Computer knowledge
175 subscribers
30 photos
65 videos
215 files
78 links
💻ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እዚህ ቻናል ላይ
📲አዳድስ የቴክኖሎጅ ዜናዎች
📲በቪዲዮ የተደገፉ የTech መረጃወችን
📲ስለ software programing
📲ስለ Android HACKING
Also about hidden records on the world
Fast foreign countries news

For Comment and cross 👉 @MrGx234
Download Telegram
👑 ROYAL WAVE 👥

📢 ቻናላቹን በአንድ ጊዜ ማሳደግ ና አንድ ላይ ለማደግ ይፈልጋሉ!
- እንግድያውስ ይሄን እድል ይጠቀሙ።
✔️ ስለታማኝነት አያስቡ 100% ፌር የሆነ ስራ እሰራለሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ።

📢 ከ 1k _ 10k ያላቹ ቻናሎች አሁኑኑ ያናግሩኝ።
- ላልሰሙ አሰሙ!
- ሼር እያረጋቹ!

✍ መመዝገብ የምትፈልጉ ብቻ አናግሩኝ።
- ለመመዝገብ @YoniRoyal
- Spam @YoniTechTips_Bot
C++ ምንድን ነው?


C++ ዓላማ--ተኮር እና አጠቃላይ ፕሮግራሞችን የሚደግፍ አጠቃላይ-ዓላማ ፣ ጉዳይ-ተኮር ፣ ነፃ-ቅፅ የፕሮግራም ቋንቋ ነው።
C++ የሁለተኛ ደረጃ እና የዝቅተኛ ደረጃ የቋንቋ ባህሪያትን አጣምሮ የያዘ በመሆኑ እንደ መካከለኛ ደረጃ ቋንቋ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡

C++ የተሰራው በ 1980 ዎቹ መጀመሪያ ላይ በኤቲ ኤንድ ቴል ቤል(AT&T Bell labs) ላቦራቶሪ በBjarne Stroustrup ሲሆን በ C ቋንቋ ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡ “++” በ C (ተለዋዋጭ ለመጨመር) ጥቅም ላይ የዋለ የተዋሃደ ግንባታ ሲሆን C++ ደግሞ እንደ ተጨማሪ ጭማሪ ማሻሻያ የታሰበ ነው አብዛኛው C የ C ++ ንዑስ ክፍል ነው ፣ ስለሆነም አብዛኛዎቹ የ C ፕሮግራሞች ሊጠናቀሩ ይችላሉ (ማለትም መለወጥ) ኮምፒውተርን በቀጥታ ሊያከናውንባቸው በሚችሉት አነስተኛ ደረጃ መመሪያዎች ውስጥ) የ C ++ አቀናባሪን በመጠቀም ፡፡
C++ የ “C” ልዕለ-ነገር ነው ፣ እና በእውነቱ ማንኛውም ህጋዊ C ፕሮግራም ህጋዊ C++ ፕሮግራም ነው።

ዓላማ-ተኮር መርሃግብር(Object-Oriented programming)

C++ ነገሮችን-ተኮር የልማት አራቱን ምሰሶዎች ጨምሮ አላማ -ተኮር ፕሮግራምን ሙሉ በሙሉ ይደግፋል-
- Encapsulation
- መረጃን መደበቅ
- ውርስ
- ፖሊሞርፊዝም

የ C ++ ጥቅም

- ሲ ++ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፕሮግራም አድራጊዎች(Programmers) በመሠረቱ በእያንዳንዱ የመተግበሪያ ጎራ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ ፡፡

- በአዶቤ ሲስተምስ ውስጥ ሁሉም ዋና አፕሊኬሽኖች በ C ++ የተገነቡ ናቸው - Photoshop & ImageReady, Illustrator, Acrobat, InDesign, GoLive

-C++ ለመሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች ስኬታማ ትምህርት በቂ ንፁህ ስለሆነ ለማስተማር እና ለምርምር በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡

- የአፕል ማኪንቶሽንም ሆነ ዊንዶውስን የሚያከናውን ፒሲን የተጠቀመ ማንኛውም ሰው በተዘዋዋሪ C++ ን ተጠቅሟል ምክንያቱም የእነዚህ ዋና ዋና ተጠቃሚዎች በይነገጾች በ C ++ የተፃፉ ናቸው ፡፡

- አማዞን ዶት ኮም ፣ ፌስቡክ ፣ ጉግል ፣ ኤችፒ ፣ አይቢኤም ፣ ማይክሮሶፍት ፣ ሞዚላ ፣ ኖኪያ እና ሌሎች ብዙ ኩባንያዎች ሲ ++ ቋንቋን ይጠቀማሉ ፡፡
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @compknowledge
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
🌱 የሞባይል ሃርድዌር ክፍል

ለመሆኑ ሃርድዌር ማለት ምን ማለት ነዉ ?

#ሃርድዌር ፦ ማለት በዓይናችን ማያት የምንችለው የሞባይል ክፍል ነዉ በተጨማሪ በእጃችን መዳሰስ መንካት የምንችለው ክፍል ነዉ ።

እሺ በእጃችን መደሰስ የምንችለው የሞባይል ክፍሎች እነማን ናቸዉ አንድ በአንድ የተወሰኑትን እንዳስስ እስክ ....

