Computer knowledge
175 subscribers
30 photos
65 videos
215 files
78 links
💻ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እዚህ ቻናል ላይ
📲አዳድስ የቴክኖሎጅ ዜናዎች
📲በቪዲዮ የተደገፉ የTech መረጃወችን
📲ስለ software programing
📲ስለ Android HACKING
Also about hidden records on the world
Fast foreign countries news

For Comment and cross 👉 @MrGx234
Download Telegram
ውጤት ተለቋል!

የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል። ውድ Ethio Games ቤተሰቦቻችን ውጤት ለማየት http://result.neaea.gov.et ላይ የመፈተኛ ቁጥራችሁን በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

መልካም ውጤት ተመኝተናል።

SHARE https://t.me/joinchat/ReQVjc7NNWMGdcUT
✅ ስልካችን ቢበላሽ እንዴት አድርገን ስልክ
ቁጥሮቻችንን እናገኛለን?
✅ እባኮትን ይህንን የማያውቁ እህት ወንድሞቻችን እንዲያውቁ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን
~~~~~~~1ኛ~~~~~~~~~
እንዴት Buckup እንያዝ?
🔶 Step By Step
1:-contact ዉስጥ መግባት
2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን
3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ
እሱን መጫን
4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን
መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ
FileManager መክፈት
5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት
6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ
7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል
8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad
በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል
~~~~~~~2ኛ~~~~~~~~
2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት
በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል
1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን
2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት
3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት
4:-inport/ export ዉስጥ መግባት
5:-Import from Storage ማድረግ
3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል።
በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል።
ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ
~~~~~~~~~3ኛ~~~~~~~~
1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ /
2:-Contacts/ የሚለውን መጫን
3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/የሚለውን በመጫን የስልክ አግራሻችንን ጂሜይል ላይ ለማኖር እንችላለን

▬▬ ▬ Share ▬▬▬▬
https://t.me/joinchat/ReQVjc7NNWMGdcUT

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
👍Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
👍Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"

የtelegram ቻናላችንን join በማድረግ የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ያሳድጉ!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@compknowledge

▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬
Cartoon Photo Filters-CoolArt_v2.0.9_apkpure.com.apk
22.6 MB
🔆ፎቶ ወደ ካርቶን(carton) መቀየርያ #ምርጥ አፕሊኬሽን ❤️
✳️ Tech News

📌አፍሪካውያን ታሪካቸውን በራሳቸው ቋንቋ በድምፅ በመቅረጽ የሚያስተዋውቁበት መተግበሪያ ተሰራ።

📌አፍሪካውያን የታሪክ ተናጋሪዎች ታሪካቸውን በራሳቸው ቋንቋ በድምፅ በመቅረጽ የሚያስተዋውቁበት መተግበሪያ ተሰራ። አማርኛን ጨምሮ  በሌሎች ቋንቋዎች የአፍሪካን ታሪኮች ወደ ድምፅ መጽሐፍት መቀየር የሚያስችል መተግበሪያ በጋናው የሶፍት ዌር ኩባንያ ሶፍትትራይብ ባለቤት ሄርማን ቺነሪይ-ሄስ ተሠርቷል።

‼️ Join & Share...
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
✳️ TOP 10 Best ''PC'' Games of All Time !!የምንግዜም ምርጥ የሚባሉ 10 የ PC ጌሞች።© Tech Amo

​​‼️ Join & Share.
📲በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት🌐 እየተጠቀምን በተደጋጋሚ ብቅ የሚሉ ማስታወቂያዎችን እንዴት ነው ልናስቆማቸው የምንችለው?

