዋቅሯል የተባለው " Key Housing Finance Solution " ከ15,000 በላይ ለሆኑ የቤት ቆጣቢ ተመዝጋቢዎች መካከል ለ60 ቆጣቢዎች / የቤት ዕድለኞች የመጀመሪያ ዙር ዕጣ አውጥቶላቸዋል።

ድርጅቱ በ77,280 ብር ቅድመ ቁጠባ ሰዎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሞዴል ፕሮጀክት እንዳለው በገለጸው እና በተለያዩ መንገዶች ባስተዋወቀው መሰረት ነው ከ15,000 በላይ ቤት ፈላጊ ቆጣቢዎች ውስጥ #ለ60_ቆጣቢዎች / #ባለዕድለኞች ዕጣ ያወጣላቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ “Key housing Finanance Solution” የቤት ዕጣ ቆጣቢ፣ “ኪ ሃውሲንግን በተመለከተ እጣ አወጣጡ ላይ ስህተቶች የተሰሩ በመሆኑ ማብራሪያና እርማት ብንጠይቅም በሶሻል ሚድያም ሆነ በሌላ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም” የሚል ቅሬታ ደርሶታል።

ከተመዝጋቢዎቹ መካከል አንዷ በሰጡን ቃል፣ “ ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ ለዚሁም ብለን  ' አትላስ ' በሚገኘው ዋና ቢሯቸው ማብራሪያ ለማግኘት ከአንዴም ሁለቴ ብንሄድም #በsystem ምክንያት ዕጣ አወጣጡ ላይ ችግር ያለበት መሆኑን ከማመን የዘለለ በቂ ምላሽ አልሰጡንም ” ሲሉ ድርጅቱን ወቅሰዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረቡ ቅሬታዎች በዝርዝር ምን ይላሉ ?

- ዕጣው የደረሳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ካደረጉ በኋላ ቼክ በምናደርግበት ጊዜ ልዩነት አለው። 

- ልዩነት የተፈጠረው ባለ 3 ፣ ባለ 2 እና ባለ 1 መኝታ ቤት ነው ያዘጋጁት። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ካለው ዝርዝር ጋር ስናስተያየው ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብኞቹ ባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው።

- ከተመዝጋቢዎች ብዛት አንፃር #ባለ_3_መኝታ_ቤት ለ30 ሰዎች (50%)፣ ባለ 2 መኝታ ቤት ለ21 ሰዎች (35%)፣ ባለ 1 መኝታ ቤት ለዘጠኝ ሰዎች (15%) እንደሚወጣ ነበር ዕጣውን ከማውጣታቸው በፊት ሲገልጹ የነበረው።

- ባለ 3 መኝታ #ለ30_ሰዎች ብለው ካሰቡት ውስጥ ለ21 ሰዎች ነው የወጣው። የባለ 2 ደግሞ ለ21 ሰዎች ብለው ከገለጹት ለ29 ሰዎች ነው የወጣው። ባለ 1 መኝታ ቤት ደግሞ ለ9 ሰዎች ብለው ካሰቡት ለ10 ሰዎች ነው የወጣው። ይህ ማለት ይፋ ካደረጉት ፐርሰንቴጂ ጋር ግልፅ የሆነ ልዩነት አለው።

- በተጨማሪም ፤ ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የታቀደው ፕላን በፐርሰት 50 በመቶ ባለ 3 መኝታ ቤት ፣ 35 በመቶ ባለ 2 መኝታ ቤት እንዲሁም ፣ 15 በመቶ ለባለ 1 መኝታ ቤት ብለው ነበር ያስቀመጡት። አክቹአል ሲወጣ ግን ወደ 35፣ 48፣ እና 17 ፐርሰቶች ተቀያይሯል።

- ከ15,000 በላይ ተመዝጋቢዎች 60 እደለኞች ብቻ መመረጣቸው ሳያንስ ይኸውም የ60 ሰዎች ዕጣ አወጣጥ ትክክል ያልሆነና ተዓማኒነት የጎደለው ነው።

- ሌላ ያስተዋልው የተመዝጋቢዎች ስም ዝርዝር ተብሎ የተመዘገበው ላይ እስከ አያት ድረስ በተመሳሳይ ደብል የሆኑ ስሞች አሉ” የሚሉ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፤ የተነሳውን #ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የብሉዞን ማርኬቲንግ ማናጀርና የኪ ሃውሲነሰግ ቦርድ ሜምበር አቶ ቸርነት መንግስቴን አነጋግሯቸዋል።

እሳቸው ምን አሉ ?