🙏 1ኛ ቻርጀር ኮኔክተር ፦ ማለት ስልካችንን ከመብራት ጋር የምያገናኝ ስልካችን ቻርጅ እንድያደርግ የምያደርግ የሞባይል ሃርድዌር ክፍል ነዉ
ቻርጅ ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን ቻርጅ አያደርግም በተጨማሪ ስልካችን ቻርጅር እያመርጠ ያስቸግርናል......

🙏 2ኛ ባቲር ኮኔክተር ፦ ማለት ባቲሪያችን ከሞባይሉ ተገጣጥሞ እንድዝ የምያደርግ ጥርስ ነዉ ይህ ማለት አንደንዴ በአንደንድ ስልኮች ጥርሶቹ አራት ይሆናል አብዛኞቹ ስልኮች ግን በለ ሦስት ጥርስ ነዉ በአጭሩ ሞባይላችን የለባቲር ኮኔክተር አይሰራም....

🙏 3ኛ ጆሮ ማይክ ፦ ማለት ደግሞ በስልካችን ሰዉ ስደዉልልን እኛ አንሲተን ሲናዉራ የደዋዩን ድምፅ ለእኛ የምያሰማን ጆሮ ማይክ ነዉ
ጆሮ ማይክ ከተበላሸ የደዋዩ ድምፅ አይሰማም ሲናገር ....

🙏 4ኛ እስፒከር ኮኔክተር ፦ ማለት ሰዉ ደዉሎልን ሲናዉራ የእኛን ድምፅ ለደዉዩ የምያሰማ የሞባይል ክፍል ነዉ
ጓደኞቼ እንደይምታታባቹ ጆሮ ማይክ እና እስፒከር
እስፒከር ከተበለሸ እኛ ደዉለን ሲናዉራ ምንም አይሰማም ለደዉልንት ሰዉ

🙏 5ኛ ርንገር ኮኔክተር ፦ ማለት ሙዚቃ ቪድዮ በስልካችን ሲናጫዉት ድምፅ የምያሰማን ክፍል ነዉ ርንገር ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን የፈለግነዉን ነጋር ሙዚቃ ድርማ ወዘተ ቢናጫዊተዉ ድምፅ አያሰማም
ጓደኞቼ እንዳትወዛገቡ ድምፅ ማሰማት ምናምን እስፒከር ኮኔክተር እንዳይመስላችሁ ርንገረ ኮኔክተር ነዉ እንጅ......

🙏 6ኛ ካሜራ ኮኔክተር ፦ ማለት ድግሞ በስልካችን ፎቶ ለማንሳት የምጠቅም በስልካችን የተገጠመ ፎቶ ማንሻ ወይም ቪድዮ መቅርጫ ኮኔክተር ነዉ

🙏 7ኛ ሲም ኮኔክተር ፦ ማለት ደግሞ ስልካችንን ከሲም ካርድ ጋር የምያገናኝ የሞባይል ክፍል ነዉ ሲም ኮኔክተር ከተበላሸ ወይም ከተሰበር ሲም ካርድ ቀፎዎችን ሲም አይሰራም .....

8ኛ ሚሞር ኮኔክተር ፦ ማለት ሚሞረወን ከስልካችን ጋር የምያገናኝ የሞባይል ክፍል ነዉ ሚሞር ኮኔክተር ከተበላሸ ስልካችን ሚሞር አይሰራም.....

🙏 9ኛ ኔቶርክ ኮኔክተር ፦ ማለት ስልካችን ኔቶርክ እንድሰራ የምያደርግ ክፍል ነዉ አንዳንዴ ኔቶርክ ኮኔክተር በላይም ከሰፈለገም ከውስጥም የምገጠምበት አጋጣሚ አለ...

🙏 10ኛ ኤርፎን ኮኔክተር ፦ ማለት ድግሞ ስልካችን ድምፁን ከርንገር ወጪ የምያደርግ ክፍል ነዉ ኤርፎን ኮኔክተር ከተሰበር ስልካችን ኤርፎን አይሰራም ....
ሳተላይት ኢንተርኔት ምንድን ነው?

ሳተላይት ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ማለት ልክ በዳያል አፕ፣ በብሮድባንድ፣ በፋይበር ኦፕቲክስ ወይም በሌላ ዓይነት መንገድ የምናገኘውን ዓይነት ኢንተርኔት ሊሰጠን የሚችል ሌላኛው አማራጭ ማለት ነው።

በላንድ ላይን በምናውቀው ዓይነት በገመድ [ኬብል] አማካይነት የሚሰራጨውን ዓይነት ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፤ እንጠቀምበታለን። ነገር ግን የሳተላይት ኢንተርኔት አጀማመሩ በፍፁም አሁን የምንጠቀመው ዓይነት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ የሌለበት ሁኔታ ሲሆን፤ ምንም ዓይነት ሌላ ምርጫ በሚጠፋ ጊዜ በተለይ ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችን እሳቤ በማድረግ የተሰራ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው።

ሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰራውም ሕዋ [ስፔስ] ላይ ካሉ ሳተላይቶች ጋር በመሆን ተጠቃሚዎች ደግሞ ዲሽ ቤታችው ላይ ቢሯቸው ላይ በማድረግ፤ በመሬት ላይ ደግሞ የኔትወርክ ኦፕሬቲንግ ሴንተር እና ቴሌፖርት የሚባሉ አሉ።

በእነዚህ በሦስቱ ጥምረቶች ኢንተርኔትን ለተጠቃሚ የሚያደርስ ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ቪሳት [Very small aperture terminal (VSAT) ይባላል። ሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰራውም በዚህ አማካኝት ነው።
🆔ስልካችሁ ላይ #አፕልኬሽን ስትከፍቱ :