💢ቀለል ያሉ #ሁለት(2) መንገዶችን ልጠቁማቹ።

#1ኛው_መንገድ:

1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና #Settings መግባት

2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Site Settings የሚለውን መምረጥ

3⃣. Site Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Pop-ups and redirects የሚለውን ክሊክ ማድረግ

4⃣. Pop-ups and redirects የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF

5⃣. OFF የሚለውን መምረጥ፡፡በቃ ካሁን በሃላ አስሬ ብቅ እያሉ የሚበጠብጣችሁ ማስታወቂያዎች ይጠፋሉ።👍

🔆2ኛው_መንገድ:- Turn On the Data Saver

- እዚያው የምትጠቀሙበት ክሮም ብራውዘር ላይ ዳታ ሴቨር (Data Saver) #On ለማድረግ፦

1⃣. Chrome ብራውዘራችሁን ክፈቱ እና Settings ውስጥ መግባት

2⃣. Settings ውስጥ ስትገቡ ከሚመጡ አማራጮች መካከል Data Saver የሚለውን መምረጥ

3⃣. Data Saver የሚለው ሲመጣ ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነሱም -ON እና OFF

4⃣. -ON የሚለውን መምረጥ በቃ አለቀ፡፡👍

🌍🌍🌍🌎🌎🌏🌎🌏🌎🌏🌏🌍🌍🌍

📌መረጃዎችን ለወዳጅዎ 🗣👥 ያጋሩ።

📥መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #MUTE(🔇🔕) ያደረጋችሁት #UNMUTE(🔊🔔) በማድረግ ተባበሩን🙏
💫10 አሪፍ አሪፍ የቴሌግራም BOT/ቡቶች💫

1 @vote Vote መስጫ ፖል ለመስራት።

2 @BunaGebeya_bot ለቡና ደጋፊዎች ብቻ።

3 @pocket_music_bot ማንኛውም የባህር ማዶ ዘፈነ ለማግኘት።

4 @songlyrbot የውጭ ሃገር ዘፈኖችን ላይሪክስ ለማግኘት።

5 @renamebot የቴሌግራም ፋይሎችን ሪኔም ለማረግ።

6 @toolkitbot በተን ያላቸው የቴሌግራም ፖስቶችን ለመስራት።

7 @mp3toolsbot ዘፈን ማቀናበሪያ።

8 @Stickers ስቲከር መስሪያ ቡት።

9 @apkdl_bot ማንኛውም ምትፈልጉት አፕ እዚ download marge tclalacu

10 @Baymax_free_bot ግሩፕ መቆጣጠርያ bot
ደመናን የማዝነብ ቴክኖሎጂ (cloud seeding)
====================
የመጀመሪያው የክላውድ ሲዲንግ ሙከራ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1946 በአሜሪካዊው ኬሚስትና ሜትሮሎጂስት ቪንሰንት ሼፈር እንደተከናወነ የሚነገር ሲሆን ከዚህ ጊዜ አንስቶ ደመናን በአርተፊሻል መንገድ ለማዝነብ፣ ጭጋጎችን ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር እና ሌሎች ተያያዥ የዌዘር እንሃንስመንት (weather enhancement) ስራዎችን ለማከናወን እየዋለ እንደሚገኝ ይገለጻል፡፡ አየር በውስጡ እርጠበት የሚይዝ ሲሆን ይህን እርጥበት ያዘለ አየር በቴክኖሎጂ አማካኝነት ወደ መሬት በዝናብ መልክ እንዲወርድ ማድረግ የክላውድ ሲዲንግ ሚና ይሆናል፡፡
