Condominuim Market in Addis Ababa
3.63K subscribers
2.34K photos
60 videos
10 files
1K links
በዚህ የቴሌግራም Chanel
ከ10,000 ተከታይ በላይ ባለው facebook page
በቀን እስከ 500 ሰው ጎብኚ ብለው condoaddis.etsecurities.com
በማስታወቂያ ክፍያ ቤትዎን እና መኪናዎን መሸጥ ፣ ማከራየት ይችላሉ ኮሚሽን መክፈል ለማይፈልጉ
buy ads here https://telega.io/c/condoaddis
0913587955
መረጃ ለመላክና ለጥያቄ
@antget1
Download Telegram
ለማህበር ቤት የተደራጃችሁ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅታችሁ ቤት ለመገንባት በመመዝገብ በ57 ቡድን ከተደለደላችሁት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ፡፡

ቀደም ሲል በተቋሙ ማህበራዊ ገፅ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ ቢተላለፍም እሰከአሁን ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ በመኖራችሁ ለመጨረሻ ጊዜ በ25/7/2015 - 27/7/2015 ድረስ ለ 3 ተከታታይ የሥራ ቀን ባምቢስ ከግሪክ ት/ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢ.ቁ.601 ቀርባችሁ ሪፖርት ካላደረጋችሁ በገዛ ፍቃዳችሁ ከቡድን ድልድሉ የተሰረዛችሁ መሆኑን እና በምትካችሁ ተጠባባቂዎችን የምንተካ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

በገጻችን የምናቀርባቸውን የቤቶች ልማት ኤጀንሲ መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
Fb.me/condoadis

ተጨማሪ ለመረዳት
👇👇👇
www.condoaddis.com/03042023-1
👍2
ገርጂ 40/60 ኮንዶሚንየም የሚሸጥ

ባለ 1 መኝታ
61 ካሬ በጣም ሰፊ
8ኛ ፎቅ

ዋጋ ብር 6 ሚልየን
ይደውሉ 0913587955

ለተጨማሪ👇👇 www.condoaddis.com/03042023-3
👍3
6ሺህ 938 እድለኞች እስካሁን ቀርበው ውል አልተዋዋሉም ተባለ

የአዲስ አ/አ ቤቶች ኮርፓሬሽን በ20/80 ለ14ኛ ዙር ፣ በ40/60 ለ3ኛ  ዙር የጋራ መኖሪያቤት አጣ ወጥቶላቸው  ውል እንዲዋዋሉ ከጥር 1/2015 ዓ.ም.  ጀምሮ ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኘው የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት ቅፅ 09 ወደ መኖሪያ ቀበሌዎች ወስደው አስሞልተው ለማምጣት ቀርበው የወሰዱ 25,703 ሲሆኑ የቀበሌውን ቅፅ 9 አስሞልተው በመመለስ ቅፅ 03 ወደ ባንክ ቀርበው መውሰድ የሚገባቸው ሰዎች ብዛት 25,353 ሰዎች ናቸው።

ይሁን እንጂ ቅፅ 03 ትን እስካሁን የወሰዱት 22,235 ናቸው ይህም በመቶኛ ሲሰላ 87.71% ነው ።

ከእነዚህ መካከል የባንኩን ሂደት ጨርሰው ወደ አንድ ማእከል ተመልሰው እስከ መጋቢት 25/2015 ዓ,ም. ድረስ ውል የተዋዋሉ በ20/80 እድለኞች ቁጥር 16,617 ሰዎች ፣ በ40/60 እድለኞች 2,218 ሰዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም አስካሁን ውል የፈፀሙት 18,835 ሰዎች ብቻ ናቸው ። ይህም ማለት መዋዋል ካለባቸው 25,773 ሰዎች መካከል 6,938 ሰዎች እስካሁን ቀርበው ውል አልተዋዋሉም ማለት ነው ። የባንኩን ቅፅ 03 ወስደው እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ ደግሞ 3,400 ሰዎች ናቸው ።

ከጥር 1/2015 እስከ መጋቢት 25/2015 ዓም ድረስ አስፈላጊውን ፕሮሰስ ጨርሰው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰራላቸው የተላኩ  በ20/80 እድለኞች ብዛት 15,836 ሰዎች  በ40/60 እድለኞች ብዛት 1,235 ሰዎች በአጠቃላይ ለካርታ የተላኩ 17,071 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን የኮርፓሬሽኑ የቤት ማስተላለፍ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ካሳሁን ዘውዴ አስታውቀዋል። በዚህ መሰረት ወደ ካርታ ስራ ያልተላኩ 8,702 ፋይሎች ይቀራሉ ማለት ነው ።