♻️This Application Stopped Working
♻️Crashing
♻️Won’t open
♻️Won’t respond
♻️Isn’t working properly

.........................እያለ ላስቸገራችሁ መፍትሔ

🔱.#Restart እና #Update ይሞክሩ፤ እንደዚህ ስታደርጉ በአብዛኛው ጊዜ ይስተካከላል።👍

1) ስልካችሁን #Restart አድርጉት።

❇️Setting Software Update ውስጥ ገብታችሁ የስልካችሁን Operating System #Update አድርጉ።

❇️Play store ላይ ገብታችሁ አፑን #Update አድርጉት።

2) .Update Google Play Services

❇️ስትከፍቱ #Update አድርጉት ይላችኋል።

3) . አፑን የማትጠቀሙበት ከሆነ Setting ውስጥ ገብታችሁ #Forced_Stop አድርጉት።

❇️System App ካልሆነ #Uninstall ያድርጉት።

4). Clear App and Cache ይሞክሩ።

❇️Setting➡️ Manage apps➡️ ያስቸገራችሁን አፕ➡️ Clear Data and Clear Cache.

5). እኔ እንዳየሁት ከሆነ ከላይ በነገርኳችሁ መፍትሔ 95% ስልኮች ይስተካከላሉ👍 ለተቀሩት ስልኮች #Hard_Reset መሞከር ይቻላል።

❇️ኮፒ ስልኮችንና ብዙ ጊዜ Hard Reset የተደረጉ ስልኮችን አይጨምርም እነሱ ስልኮች ሌላ ታሪክ ውስጥ ናቸው።😁
#ሟር
https://t.me/joinchat/VQQzbntxyAVAVruq
🆔 #ICT_terms

♻️ 30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች

❇️1.
#ጥቁር_መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው።

❇️2.
#ብሉቱዝ (Bluetooth) -ገመድ አልባ ከሞባይል እና
ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል

❇️3.
#ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ
ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው።

❇️4.
#አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ

❇️5.
#መሠረታዊ _የግብአት/ውጤት ሲስተም ሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) -የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው።

❇️6.
#ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው።

❇️7.
#ሲዲ_በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች
ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው።
ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ
መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል።
ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊው ድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው
መጻፍ ይችላሉ።

❇️8.
#ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና
የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ።

❇️9.
#ክሌም_ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ የተሠራየኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ

❇️10.
#ኮቢያን_ባክአፕ (Cobian Backup) -
የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው።
የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው
የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤
የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ።

❇️11.
#ኮሞዶ_ፋየርዎል (Comodo Firewall) -
ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው።

❇️12.
#ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ
(browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው።

❇️13.
#ዲጂታል_ፊርማ (Digital signature) -
ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን
የማረጋገጫ መንገድ

❇️14.
#የዶሜይን_ስም (Domain name) - በቃላት
የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ

❇️15.
#ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ ትክከለኛው መረጃ ማለትም ያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ

❇️16.
#ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ
የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም
በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል

❇️17.
#ኢሬዘር/መደምሰሻ (Eraser) ከኮምፒውተር
ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት

❇️18.
#ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው።

❇️19.
#ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን
አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤት ውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው።

❇️20.
#ነጻና_ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር- ኤፍኦኤስኤስ
(Free and Open Source Software-FOSS) -
ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች
የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣ እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ ሶፍትዌሮች ምድብ

❇️21.
#ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (sourcecode) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች

❇️22.
#ጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU/Linux) -
የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤
ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው።

❇️23.
#ጂፒኤስ (Global Positioning System - GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ
በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤ በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣
በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው።

❇️24.
#ሐከር/ሰባሪ (Hacker) በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስስ
መረጃዎቻችንን ለመስረቅ አይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ

❇️ 25.
#የኢንተርኔት_ፕሮቶኮል_አድራሻ-(
አድራሻ) (Internet Protocol address -IP
address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ

❇️26.
#ኢንተርኔት_አገልግሎት (አይኤስፒ)
(Internet Service Provider-ISP) - የኢንተርኔት ወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም
ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔት አሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ።

❇️27.
#ኢንፍራሬድ_ዳታ (Infrared Data
Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት
የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀም
መረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል።

❇️28.
#ጃቫ_አፕሊኬሽንስ (Java Applications)
(አፕልትስ/Applets) - በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

❇️29.
#ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር
የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ
የመተየቢያ ገበታ (keyboard) ላይ የነካናቸውን/ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

❇️30.
#ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው።
https://t.me/joinchat/VQQzbntxyAVAVruq
⚡️10 ጎግል ላይ ስኬታማ የሆነ መረጃ የመፈለጊያ ዘዴዎች::⚡️

👋ሰላም ሰላም የቻናሉ አባላት ብዙ ጊዜ ሰዎች ጎግል ላይ የፈለጉትን ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ይቸገራሉ::

🔎ሰርች ሲያረጉ የማያስፈልጋቸው ነገር ግን በዛ ርዕስ ስር ያለ መረጃ በብዛት ያገኙታል::

ስለዚህ የተመረጡ ጥሩ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ዘዴዎች ይጠቀሙ::

⚡️1.የቃላትን ትክክለኛ ትርጉም/ውጤት ለመግኘት⚡️
ስለ ፃፋችኃቸው ቃላት ትክክለኛ ውጤትን ለማግኘት " ይህን ምልክት ከቃሉ በፊት እና በኃላ መጠቀም ይመረጣል::