ቴክኖሎጂው ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በዋናነት አርጠበት ይዞ ያለውን ዳመና ሲሊቨር አዮዳይድ (siliver iodide) የተባለውን ኬሚካልን በመጠቀም በተለይም ተበታትኖ የሚገኘውን የደመና ቅንጣት በማሰባሰብ እና ለዚሁ ስራ ተብሎ በተዘጋጀ አውሮፕላን አልያም በሌላ መንገድ በደመና ላይ በመርጨት ዝናበን ለማዝነብ የሚያስቸል ዘዴ ነው፡፡ ዌዘር ኢንሃንስመንት በሚባለው ሰው ሰራሽ ዝናብ የማዝነብ ሙከራ ብዙ የቴክኖሎጂ አቅም የሚጠይቁ መንገዶች ቢኖሩም ቀላሉ የሆነው በአካባቢው የሚገኘውን ደመና በመጠቀም የሚደረግ የከላውድ ሲዲንግ ቴክኖሎጂ ነው። Cloud seeding የተለያዩ ኬሚካሎችን በመጠቀም ደመና በዝናብ ወይም በበረዶ መልክ ወደ መሬት እንዲወርድ ማድረግ ሲሆን ለምሳሌ ከ ሲሊቨር አዮዳይድ በተጨማሪ የሶዲየም ክሎራይድ፣ ፖታሺየም ክሎራይድ እንዲሁም Dry ice (ብናኝ በረዶ) በመጠቀም ሰው ሰራሽ ዝናብ ማዝነብ ይቻላል። በቅርብ የተደረጉ ግኝቶች እንደሚያሳዩት የምግብ ጨው በደመና ላይ በመጠቀም የተሻለ ዝናብ ማዝነብ እንደሚቻል ይገለፃል።
በዚህ የረዥም ጊዜ ፕሮጀክት ላይ የምርምሩ ተሳታፊ የሆኑት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የቴክኖሎጂ አማካሪ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለቴክኖሎጂው አሰራር ለማብራራት እንደሞከሩት የከላውድ ሲዲንግ አተገባበር በአጭር ጊዜ እና በረዥም ጊዜ ሊተገብር የሚችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት ሲሞከር የቆው የቴክኖሎጂው አተገባበር በስፋት የሚገኙትን የሶዲየም ክሎራይድ እና ፖታሺየም ክሎራይድ ድብልቅ (ሃይድሮስኮፒክስ) በመጠቀም በአውሮፕላን የሚረጨው አተገባበር ሲሆን ከዚህ በኋላም ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር ምርምሩን ይበልጥ በማበልፀግ በምን መልኩ ቴክኖሎጂው መተግበር እንዳለበት የሚወሰን መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምርምሩን አስፋፍቶ ለማከናወን የፅንሰ-ሀሳብ ማረጋገጫ (proof of concept) በሚሰራበት ወቅት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው ልታገኘው የምትችለው ሁለተናዊ ጥቅም በተለያየ ፈርጅ ለማየት መሞከሩን የሚናገሩት አቶ ዮዳሄ ከኢኮኖሚ አዋጭነት፣ ከቴክኒካል ፊሲቢሊቲ እና ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች አንፃር ቴክኖሎጂው በሀገር ደረጃ ምን ምን ጉዳይ ላይ ሊተገበር እንደሚችል መጠናቱን ይናገራሉ፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ብዙ ሀገራት ይህን ቴክኖሎጂ የሚተገብሩት የግድብ ስራዎች ላይ ውሃን በፍጥነት ለመሙላት እና ሌሎች የግብርና እንቅስቃሴዎች ለማፋጠን በመሆኑ እንደታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት የዝናብ ውሃን መጠበቅ ሳያስፈልግ በፍጥነት ለመሙላት እና ዝናብ አጠር በሆኑ ቦታዎች የውሃ ሃብትን ለማስፋት ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥር ይናገራሉ፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ ካለይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ከሌሎች የዌዘር ኢንሃንስመንት ስርዓቶች አንፃር በዋጋ ደረጃ አነስተኛ የሚባለው ሲሆን እንደ አቶ ዮዳሄ አገላለፅም ለኬሚካል ርጭቱ በዋነኝነት የሚያስፈልጉት የሶዲየም ክሎራይድ እና ፖታሺየም ክሎራይድ ንጥረ ነገሮች በኢትዮጵያ እንደልብ መገኘታቸው ቴክኖሎጂውን ይበልጥ ለማስፋፋት እድል እንደሚሰጥ ይነገራሉ፡፡
ውድ የፔጃችን ተከታታዮች በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ ሰፊ ዘገባ የሚኖረን ይሆናል
ድምጽን ብቻ በመጠቀም የኮቪድ 19 ተጠቂዎችን የሚለየው መተግበሪያ
