በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ር/አ/ደ/ሰ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ - ኮሎኝ
73 subscribers
883 photos
40 videos
11 files
163 links
ይህ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል (ኮለን ሚካኤል) ቤተክርስትያን ድምጽ ነው።
Download Telegram
የኅዳር ሚካኤል በዓለ ንግሥ ጥሪ
ኅዳር ፲፪ በዓለ ሢመቱ ለቅዱስ ሚካኤል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !?
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”

(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡

ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ !?
በዓታ ለማርያም ወስተ ቤተመቅደስ

ታኅሣሥ 3 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው፡፡ እንኳን አደረሰን ?

ማርያም የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ማሪሃም/ሚርያም/ሲሆን ትርጉሙም/እመ ብዙኃን/ የብዙዎች እናት ማለትነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ ቅድስት ሐና አባቷ ደግሞ ቅዱስ ኢያቄም ይባላሉ፡፡ ወላጆቿ ልጅ በማጣት ምክንያት ለብዙ ጊዜ ቆይተዋል፤ በዚህ ቆያታቸው ፈቃደ አግዚአብሔርን በመጠባበቅ በደጅ ጥናት ነበር፡፡

በጊዜው መካንነት አንደ ነውር ተቆጥሮ ከማኅበረሰቡ የሚያስገልል አንገት የሚያስደፋ ፤ በቤተ አግዚአብሔርም ከምእመናን ተቀላቅሎ አምልኮተ አግዚአብሔርን ለመፈጸም የኀጢአት ምልክት ነው ተብሎ የሚያሳፍር ቢሆንም ቅሉ በመሐከላቸው ያለው ፍቅር ፈጽሞ አልቀነሰም አንድም ቀን አግዚአብሔርን አማረውት አያውቁም በተስፋ የእግዚአብሔርን ሥራ ይጠባበቁ ነበር አንጂ ዕለት ተዕለት ልመናቸውም የምትሠጠንን ልጅ መልሰን ላንተ እንሰጣለን ነበር፡፡

እግዚአብሔር አምላክም ከልብ የሆነ ልመናቸውንና ስእለታቸውን ሰምቶ ልጅን ሠጣቸው፡፡ ይህች ብላቴና የተሠጠችው ለጊዜው በደጅ ጥናት በልመና ለእናት ለአባቷ ይሁን አንጂ ፍጻሜው ግን ለአዳምና ለልጆቹ ለፍጥረተ ዓለም ሁሉ የተሰጠች ናት፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፡፡

ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላት ግን ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ ትውጣልን በማለት አይሁድ በጠላትነት ተነሡባት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን ጠየቃት «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡

እርሷም «ከእግዚአብሐር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናት አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትራቸውን ሰብስበህ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይ አድረህ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጣው ብሎ ምልክትም እሳይህአለው ብሎ ነገረው፡፡ እርሱም እንዳለው አድርጎ በማግሥቱ በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት፤» የሚል ጽሑፍ አገኙ፤ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋለች፤ በዚህ ምክንያት ዮሴፍ እንዲጠብቃት ተወሰነ፡፡

ከዚህም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቤተ መቅደስ ወጥታ እስከተሰደደችበት ወራት ድረስ በዮሴፍ ቤት ኖረች፡፡

እመቤታችን በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ከተወለደችበት ዕለት ግንቦት ፩ ቀን ጀምሮ በወላጆቿ ቤት ለሦስት ዓመት ከኖረች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

ምንጭ፡- ነገረ ማርያም (መ/ር ሶሎሞን መኩሪያ 2015 ዓ.ም)
-መዝገበ ታሪክ ቊጥር ፩ (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)