ለምሳሌ❗️የ iPhone የሚለውን ቃል ትርጉሙን ለማግኘት "iPhone" ብላችሁ ብትፅፉ ይመረጣል::

⚡️2.ከአንድ ዌብሳይት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ሌሎች ዌብሳይቶችን ለማግኘት⚡️

💡ይህን ለማድረግ related የሚለውን ቃል ከዌብሳይቱ በፊት መፃፍ ነው::

ለምሳሌ እንደ አማዞን ያሉ ዌብሳይቶችን ለማግኘት related:amazon.com ብሎ ሰርች ባሩ ላይ መፃፍ ነው::
ከዛም በአይነታቸው ከአማዞን ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ዌብሳይቶች ይመጡላችኃል::

⚡️3.ጎግል የምትፈልጉትን ብቻ እንዲያመጣላችሁ - ይህቺን ምልክት ተጠቀሙ::
ለምሳሌ spider-movie ብላችሁ ብትፅፉ የሚመጣላችሁ ስለ ሸረሪት ብቻ ይሆናል ፊልም አይመጣላችሁም::

⚡️4.የአንድን ዌብሳይት ከዚህ ቀደም የለቀቃቸውን ፅሁፎች ለማግኘት⚡️

የዌብሳይቱን የቀደሙ ፅሁፎች በቀላሉ ለማግኘት ፅሁፉን በመፃፍ ከዛ site: ን አስቀድመን ጎግል መረግ ነው::

ስለ ባራክ ኦባማ ከቢቢሲ ዌብሳይት ለማንበብ

Barrack Obama site:bbc.com ብለን መፃፍ ነው::

⚡️5.የቃላትን ፍቺ ለማግኘት⚡️

Define: የሚለውን በማስቀደም ቃሉን መፃፍ ነው::

⚡️6.የተለያዩ ፋይሎችን ለማግኘት⚡️

ይህን ለማድረግ የፋይሉ ስም በማስቀደም filetype: ብለን የፋይሉን አይነት መፃፍ ነው::

ለምሳሌ መርበብትfiletype:pdf ብለን ብንፅፍ ፒዲኤፉ ይመጣልናል::

⚡️7. አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት⚡️
#Action 2020 ብላችሁ በመፃፍ ወይም #ይህን ምልክት አስቀድማችሁ የፈለጋችሁትን በመፃፍ መረጃውን መያዝ ትችላላችሁ::

⚡️8.የቃላትን በሌላ ቋንቋ ስያሜ ለማወቅ⚡️

ለምሳሌ cat ትርጉሙን/ አጠራሩን በfrench ማወቅ ብንፈልግ translate english to french cat ብለን መተየብ ነው::

⚡️9.የእንግሊዝኛ ቃላትን ስፔሊንግ ለማስታወስ⚡️

*ይቺን ምልክት በጠፋን ስፔሊንግ ቦታ መተካት ነው::
ለምሳሌ da*nger ብለን ብንፅፍ danger የሚል ቃል ይመጣልናል::

⚡️10.የከተሞችን የአየር ሁኔታ ለማወቅ⚡️

Weather ን ከከተማው ስም በፊት መፃፍ ነው::
ለምሳሌ wether London ብለን ብንተይብ የከተማውን የአየር ሁኔታ ይገልፅልናል::

💍🕓እነዚህን በመጠቀም ጊዜያችሁንና ብራችሁንም መቆጠብ ትችላላችሁ::

🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀🌀

♨️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎት
ቻናሉን 📢#unmute በማድረግ ይተባበሩን::

♨️ጥያቄዎትን በ https://t.me/joinchat/Uzlpv8jqOWc9xSFz ላይ ይጠይቁ::

♨️ቻናሉን ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩት::

🙏ከዘመኑ ጋር አብረው ይጏዙ!!!🙏

@compknowledge 🚶🏽📱
📌ከዚህ ግዜ አንስቶ ሀምዛ በአሜሪካ ተፈላጊ ከሆኑት top10 አደገኛ አስሩ ወንጀለኞች ተመደበ።
በታይላንድ ባንኮክ ወድ ግብፅ ሊሄድ ሲል እስከተያዘበት ቀን ድረስ በበርካታ የአለም ሀገራት ላይ እየተንቀሳቀሰ ሲኖር ነበር።
የአልጄርያ መንግስት ወጣቱን ጂንየስ ሀምዛ ያጠፋውን እዳ ከፍዬ በነፃ እንዲለቁትና ባለው እውቀት ሀገሩን እንዲያገለግል ብትጠይቅም ሀምዛ እስራኤል ላይ ያለው የማይመለስ አቋም አሜሪካ ይሄን ካሳ እንዳትቀበልና ሃምዛን እንዳትለቅ የ15 አመት እስራት ፈርዳበታለች ፤ ከሀምዛ ጋር speEYE የተባለውን ማልዌር አብሮ የሰራውን አደገኛውን ሀከር Aleksandr Andreevich Panin 9 አመት ከ 6 ወር እስራት ተፈርዶበታል።

●○በ2015 አንድ የቱኒዚያ ዌብሳይት ሀምዛ የሞት ፍርድ ሊፈረድበት ነው የሚል ዜና ይዞ ከወጣ በኋላ የአልጄሪያ መንግስትና ህዝብ በtwitter,facebook..ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረው ነበር::