ወደ ሲስተም ሲሞላ የታይኘ ኢረር ይኖረዋል። ባለ 2 የተመዘገበን ሰው ባለ 1 ብለህ ልትጽፍ ትችላለህ፣ ባለ 1 የተመዘገበን ባለ 3 ትላለህ። 

ይኼ ከሆነ ምናልባት ደንበኛው ራሱ ደግሞ ዕጣ ውስጥ ' መካተት ፤ አለመካተቱን ' እንዲያረጋግጥ ፣ እንዲህ አይነት የታይፕ ስህተቶች ተፈጥረው ከሆነ ታይቶ እንዲነገረን ፖስት አድርገንላቸዋል። 

በቴሌግራም ላይ ፖስት ካደረግን በኋላ ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ፅፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ። እሱን ከውሉ ጋር ወዲያው ከሀርድ ኮፒው እናመሳክራለን። ሲስተሙ ላይ ይስተካከልላቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ሲስተም ነው። መሞከሪያም ነው መስተካከል አለበት።

ፓስት ያደረግነው ቁጥር ሁሉም ማለት አይደለም የተወሰኑ ሰዎች ‘እንዲህ አስተካክሉልን’ ብለውናል። አስተካክለንላቸዋል። ‘አስተካክሉልን’ ያሉን ሰዎች ከተስተካከለላቸው በኋላ በቀጥታ ሰነዱን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ያስረክብነው የተስተካከለውን። 

ቴሌግራም ላይ ፖስት የተደረገው ያልተስተካከለው የመጀመሪያው (አስተያዬት ለመሰብሰብ ፓስት የተደረገው) ነው። ዕጣ ከወጣ በኋላ ሰዎች ሂደው ሲያመሳክሩ ያን ያዩታል። ግን እነዛ ሰዎች እዚጋ እንዲስተካከልላቸው ሆኗል። ራሳቸው ባቀረቡት መሠረት ማለት ነው።

እንዲህ ካደረጋችሁ ፥ በተመዝጋቢዎች በኩል ብዥታ እንዳይፈጠር ለምን የተስተካከለውን በድጋሚ ፖስት አላደረጋችሁላቸውም ? ብሎ ቲክቫህ ጠይቋቸዋል።

ምላሻቸውም ፤ " ካለፈ በኋላ ፓስት ማድረግ እንችል ነበረ " ብለዋል።

ዕጣው ከመውጣቱ በፊት #የተስተካከለውን ሰነድ ፓስት ያላደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ፤ " የተጣራው ለአዲስ አበባ የምንሰጠው ሰነድ ነው። የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ Soft ware ከሰራበት በኋላ ነው እንጂ ኦዲት የምናደርገው ቀድመን ምን ይደረግ የሚለውን አናውቅም። ዜሮ፣ ዜሮ መሆኑን ብቻ ነው የምናየው " ሲሉ ተናግርዋል።

በተጨማሪ ...

ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው ዕጣ የወጣላቸው ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ፤ ተብሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ይህ #እውነት_አይደለም። ምክንያቱም ባለ 2 ተመዝግበው ባለ 3 እንዴት ይደርሳቸዋል ? የደረሰውስ እንዴት ይቀበላል ? የማይሆን ነገር ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ዕጣ ከማውጣቱ በፊት ለባለ 3 ፣ ለባለ 2 እንዲሁም ለባለ 1 የቤት ዕድለኞች ያቀዱት ፐርሰንቴጂ ዕጣው ከወጣ በኋላ ተቀያይሯል ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ቤቱን ገና አላስተላለፍንላቸውም። ገና በ18 ነው ቤቱን የሚረከቡት።