***************************
የሰዎችን ድምጽ ብቻ በመጠቀም የኮቪድ ተጠቂዎችን ለመለየት የሚያስችል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ መተግበሪያ መሰራቱ ተሰማ፡፡ ይህ መተግበሪያም 80 በመቶ የደረሰ ትክክለኝነት እንዳለውም ተሰምቷል፡፡ እንደሚታወቀው ኮቪድ 19 የሚያሳየው ምልክት ከሰዎች ሰዎች የተለያየ በመሆኑ ተጠቂዎችን መለየት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ አንድ ሰው የጉሮሮ መከርከር፣ ሙቀት፣ ሳል ወይም የማሽተትና የመቅመስ ችግር ሲስተዋልበት የኮቪድ ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ይመከራል፡፡
ይህንን ችግር የተመለከተው ቮካሊስ የተሰኘ ኩባንያ የኮቪድ ተጠቂዎችን ለመለየት የሚያስችል ድምጽንና የሞባይል መተግበሪያን የሚጠቀም ቴክኖሎጂን አበልጽጓል፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ የተለየ የሚያደርገው ነገር በአንድ በቫይረስ የተጠቃም አካባቢ የሚገኙ ሰዎችን ለመለየት ሁሉንም ሰዎች ወደ ጤና ተቋም ማምጣት አስፈላጊ ቢሆንም ቴክኖሎጂው ልየታውን ለማድረግ ሰዎች ባሉበት ሆነው በድምጻቸው ብቻ ቫይረሱ በውስጣቸው መኖሩንና አለመኖሩን መለየት የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ይህን ለማድረግ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ይጠቀማል፡፡
ቮቻሊስ የተሰኘው ድርጅት ከሰዎች ድምጽ ጋር የተያያዙ ሰፊ መረጃዎችን የሰበሰበ ሲሆን የቴክኖሎጂ ተቋሙ የህመም ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች የሚኖራቸውን ድምጽ ሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የተሰበሰበውን የድምጽ መረጃ በመጠቀም የሚለይ ቴክኖሎጂን አበልጽጓል፡፡ ካምፓኒው ያበለጸገው ስልተ ቀመር 512 የሚደርሱ የተለያዩ የድምጽ ባህሪያትን የለየ ሲሆን ተገማች ህመሞችን መተንበይ የሚያስችለውን ምስል spectrogram ይሰራል፡፡
በሙከራ ወቅትም ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ከ50 እስከ 70 የሚደርሱ ቁጥሮችን እንዲቆጥሩ በማድረግ ቴክኖሎጂውን የማለማመድ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም 275 ሺህ የሚደርሱ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ይህ ቴከኖሎጂ በአሜሪካ፣ቺሊ፣ኢንዶኖዢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሉክሰምበርግ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ቮካሊስ የተሰኘው መሰረቱን እስራኤል ያደረገው ተቋም በ2019 የተመሰረተ ሲሆን በያዝነው አመት በህንድ ሙባይ 2000 ታካሚዎችን በመመርመር ነው ስራውን የጀመረው፡፡

ምንጭ The next web
Šadama tech
ሰላም ለዚህ ቻናል ቤተሰቦች ሁሉ፤ለዛሬ አንዳንድ የሞባይልና ተያያዥ አከሰሰሪወች አጠቃቀም ስህተት በተመለከተ ከታዘብኳቸው መካከል የተወሰኑትን የማደርሳችሁ ይሆናል።

1, ኤርፎን መጎንጎን(እንደ ፀጉር ስሬት) :— መጎንጎን በኤርፎኑ ኬብል ውስጥ ያሉት ድምፅ አስተላላፊ የሆኑት ቀጫጭን ገመዶች እንዲሰባበሩ በማድረግ ኤርፎኑ ስራውን እንዲያቆም ይሆናል።
2, ቻርጀርን አዳብተር ላይ ሁሌም ቻርጅ የሚደረግ ሞባይል ሳይኖር እንደተሰካ እዛው ላይ መተው የቻርጀሩን እድሜ ስለሚያሳጥረው ይህን መጥፎ ልማድ ማስወገድ ይኖርብናል።
3, ስማርት ስልክን ያለሴፍቲ ከቨርና ግላስ መጠቀም ለአደጋ ተጋላጭ ስለሚያደርገው በተለይ ውድና መለዋወጫቸው ሀገር ውስጥ እንደልብ የማይገኙ ስልኮችን ተጠንቅቆ መያዝ መተኪያ የሌለው አማራጭ ይሆናል።
