Condominuim Market in Addis Ababa
3.62K subscribers
2.34K photos
60 videos
10 files
1K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@antget1
Download Telegram
🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕
Condominium for sale at
Birechiko Meckeyililand
Price Br. 1,800,000
Area:- 64 m2 Bedroom:-3
Floor:- 4th
ሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚንየም ባለ2 ወይም ባለ 3 ወይም ባለ 4 መኝታ ያለው መሸጥ የሚፈልግ? ገዢ ስላለ በ0913587955 ይደውሉ።
ምርጥ የሚሸጥ ሙሉ ግቡ ቪላ ቤት ኮተቤ
ወንድይራድ ት/ቤት ጀርባ
ዋጋ ብር 4,800,000 ከድርድር ጋር
ስፋት 200 ካሬ ሜ.
ዋና ቤትና ሶስት መኝታ ቤቶች
በተጨማሪም ሰርቪስ ቤቶች ያሉት
ይደውሉ 0913587955
Channel name was changed to «Condominuim Sale & Buy Addis Ababa»
አዲስ አበባ:- 18 ሺህ 576 የ40/60 የቤት ዕድለኞች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ውል አስረው የአስር ወራት ክፍያ ቢፈፅሙም እስከ አሁን ቤታቸውን የአስረከባቸው አካል እንደሌለና ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ተናገሩ።

ቅሬታ አቅራቢ የሁለተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለዕድለኞችም ከነሐሴ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ውል በመግባት ወርሐዊ ክፍያ መጀመራቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ ለአስር ወራት ክፍያ ቢፈፅሙም እስካሁን የከተማ አስተዳደሩ ቤታቸውን እንዳለስረከባቸው ጠቅሰው ይህም በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ የይኢኮኖሚ ጫና እያደረሰባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

በሃያት ሁለት ባለሁለት መኝታ ቤት የደረሳት ወይዘሪት ሰላማዊት ውቤ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገረችው፤ ባለፈው ነሐሴ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውል በመግባት የአርባ በመቶ ክፍያውን ከመስሪያ ቤቷ የቁጠባ ተቋም ብድር በመውሰድ በየወሩ 3 ሺህ 173 ብር ትከፍላለች። በተጨማሪም የቤቱን ዕዳ በመክፈል ኑሮዋን ከዘመድ ጋር በጥገኝነት አድርጋ ለተደራራቢ ወጪ መዳረጓን ገልፃለች። ይህም በኑሮዋ ላይ ጫና እንደፈጠረባት መሆኑን ተናግራለች።

አስተዳደሩ የቤቱን ግንባታ ሳይጠናቀቅ ውል በማስገባት ክፍያ እንዲፈጽሙ ማስገደዱን የምታነሳው ወይዘሪት ሰላማዊት፤ ቤቱን ሳያስረክብ ወለድ ማስከፈል ተገቢ እንዳልሆነ ገልፃለች። በዚያ ላይ ውል ከተገባው እስከ ሁለት እጥፍ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉና የእፎይታ ጊዜም አለመኖሩ ለባለድለኞች አስቸጋሪ ሆኗል ትላለች። ከምንም በላይ ግን እየተቸገረችበት ያለው የከተማ አስተዳደሩ ቤት ሳያስረክብ ወርሃዊ ክፍያ ማስከፈሉ ሲሆን፤ መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን ችግራቸውን ሊፈታላቸው እንደሚገባ አበክራ ትናገራለች።

በቱሪስት መገናኛ የባለሁለት መኝታ ባለዕድለኛው አቶ አዳነ አወቀ በበኩላቸው፤ ውል ከገቡ በኋላ ለደረሳቸው ቤት በየወሩ 3 ሺህ 500 እንዲሁም ለመኖሪያቸው ቤት ኪራይ 4 ሺህ 500 ብር እየከፈሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የአራት ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናቸውም የተናገሩት አቶ አዳነ አወቀ ቤቱን ሳይረከቡ እንዲከፍሉ መደረጋቸው ከፍተኛ ጫና እንደሆነባቸው አስረድተዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ዕጣ ሲወጣ ግድግዳቸው ያልተከፈሉ ቤቶች መኖራቸውን ያነሱት አቶ አዳነ፤ መሰረተ ልማቱና የቤቶቹ ሥራ ሳይጠናቀቅ ውል አስገብቶ ገንዘብ ማስከፍል ከሞራልም ከህጋዊነትም አንፃር አግባብነት የሌለውም ይላሉ።