በኢኔተርኔት ላይ በገመድ ስቅላት ሊደረግበት ሲል የሚያሳየው ፎቶ የእሱ ሳይሆን የአክቲቪስት መጊድ ካራፊር ነው፡፡ Bendelladj የሞት ቅጣት አልተላለፈበትም።

በታይላንድ ፓሊሶች እንደተያዘም እየሳቀ am not a terrorist ሲል ነበር።
ከተያዘ ጀምሮ ፊቱ ላይ የሚነበበው የደስታ ድባብ ባደረገው ነገር እንደኮራ ያሳያል።

ŠNoah (Dxkiller)
ብዙ ጊዜ termux ለመጠቀም አስበን ግን አጠቃቀሙን ሳታውቁ ቀርታቹ ይሆናል ግን አሁን በጥቂቱ አስተምራችኋለሁ 🧐
¤ termux ለ hacking የተሰራ የ android app nw
¤ በtermux hack የሚደረገው command በመፃፍ ነው ለምሳሌ :- pkg install Python
¤ termux ለአጠቃቀም ቀላል ነው
¤ በ termux hack የሚደረገው -social media
-iP address and location
-camera
-sms
-web
-Android.........
¤ብዙ ጊዜ termux hack ለማረግ phishing እንጠቀማለን phishing ማለት አንድን ሰው ሀክ ለማረግ የምንጠቀምበት ስልት ሲሆን በማታለል ሰውየው ወደ ሀክ የሚያረገው web እንዲገባ ወይም የተፈለገው app,photo እንዲጭን መገፋፋት ነው
ምርጥ 8 ነፃ አንቲቫይረስ ሶፍትዌር ለኮምፒዩተር 2021
The Best Free Antivirus Software in 2021

✅ Avast Free Antivirus.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-avast-antivirus/

✅ AVG AntiVirus FREE.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-avg-antivirus/

✅ Avira Antivirus.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-avira/

✅ Bitdefender Antivirus Free.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-bitdefender/

✅ Kaspersky Security Cloud – Free.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-kaspersky-rescue-disk/
✅ Microsoft Defender Antivirus.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-security-essentials/

✅ Sophos Home Free.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇

https://www.filehorse.com/download-sophos-home/

✅ Smadav Antivirus 
🔶 Smadav Antivirus mainly function as additional protection for your PC (especially its total protection for USB Flash Drive), so the software doesn't offer total protection.
አንቲቫይረሱን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇
https://www.filehorse.com/download-smadav-antivirus/
💢 ውድ የcomputer knowledge ቤተሰቦች ዛሬ ደሞ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፍሉ ምርጥ 1ዐ የስራ ዘርፎችን ይዘን መተናል።

🔺Product manager

◽️ Product managers: በቢዝነስ ቴክኖሎጂ ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፣ አንዳንዶቹ ከproject managers ጋር አንድ አድርገው ይቆጥራሉ ግን አይደሉም። Product managers በሚሰራው ምርት ላይ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን መንደፍ፤ የቡድን አባሎችን ማስተባበር እና ሌሎች ከምርቱ ጋር ተያያዥነት ባለቸው ነገሮች ላይ በንቁ ይሳተፋሉ።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 100,000 $

🔺Artificial Intelligence (AI) Engineer

◽️ AI Engineer: ለድርጅቱ የሚሆኑ የተለያዩ ተግባሮችን በAI ላይ ተሞርክዞ ማበልጸግ፤ ማኔጅ ማድረግ። AI engineer በሂሳብና ስታሰቲክስ ጠለቅ ያለ እውቀት ሊኖረው ይገባል።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 119,000 $

🔺Full-Stack Developer

◽️ የFull-stack አበልጻጊ ይሄ ነው ብሎ ማብራራት ያስቸግራል፣ ግን ተቀራራቢው ማብራሪያ ሊሆን የሚችለው፡ የሆነ ሰው በሁለቱም ማለትም back-end እና front-end ላይ በደንብ እውቀቱ ሲኖረው ወይም በሚበለጽገው ምርት በእያንዳንዱ ደረጃዎች ላይ በቂ ክህሎት ሲኖረው።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 110,000 $

🔺Cloud Architect

◽️ Cloud architect: ዋናው ተግባሩ የድርጅቱን የCloud computing ስትራቴጂ መንደፍ፤ ማኔጅና ስምሪት ማደርግና cloud architecture መቅረጽ።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 118,000 $

🔺DevOps Engineer

◽️ DevOps engineer: በግልጽ የተቀመጠ ሚና የለውም። እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡ የሆነ ሰው በተቋቋመው የብልጽግና ቡድን ውስጥ ገብቶ በdeployment እና network operation ክፍል ላይ ሲሳተፍ ወይም ከOperation ቡድን እንደገና በመተግበሪያ ቡድን ላይም ሲሳተፍ።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 123,000 $

🔺Blockchain Engineer

◽️ Blockchain engineer: ስፔሻላይዝድ የሚያደርገው blockchain ንን በመጠቀም ችግር ፈቺ መፍትሄዎችንና architecture ማበልጸግ ላይ ነው። በዚህ ዘርፍ ላይ የሰለጠኑ ልምድ ያላቸው ባለሙያተኞች እጥረት አለ።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 130,000 $

🔺Software Architect

◽️ Software architect: የብልጽግና ሂደትን አመረቂ እንዲሆን ጥሩ ዲዛይን መምረጥ፤ በቴክኒካል ስታንዳርድ እንደ ኮዲንግ፤ ቱሎችና ፕላትፎርሞች ላይም መወሰን ይችላል።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 130,000 $