4,ውሀ የገባን ስልክ ወዲያው አስነስቶ ለመጠቀም መሞከር ስልኩን ለበለጠ ጉዳት ስለሚዳርግ፤ባትሪውን አውጥተን ፀሀይ ላይ ማስጣትና አሊያም ሩዝ ውስጥ ማስገባት ጊዚያዊ መፍትሄ ይሆናል። የበለጠው አማራጭ ግን ወደ ባለሞያ መውሰዱ በተራዘመ ጊዜ ለሚመጣ የተባባሰን ብልሽት ማስቀረት ይቻላል። ሌላው ደግሞ ባትሪው የማይወጣ ስልክ ከሆነ ስልኩን ማጥፋት(switched off) ማድረግ ቀዳሚ እርምጃ መሆን ይኖርበታል። በመቀጠልም
ፀሀይ ማስመታና ሩዝ ውስጥ ማስገባት ጊዚያዊ አንዳንዴም ዘላቂ መፍትሄን ሊያመጣ ይችላል።
በተለይ ስልኩ በደንብ ውሀ ላይ የቆየ ከሆነ ብዙ ውሀ ከገባበት በቀጥታ ወዲያውኑ ወደ ባለሞያ መውሰዱ መተኪያ የሌለው አማራጭ ይሆናል።
5,ጥቅማቸው እዚህ ግባ የማይባሉ መተግበሪያወችን መጫን ስልኩን የማጨናነቅና ሶፍተዌሩን እስከማዛባት ስለሚያደርሱ አለመጫን ይመረጣል። ለምሳሌ የስልክ ጥሪ ማሳመሪያ የተለያዩ ዌልፔፔሮችና የመሳሰሉት ቢቀሩ ይመረጣል። በተረፈ አፖችን ከጎግል ፕሌይ ስቶር ማውረድ ከቫይረስ ነፃ የሆነ አፕ እንዲኖረን ያደርጋል።
6,ያለምንም ምክንያት ብሉቱዝና ዋይፈይን ከፍቶ መተው ባትሪያችን ቶሎ እንዲያልቅ ስለሚያደርግ ተጠቅመን ከጨረስን በሗላ ወዲያውኑ መዝጋት የተሻለ ነው።
ይቀጥላል

👤 Channel https://t.me/compknowledge
8 ተመራጭ ፎቶ እና ቪድዮ ማቀናበሪያ አፕልኬሽኖች
አብዛኛውን ጊዜ ፎቶዎችን እና ቪድዮዎችን ኤዲት ለማድረግ ተንቀሳቃሽ ስላካችንን📱 እንጠቀማለን ሆኖም ግን በጣም ቀላል እና በአንድ ጊዜ በጣም ብዙ ነገሮችን መስራት እየቻልን እነዚህን ዋነኛ አፖችን ባለማግኘት ለእያንዳንዱ ነገር የተለያዩ እና ብዙ አፖችን እንጠቀማለን ይህም ለስልካችን STORAGE እና አለአስፈላጊ ጊዜ እናባክናለን እናም እንዚህን ትንሽ አፖችን ብቻ ከPLAY STORE አውርደን በመጠቀም ለሌሎች አፖች የምናጠፋውን ጊዜ በ1 አፕ ብቻ መጨረስ እንችላለን ማለት ነው

#ከነዚህ ምርጥ አፖች መካከል
➢PHOTO EDITORS
1. PicsArt
2. PixelLab
3. Airbrush
➢VIDEO EDITORS
1. Kinemaster
2. FilmoraGo
3. Powet Director
#EthioTechs_News

✅በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን በማየት ኮቪድ 19ኝን የሚመረምር የሞባይል📲 መተግበሪያ ተሰራ።

🔆መሰረቱን ጀርመን ያደረገ ሰሚክ አር ኤፍ የተባለው ኩባንያ በሦስት ደቂቃ ውስጥ ዓይንን👀 ፎቶ በማንሳት /ስካን/ በማድረግ ኮቪድ19ኝን የሚመረምር የሞባይል📲 መተግበሪያ /አፕሊኬሽን/ መስራቱን አስታወቀ፡፡

🔆ይህ ሦስት ደቂቃ ይወስዳል የተባለው መመርመሪያ 95 በመቶ ውጤታማ ነው ተብሏል፡፡

🔆መተግበሪያው ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን📲 በመጠቀም ቫይረሱን እንደሚለይ ተገልጿል፡፡

🔆እስካሁን በ70 ሺህ ግለሰቦች ላይ እንደተሞከረም ተሰምቷል፡፡

🔆በደቂቃዎች ውስጥ ስካን በማድረግ በሚሊየን የሚቆጠር ውጤት ይሰጣል ተብሏል፡፡

🔆ይህም እንደ እግር ኳስ ባሉ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ዝግጅቶች ላይ መተግበሪያውን መጠቀም እንደሚያስችልም ነው የተገለጸው፡፡

🔆መተግበሪያውን ለንግድ አላማ መጠቀም ለሚፈልጉ ኩባንያዎች በወር 570 ዶላር መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

📌ኩባንያው ጊዜውን በትክክል ባያስቀምጥም ለግለሰቦች ለማዳረስ ዕቅድ መያዙንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

#Share
@compknowledge
✳️ Tech News