የሚረከቡትም በተባለው መሠረት ባለ 1 መኝታ ቤት ዘጠኝ ሰዎች፣ ባለ 2 መኝታ ቤት 21 ሰዎች፣ ባለ 3 መኝታ ቤት 30 ሰዎች ናቸው። ባልተዘጋጁ ቤቶች ዕጣ አናወጣም። ከየትስ እናመጣዋለን "  ከሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ድርጅቱ ማብራሪያ ሊሰጥ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ ፦

° “ ተወካይ ነን ብለው ለመጡ አባላቶች (የምር ተወካይ አይደሉም፤ የተወካይ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም) ፤ ግን ነገሩ መልካም ስለሆነ ቢሮ ለእያንዳዱ ሰነድ ጭምር እያሳዬን ማብራሪያ ሰጥተናል ” ሲሉ መልሰዋል።

በተመሳሳይ ስም የተጠቀሱ " ዳብል " ተመዝጋቢዎች መኖራቸው ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ ፦

° " ... እንድ ተመዝጋቢ #ለብዙ_ሰዎች መመዝገብ ይችላል፣ ኮዱም ቢሆን ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል "  ሲሉ መልሰዋል።

በአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ።
👍6
በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ።

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዳስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ ጥር 21 /2016 ዓ.ም ጀምሮ  የመሬት አገልግሎቶች በጊዜያዊነት መታገዳቸውን የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

@condoaddis
👍7
የሚሸጥ ቤት ጀሞ 3
👉ባለ ሶስት መኝታ ክፍል
👉103 ካሬ ስፋት
👉4ኛ ፎቅ ላይ
👉ዋጋ 6,500,000 ገዥ ከሆኑ ፈጥነው ይደውሉልን ድርድር አለው
ጥሩ location

0913587955
Visit our website
1👍1
የሚሸጥ ቤት አትክልት ተራ ጊዮርጊስ

ባለ 2 መኝታ
68 ካሬ
3ኛ ፎቅ ላይ

ዋጋ 8 million
ይደውሉ 0913587955
Condoaddis.com
👍41
ለሽያጭ የቀረቡ ኮንዶሚንየም ቤቶች

ያማርጡ ይግዙ


ስቱዲዮ 👉 Studio option

ባለ 1 መኝታ 👉 1 bedroom

ባለ 2 መኝታ 👉 2 bedroom

ባለ 3 መኝታ 👉 3 bedroom
1
ለሽያጭ የቀረቡ ኮንዶሚንየም ቤቶች

ያማርጡ ይግዙ


ስቱዲዮ 👉 Studio option

ባለ 1 መኝታ 👉 1 bedroom

ባለ 2 መኝታ 👉 2 bedroom

ባለ 3 መኝታ 👉 3 bedroom
👍21
Gotera Mamo condominium

Bedroom:- 1
37 sqm
Ground floor
Price:- 7 million birr

Call us 0913587955
More on condoaddis.com
👍2
Condominuim Market in Addis Ababa pinned «https://www.youtube.com/watch?v=0W_Lm0JLJS4»
IMG_20240209_122012_101.jpg
20.5 KB
የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነሳ

የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው መነሳቱን ክብርት ፅጌወይን ካሳ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ ያሳወቁ ሲሆን ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ከቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በዚህ ሳምንት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።
Condoaddis.com
👍6
#እንድታውቁት
(የካቲት 1,2016 ጀምሮ)

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ የካቲት 1 ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ #ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

👉 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) #አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።

ቅዳሜ ደግሞ ግማሽ ቀን ነበር የሚሰራው።

ከዛሬ በኃላ በአ/አ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋት 2:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ በሁሉም ቅርንጫፍ ከጥዋት እስከ 11:30 አገልግሎት ይሰጣል።

👇 Read more
condoaddis.com/100224
👍4
Condominuim Market in Addis Ababa pinned «https://www.youtube.com/watch?v=Mxbwg8RRmts»