🔺Big Data Engineer

◽️ Big Data engineer: በጣም ግዙፍ በሆነ የብልጽግና ሂደቶችና የBig Data መተግበሪያዎች ላይ ዲዛይን ያወጣል ያቅዳል።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 140,000 $

🔺Internet of Things (IoT) Solutions Architect

◽️ IoT solutions architect: በIoT solutions በስተጀርባ ስላለው ብልጽግና እና ስምሪት ስትራቴጂ ላይ በአመራርነት ያገለግላል።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 133,000 $

🔺 Data Scientist

◽️ Data scientist: ውስብስብ ዳታን አናላይዝ በማድረግ ድርጅቱን የተሻለ ማድረግ ብሎም ጊዜው የሚፈልገውን ውሳኔ እንዲወስኑ ይረዳቸዋል።

💰አማካኝ አመታዊ ክፍያ: 141,000 $

↘️#share ማድረጎን አይርሱ🙏🙏🙏

🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

@compknowledge
✳️ ትውልደ ኔትዎርክ1G, 2G, 2.5G, 3G, 4G, 5G

▫️1ጂ

ከ1980-1990 ፍጥነቱ #2.4Kbps ሚሰራዉ በ አንድ ሀገር
ዉስጥ ብቻ ነዉ ሚጠቀመዉ የ ሞገድ አይነት አናሉግ ነዉ
መጀመሪያ #ዩኤሰኤ(USA)ዉሰጥ ነዉ ደካማ ጎኑ #የድምፅ ጥራት
የለዉም ባትሪ ይጨርሳል ስልኩ ትልቕ ነዉ ሴኪዩሪቲ የለዉም

▫️2ጂ

የተጀመረዉ ፊንላንድ ነዉ በ 1991 ዲጂታል ሞገድ ነዉ
ሚጠቀመዉ እስከ #64kbps ደርስ ፍጥነት አለዉ መልእክት
መላላኪያ አለዉ(SMS,MMS) ጥሩ የድምፅ ያሰማል። ደካማ
ጎኑ #ጠንካራ ሞገድ ይፈልጋል አንድ ቦታ ከተበላሸ ሌላ ቦታ ሞገዱ
ይደክማል ብዙ ዳታ መላክ እና መቀበል አይችልም።

▫️2.5 ጂ

#በ 2ጂ እና 3ጂ መካከል ይገኛል ኢሜል መላክ እና መቀበል
ያስችለናል ኢንተርኔት ማስጠቀም ይችላል 64Kbps-144Kbps

▫️3ጂ
#በ 2000 አከባቢ ነዉ የተጀመረዉ ፍጥነቱ 144Kbps-2Mbps
ትልቅ መጠን ያለዉ ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችላል #እየተያዩ
መደወል ይቻላል/3ዲ ጌሚንግ(3D GAMING) ቀጥታ ቲቪ
ማየት/የስልክ ቲቪ ደካማ ጎኑ ዉድ ነዉ መስመሩን መዘርጋት
ከባድነዉ ስልኮቹ ትልቅ/ዉድ ናቸዉ ብዙ ሞገድ ይጠቀማል

▫️4ጂ

#ፍጥነቱ ከ100Kbps-1Gbps ሌላ ስሙ #(MAGIC)
(M)obile Multimedia
(A)nytime Anywhere
(G)lobal Mobility Support
(I)ntegrated Wireless Solution
(C)ustomized Personal Services
#ደካማ ጎኑ ባትሪ በጣም ይጠቀማል ዉስብስብ የሆነ ስልክ
ያስፈልጋል ዉድ አቃዎች ያስፈልጋሉ መስመሩን ለመዘርጋት

▫️5ጂ

#ከ 2010 ጀምሮ ነዉ ይሄ ሁሉን ነገሮች አሉት እንከን የለዉም ብዙ
ነገር ይሰራል እያንዳንዱን ነገር #ጥርት አርጎ ያሳያል (HD)
ከሁሉም በጣም ፈጣን ነዉ በ አንድ ግዜ ብዙ ነገር ያስጠቅማል
ከ 1Gbps በላይ ፍጥነት አለዉ ለ ማንኛዉም አገልግሎት
በያዝነው 2020 እየቀረበ ይገኛል ::

@compknowledge
💢📲በስልካችን #Internet 🌐 ስንጠቀም ቶሎ ቶሎ ካርድ እንዳይቆጥርብን ምን ማድረግ አለብን❓

1⃣ #Setting🛠 ውስጥ በመግባት background data restricted ማድረግ (ከኛ እውቅና ውጪ የአፕልኬሽኖች በራሳቸው ዳታ እንዳይጠቀሙ ያደርጋል)

2⃣ ሲም ካርዳችንን #3G ከነበር ወደ #2G መቀየር አስፈላጊ ነው (በተለይ #Facebook ለረጅም ሰአት ምንጠቀም ከሆነ)

3⃣ #Facebook በምትጠቀሙበት ጊዜ በ F እና Facebook lite ባትጠቀሙ እና እንደ opera mini, uc, messenger lite አይነት browser's መጠቀም ይመረጣል።

4⃣ ረጃጅም ፅሁፎችን 📃 በሚያነቡበት ጊዜ ዳታ ማጥፋት ✖️ ወይም save page ማድረግ አለብን።

5⃣ በ WiFi 📶 ካልሆነ በቀር play store, Instagram, palm play አለመክፈት እና #video_online_play /#download/ አለማድረግ ይመረጣል።