እንደ ዳሬክተሩ ገለፃ በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች ከ25,773 ሰዎች ውላቸውን ተዋውለው ካርታቸውን ሊወስዱ እንደሚገባ ጠቁመው ካለው ቁጥር አንፃር  ሲታይ በተለያዩ ምክንያቶች ቀርበው ያልተዋዋሉ እንዳሉ ጠቁመዋል ።

እንደሚታወቀው የውል መዋዋያ ጊዜው ላለፉት 3 ወራት ማለትም ከጥር 1/2015 ጀምሮ እስከ መጋቢት 26/2015 ድረስ ብቻ እንደሆነ የገለፁት ዳይሬክተሩ በተቀመጠው መርሀግብር መሰረት የውል ጊዜው መጋቢት 26/2015 ያበቃል ። አምስት ቀን (5) የመክፈያ ጊዜ ብቻነው ከዚህ በኃላ የሚቀረው ስለሆነም ወደ 6938 ሰው ገና ያልተዋዋሉ አሉ በዚህ መካከል በፕሮሰስ ላይ ያሉትን ጨምሮ ገና በርካታ ሰዎች በሂደት ላይ ያሉ መሆናቸውን ኮርፓሬሽኑ ስለተረዳ የውል ማዋዋሉ ሂደት ለአንድ ወር እንዲራዘም መጠየቃቸውን ገልፀዋል ።

የቤት እድለኞች መገንዘብ ያለባቸው አሁን በጠየቁት የውል መዋዋያ ይራዘምልን ጥያቄ መሰረት አንድ ወሩ ከተፈቀደ በተሰጣቸው እድል ቀርበው መዋዋል ካልቻሉ  በመመሪያው መሰረት ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ለመንግስት ተመላሽ ስለሚሆን ባለ እድለኞች አሁንም ወደ አንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ በመምጣት እንዲዋዋሉ ጥሪ አቅርበዋል ።

__
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በፌስቡክ ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
F.me/condoadis
እንዲሁም፦
www.condoaddis.com/04042023-1
👍6
የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት ለ30 የስራ ቀናት ተራዘመ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ14ኛ ዙር የ20/80 እና 3ኛ ዙር የ40 /60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እጣ አውጥቶ ለባለ እድለኞች ለማስተላለፍ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 26/2015 ዓ.ም ውል ሲያዋውል መቆየቱ ይታወቃል :: የመወያያ ጊዜውም መጋቢት 26/2015 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት 60 የስራ ቀናት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ መዋዋል ካለባቸው 25,773 መካከል ውል የተዋዋሉት 1,835 ብቻ በመሆናቸው ቀሪዎቹ በፍርድ ቤት፣ በግዳጅ ፣ በወሊድና በሌሎችም ምክንያቶች ቀርበው መዋዋል ላልቻሉ ውል እንዲዋዋሉ ለማድረግ እና ፕሮሰስ ጀምረው ያላጠናቀቁትን እንዲያጠናቅቁ ለማስቻል ኮርፖሬሽኑ በአዋጅ ቁጥር 64//2011 አንቀፅ 22 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት እስካሁን ውል ያልተዋዋሉ የቤት እድለኞችን ማዋዋል እንዲያስችል ከመጋቢት 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ 30 የስራ ቀናት ያራዘመ መሆኑን እያሳወቅን በነዚህ ቀሪ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ ማንኛውም የቤት እድለኛ ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሩ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን እንዲያውቁት ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

ለተጨማሪ መረጃ 👇👇
www.condoaddis.com/07042023-1
👍1
#እጅግ# ውብ ፅድት ያለ አፓርትመንት ነው ወይስ ቪላ የሚያስብል ፊኒሺንግ የተሰራለት ግርም #ኮንዶሚንየም##ሽያጭ#

#ቦሌ አራብሳ ሳይት#

97 ካሬ ስፋት

ባለ 3 መኝታ

1ኛ ፎቅ ላይ

ቆንጆ ሎኬሽን ላይ የሚገኝ

ዋጋ ብር 7.5 ሚልየን

ይደውሉ 0913587955
ለተጨማሪ መረጃ 👇👇
www.condoaddis.com/07042023-2
👍2
Ayat 49 condominium 40/60 for sale

Two bedrooms & one additional servant room
Area:- 75 sqm
Floor:- 8th

Finishing works on progress
Water and electricity available 

Price Birr 4.5 million
Call us 0913587955

For more info👇👇
www.condoaddis.com/07042023-3
👍3
#Jemo 3 condominium for sale

Bedroom:- 2
Size:- 72 sqm
Floor:- Ground

Price Birr 4.7 million
#Cash buyers only
Call 0913587955

For more 👇👇
www.condoaddis.com
👍1