በአስኮ ሳይት የቤት እድለኛው ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ አቶ እስጢፋኖስ ዘኪሮስ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ ባለተረከቡት ቤት በየወሩ 2 ሺህ 973 ብር እየከፈሉ መሆኑን ተናግረዋል። ቤቱ የግድግዳ ግርፍ፣ መፀዳጃ ቤት፣ የመሠረተ ልማት፣ የበርንዳና ሌሎች ሥራዎቹ ያልተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀው የከተማ አስተዳደሩ ዕጣ ማውጣትና ቤቱ ሳይጠናቀቅ ውል ማሰሩ ተገቢ አለመሆኑን አመልክተዋል። ይህም የቤት እድለኞችን ከዕቅዳቸው ውጭ በኢኮኖሚ ጫና እንዲጎዱ አድርጓል። በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ቤቱን በፍጥነት አጥናቆ ማስርከብ አለበት ብለዋል።

በመገናኛ ቱሪስት ባለሁለት መኝታ እድለኛው አቶ ማለደ ዋሲሁን በበኩላቸው፤ የ40/60 የቤት ፕሮግራም ከግንባታ እስከ ዕጣ አወጣጡ አወዛጋቢ መሆኑን አንስተው መንግሥት በቃሉ መሠረት ቤቶቹን ሠርቶ ማስረከብ አልቻለም ይላሉ።

ከግንባታው ማዕቀፍ ውጭ መንግሥት ባለአራት መኝታ ግንብቶ አስረክቧል። የቤቱ ስፋት ካሬውም በተመሳሳይ ደረጃ የተለያየ ነው። ዕጣውን ለመውጣት የክፍያ መጠኑ አወዛጋቢ ነበር። ዕጣው ወጥቶ ውል ከታሰረም በኋላ ለአስር ወራት አስተዳደሩ ቤት ሳያስረክብ ገንዘብ በመሰብሰብ ዜጎችንም ችግር ላይ ጥሏል። ይህ ደግሞ ለዜጎች አለማሰብ ነው ሲሉ ያስረዳሉ።

በአጠቃላይ የቤት ፕሮግራሙ በመመሪያና በደንብ የማይመራ፤ ለመንግሥትም ባዕድ ፕሮጀክት ነው። ተጠያቂነትም የለም። ለበርካታ ዓመታት ተገንብተው የተወሰነ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ሳይጠናቀቅ በማቆም የአገር ሀብት እየባከነ መሆኑን ጠቅሰው ዜጎችም በቤት እጦት እና በተለያየ የዕዳ ክፍያ በኢኮኖሚ ጫና እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብለዋል።

ለዝግጅት ክፍላችን በቀረበው ቅሬታ ዙሪያ ምላሽ ለማግኘት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሪት የንጋትኮከብ ምላሽ ለመስጠት በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም ለሦስት ሳምንት ያህል የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በአካልም ሆነ በተደጋገሚ የስልክ ግንኙነት መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በቀጣይም የሚሰጡን ምላሽ ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም የወጣ ሲሆን፤ ባለአንድ መኝታ 3 ሺህ 60፣ ባለሁለት 10 ሺህ 322 እና ባለሦስት መኝታ 5 ሺህ 194 በድምሩ 18 ሺህ 576 መሆናቸው ይታወሳል።

አዲስ ዘመን ግንቦት 23/2012

 አጎናፍር ገዛኸኝ
Br 1,100,000
 ካሬ ቆሬ ኮንደሚንየም ሽያጭ

ስፋት:– 54 ካሬ
ባለ 1 መኝታ
ለሽያጭ የቀረበ በካሬ ቆሬ አጃምባ ሳይት
3ኛ ፍሎር ላይ የሚገኝ
ዕዳ 120,000
ሰሚት ኮንዶሚንየም የሚሸጥ
አድራሻ:- ሰሚት እሳትና ድንገተኛ አካባቢ
ዋጋ ብር 2,000,000
ፎቅ:- 2ኛ ላይ
መኝታ:- ባለ 3 ስፋት:-86 ካሬ ከመኝታዎቹ በስተቀር ክፍሎቹ ጂብሰም ቦርድና ፍሬም በደንብ የተሰሩ
ዕዳ ብር 320 ሺ አለበት ( ዋጋው ከነእዳው ነው) ለእጅ ብር 1,700,000
Condominuim Sale & Buy Addis Ababa
📌የሚሸጥ ኮንዶሚንየም ቤት ካሎት ይላኩልን
📌ኮንዶሚንየም/አፓርታማ ባለ1, 2 እና 3 መኝታ ይግዙ፣ይሽጡ!
📌To Buy or Sell Condominium House send descriptions
via @natang2

Subscribe 👉 @condoaddis
Like us 👉 https://www.facebook.com/Condoadis
https://t.me/condoaddis