↘️#share ማድረጎንአይርሱ

@compknowledge
በቀጣይ ምን software ይዘን እንምጣ
Anonymous Poll
13%
ANTIVIRUS
31%
Game
31%
Graphics design
25%
Animator app
​​✳️ Artificial Intelligence (AI):

◽️ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በማሽኖች በተለይም በኮምፒተር ስርዓቶች ውስጥ የሰዎችን የማሰብ ችሎታ በኮዲንግ (Coding) በማስገባት የኮምፒውተሮችን የአስተሳሰብ ሂደት ከሰዎች ጋር የማስመሰል ስራ ነው።

◽️ Artificial Intelligence (AI) የሚሠራው ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መረጃዎች ከፈጣን እና ተለዋዋጭ የሥራ ሂደት ጋር በማጣመር ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ስልተ ቀመሮች በመጠቀም ሶፍትዌሩ ሲስተም ውስጥ ካሉ መረጃዎች ራሱን-በራሱ እንዲያስተምር ያስችለዋል፡፡

🔺የAI ምሳሌ

◽️ በ iPhone እና በ iPad ውስጥ በአፕል ከሚቀርቡት በጣም ታዋቂ የግል ረዳት (Personal Assistant) Siri አንዷ ናት፡፡ ይህች ተግባቢ ሴት የተለያዩ የተቀነባበሩ ድምፆችን በመጠቀም የተጠቃሚዎቾን የእለት ተእለት ኑሮ ለማቅለል ትረዳለች።

◽️ Siriን በመጠቀም ሞባይላችንን በምንም አይነት መልኩ ሳንነካ ከሷ ጋር በመነጋገር ብቻ የተለያዮ መረጃዎችን ማግኘት ፣ የመንገድ አቅጣጫዎችን ማግኘት ፣ መልዕክቶችን መላክ ፣ የስልክ ጥሪዎችን ለማድረግ ፣ አፖችን መክፈት እና ሌሎችም ነገሮችን ለማድረግ እንችላለን።

◽️ Artificial Intelligence ለሰው ልጆች የሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለ ሆኖ በሰው ሰራሽ አጠቃላይ የማሰብ ችሎታ ላይ የሚደርሰው አደጋ በሰው ሰራሽ አጠቃላይ መረጃ (AGI) ውስጥ አንድ ቀን በሰው ልጅ መጥፋት ወይም ሌላ ሊመለስ የማይችል ዓለም አቀፍ ጥፋት ሊያስከትል ይችላል የሚል መላምት አለ።

◽️ የሰው አንጎል ሌሎች እንስሳት የጎደሏቸው አንዳንድ የተለዩ ችሎታዎች ስላሉት በአሁኑ ጊዜ የሰው ዝርያ ከሌሎች ዝርያዎች የበላይ ነው። ነገር ግን የAI አጠቃላይ የማሰብ ችሎታ ከሰው ልጅ የሚበልጥ ከሆነ እና “የላቀ የማሰብ ችሎታ” ያለው ከሆነ ለሰዎች መቆጣጠር ከባድ ወይም የማይቻል ሊሆን ይችላል።

◽️ እንስሳት እጣ ፈንታ በሰው በጎ ፈቃድ ላይ እንደሚመረኮዝ ሁሉ የሰው ልጅም ዕጣ ፈንታ ወደፊት በሚመጣው የማሽን ብልህነት ተግባር (AI) ላይ የተመረኮዘ ሊሆን ይችላል።
#ምርጡን እና ጠቃሚውን_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ

ይህ አፕሊኬሽን PDF Cam Scanner ይባላል፡፡
ይህ አፕሊኬሽን በሞባይል ስልካችሁ ካሜራ አማካኝነት የተለያዩ በጣም ጠቃሚ #ዶክመንቶቻችሁን ስካን አድርጎ ሶፍት ኮፒ ወደ PDF ፎርማት ለውጦ ያስቀምጥላችኋል፡፡

#PDFCamScanner አፕሊኬሽን ተጠቃሚ ከሆናችሁ የተለያዩ ጠቃሚ ዶክመንቶቻችሁን በPDF ፎርማት ስልካችሁ ላይ በማስቀመጥ ቤትኛውም ቦታና ሰዓት #ዶክመንቶቻችሁን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የተለያዩ ከስራ ጋር የተያያዘ ወይም የግል ጠቃሚ ዶክመንቶች ይኖራችኋል፡፡
ለምሳሌ፡-

ተማሪዎች፡-
#ሲቪ
#የትምህርት ማስረጃዎች ይኖራችኋል

ሌሎቻችሁ ደሞ፡-
#መንጃ ፍቃድ
#ፓስፖርትና የቀበሌ መታወቂያ
#ንግድ ፍቃድ
#ግብር የከፈላቸችሁበት ደረሰኞች
#ውሎች #የፍርድ ቤት ዶክመንቶች….ወዘተ ይኖራችኋል

እነዚህ በጣም ጠቃሚ #ዶክመንቶች በወረቀት መልክ ቤታችን እናስቀምጣለን፡፡

ጉዳያችንን ለማስፈፀም የተለያዩ መ/ቤቶች ስንሄድ የነዚህ #ዶክመንቶች ፎቶ ኮፒ እንጠየቃለን፡፡ስለዚህ ምንድ ነው የምናደርገው- እነዚህን በጣም ጠቃሚ ዶክመንቶች በፎልደር ይዘን እንዞራለን ማት ነው፡፡