📌የቴስላ ሼር መወደድን ተከትሎ ... ለሳምንታት የአለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም የነበረው elon musk... በቴስላ ሼር መቀነስ ምክንያት የአንደኛ ደረጃነቱን መልሶ ለአማዞኑ ጆፍቤዞስ አስረክቧል።

📌ቴስላ 1.5 ቢሊየን ዶላር ቢትኮይን መግዛቱ ለቴስራ ሼር መቀነስ እንደምክንያት ከተጠቀሱት ውስጥ አንዱ ሆናል ።
‍✳️የፌስቡክ ኩባንያ የቲዊተርና ፤ ኢንስታግራም እና የማህበራዊ ትስስር ገጾች የሳይበር ጥቃት ማስተናገዳቸው ተሰማ

🔻የግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ፌስቡክ በቲዊተርና የኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ለአጭር ጊዜ በመረጃ በርባሪዎች ቁጥጥር ውሎ እንደነበር ተነገረ።

🔻አወርማይን /OurMine/ የተባለው የመረጃ በርባሪዎች ቡድን በኩባንያው የኢንስታግራምና የቲዊተር ገጾች ላይ "ፌስቡክ እራሱ ተሰብሮ ይገባበታል" በማለት ጽሁፍ አስፍሮ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

🔻የበይነ-መረብ መረጃ ጠላፊ ቡድኑ እንዳለው በፌስቡክ ላይ የሰነዘረው ጥቃት በኢንተርኔት ላይ ያለን ለጥቃት ተጋላጭነት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ነው።

🔻በፈረንጆቹ ጥር ወር ላይም ቡድኑ ተመሳሳይ ድርጊትን በአሜሪካ እግር ኳስ ቡድኖች ገጾች ላይ ፈጽሞ ነበር።
ቡድኑ በፌስቡክ የቲዊተር ገጽ ላይ "ሰላም፤ አወርማይኖች ነን። ፌስቡክ በደህንነት አስተማማኝነት ከትዊተር የተሻለ ቢሆንም ከመሰበር አያመልጥም" የሚል መልዕክትን አስፍሮ ነበር፡፡።

🔻አወርማይን ቀደም ባለው ጊዜ የትልልቅ ተቋማትንና የታዋቂ ግለሰቦች አካውንቶች ላይ ጥቃት በመፈጸም የሚታወቅ መቀመጫው ዱባይ ውስጥ እንደሆነ የሚነገርለት የበይነ-መረብ በርባሪ ቡድን ነው።

🔻ቡድኑ እንደሚለው የሚፈጽማቸው ጥቃቶች በበይነ መረብ ላይ ያለውን ደካማ የደህንነት አጠባበቅን ለማጋለጥ ነው።
አሁን ላይ በመረጃ ጠላፊዎች ተሰብረው የነበሩት የፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ወደነበሩበት መመለሳቸው ተገልጿል።
✳️ ማስጠንቀቂያ ለ Facebook ተጠቃሚዎች በሙሉ‼️

🔻የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ሰሞኑን ሾልኮ ከወጣው የፌስቡክ ዝርዝር ውስጥ ካለ እንዴት ማረጋገጥ ይችላሉ?

🔻ሰሞኑን ከ530 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዳታ (ስልክ፣ ኢሜይል ወዘተ) በጠላፊዎች ሾልኮ እንደወጣ ተሰምቷል። ከዚህ ውስጥ 12,000 ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙበትም ታውቋል።

🔻የእርስዎ ስልክ ወይም ኢሜይል እዚህ ዝርዝር ውስጥ ከተገኘ ማረጋገጫ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል በውስጥ መስመር ጥያቄዎች ደርሰውኛል።

🔻Have I Been Pwned (https://haveibeenpwned.com/) የተባለ ድረ-ገፅ ይህን ማረጋገጥ ይችላል።

🔻አጠቃቀሙ እንዲህ ነው.... https://haveibeenpwned.com/ ድረ-ገፅን ሲከፍቱ የመፃፍያ/ Search / ማርጊያ ቦታ ያገኛሉ። ባዶ ቦታው ላይ ስልክዎን ወይም ኢሜይልዎን ያስገቡ። በመቀጠል " pwned? " የሚለውን ይጫኑ።

🔻" Oh No- Pwned " የሚል መልስ ካገኙ ስልክዎ ወይም ኢሜይልዎ ለጠላፊዎች (ሀከሮች) ተጋልጦ ነበር ማለት ነው። " Good News- No Pwnage Found!" የሚል ምላሽ ካገኙ ለጠላፊዎች (ሀከሮች) አልተጋለጡም ማለት ነው።