ነገር ግን ይህ ሁኔታ ብዙ #ችግሮችን ይፈጥራል፡፡

ለምሳሌ እነዚህ ዶክመንቶች ይዘን ስንዞር #ዶክመንቶቹ ቢጠፉስ፤ከነ ፋይል መያዣው #ቢጠፋስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው የምንገባወ፡፡

ነገር ግን በ #PDFCamScanner አፕሊኬሽን ዶክመንቶቻችሁን በሙሉ ስካን እያደረጋችሁ ሞባይል ስልካችሁ ላይ ብታስቀምጡ፡-

1ኛ፡- ዶክመንታችሁ #በፎልደር ይዞ ከመዞር ትገላገላላችሁ

2ኛ፡- ዶክመንቶቹ #ቢጠፉ ስልካችሁ ላይ ስለተቀመጡ ከመጨነቅ ትድናላችሁ

3ኛ፡- አንድ ቢሮ ሄዳችሁ ድንገት አንድ #ዶክመንት ብትጠየቁ…አይ አልያዝኩትም ወይም ረስቼው መጣሁ…ነገ አመጣለሁ አትሉም፡፡ እዚያው ሞባይላችሁ ላይ ገብታችሁ የተፈለገው ዶክመንት #ፕሪንት አድርጋችሁ መስጠት ትችላላችሁ፡፡ ግዜ ይቆጥባል፡፡

ለምሳሌ፡- #ስራ ፈላጊ አዲስ ተመራቂዎች መንገድ ላይ ስትሄዱ ድንገት ለናንተ የሚሆን ስራ ማስታወቂያ ብታገኙ እና የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ዛሬ ቢሆን አመለጣችሁ ማለት ነው፡፡

ምክንያቱም ሲቪያችሁ ቤት ኮምፒውተር ላይ ፤ወይም ፍላሽዲስክ ላይ ነው ያለው፡፡ እና #ኮምፒውተራችሁም፤ፍላሽ ዲሰካችሁንም አልያዛችሁም፤ ቤታችሁ ሄዳችሁ ለማምጣት ደሞ ግዜ አይበቃችሁም፡፡ ስለዚህ ቀለጣችሁ ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ቀደም ብላችሁ #የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን፤ሲቪያችሁን በ #PDFCamScanner ስካን አድርጋችሁ ሞባይላችሁ ላይ ካስቀመጣችሁ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ስታገኙ ከሞባይል ስልካችሁ ላይ የተፈለገውን #ዶክመንት #ዳውንሎድ አድርጎ ፕሪንት በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

#PDFCamScanner አፕሊኬሽን #ዶክመንቶቻችሁን ብትፈልጉ በከለር ብትፈልጉ በነጭና በጥቁር በPDF ፎረማት ስካን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

እኔም #ተጠቃሚው ነኝተጠቀሙበት ትውዱታላችሁ፡፡
Computer knowledge pinned «በቀጣይ ምን software ይዘን እንምጣ»
✳️ #ስልኬ_ሊጠለፍ ይችላል የሚል ስጋት አለብዎ 🤷‍♂

የሚያዋሩበት ሞባይል ስልክዎ በተለያዩ ምክንያቶች ሊጠለፍብኝ ይችላል የሚል ስጋት ካለብዎ የሚከተሉትን #ቁልፎች ተጭነው ይደውሉና መጠለፍ አለመጠለፋን ያረጋግጡ።

*#21# ብለው ሲደውሉ ፦

1. #Not_forwarding የሚል ምላሽ ከሰጠዎ ስልክዎ አልተጠለፈም ከስጋት ነጻ ነው ማለት ነው።

ወይም *#21# ብለው ሲደውሉ ፦

▫️VOICE: Not Forwarded
▫️DATA: Not Forwarded
▫️SMS:... Not Forwarded
▫️SYNC: Not Forwarded
▫️ASYNC:Not Forwarded
▫️PACKET:Not Forwarded
▫️PAD :Not Forwarded
የሚል መልዕክት ከመጣሎት ስልኮ አልተጠለፈም ማለት ነው።

2. #Forwarding የሚል ምላሽ ከሰጠዎ ግን በእርግጠኛነት ተጠልፎብዎታል ማለት ነው።

ከላይ በተቀመጠው መሰረት ስልኮ ከተጠለፈና #ጠለፋውን_ለማቆም ፦
የተጠለፈበዎትን ስልክ ለማስቆም እንዲሁም ወደፊት እንዳይጠለፍ ለማድረግ ##002#ብለው ሲደውሉ call forwarding all erased successful ይልዎታል።

አሁን #ከስጋት_ነፃ ወጡ ማለት ነው።
ነገር ግን ይህ ኮድ ሁሉም ስልኮች ላይ ይሰራል ማለት ላይሆን ይችላል ። ብቻ ይሞክሩት።

#Share with your friend
@compknowledge
💢What is HTML?

✅#HTML is the standard #markup_language for creating web pages.

- HTML stands for Hyper Text Markup language.
(HTML ስንሰራ ስዕል እንደመሳል ነው፤ እኛ keyboard ላይ የምንሰጠውን monitor ላይ ያወጣዋል አለቀ፤ ለዚህም ነው programming language አይደለም የሚባለው)።

- HTML describes the structure of Web pages using markup.

-HTML elements are the building blocks of HTML pages.

-HTML elements are represented by tags.

-HTML tags label pieces of content such as "heading", "paragraph", "table", and so on.

- Browsers do not display the HTML tags, but use them to render the content of the page.