አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.15K photos
168 videos
14 files
771 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ ክብር ይገባካል👆



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወጣቱ አጥቂ የሙከራ ዕድል በማግኘቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያያመራ እንደሆነ ተገልጿል!

ከሐዋሳ ከተማ የታዳጊው ቡድን እስከዋናው ድረስ መጫወት የቻለው እና ሁለት ድንቅ አመታትን በቡናማዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለው የመስመር አጥቂው መስፍን ታፈሰ የፊታችን አርብ ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ወጣቱን የመስመር አጥቂ ወደክለባቸው የጋበዘው ክለብም ፖሎኩዋኔ ሲቲ ሲሆን ለወጣቱም የአንድ ሳምንት የሙከራ ጊዜ እንደሰጡት ተገልጿል።

ሐምሌ 01/2016
ሸገር ስፖርት አሬና!



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አብዱልከሪም🌟😍

መልካም ቀን ቤተሰብ💛🤎

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ

💛@coffeefc🤎
💛@coffeefc🤎
ደምህ ቡኒ 👆👆ሲሆን የሚትደሰተው ደስታ🤌🥰
የዋንጫው ባለቤት👏👏👏
🏆🏆🏆🏆🏆
ኪያር ጀግናው🔥💪💪ደስታው እንደቀጠለ ነው.......

መልካም ቀን ቤተሰብ💛🤎



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የውድድር_አመቱ_4_ተኛ_ዋንጫ
በድሬዳዋ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ እየተካፈለ የሚገኘ #የኢትዮጵያ_ቡና ሴቶች ቡድናችን ዛሬ እንጦጦ ሽሮሜዳን በማሸነፍ የክልል ክለቦች ሻምፒዮናን ዋንጫ መብላት ችለዋል።
#የዋንው ቡድናችን የጥሎ ማለፍ ዋንጫን
#በሴቶች የአዲስ አበባን ዋንጫ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና
#የተስፋው ቡድናችን ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ኢትዮጵያ ቡና መካከል ነሐሴ 5/2016 አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#48_ዓመታትን_ለፍትሃዊ_እግር_ኳስ_የቆመ_ክለብ

ከንጋት ኮከብ እስከ ኢትዮጵያ ቡና በዘለቀባቸዉ ባለፉት 48 ዓመታት ለእግር ኳስ ስፖርት ዕድገት ፣ለዘመናዊነትና ለፍትሃዊነት የታገለ ግንባር ቀደም ክለብ ነው።

ዘመናዊ የክለብ አደረጃጀትን ዕዉን በማድረግ ፣የመጀመሪያው ህጋዊ የደጋፊዎች ማህበር በመመስረት፣ የራሱን ወጪ በአጋሮችና በደጋፊዎቹ በመሸፈን ለሌሎች አርአያ መሆን የቻለ ኢትዮጵያዊ ክለብ ነዉ።

ገና ከምስረታው ዘር ቀለም ሳይለይ፣ በአካባቢ እና በክልል ሳይወሰን፣ ሁሉን ባቀፈ፣ ለሁሉም የሆነ፤ የስፖርት ለሁሉም መርህ ተከትሎ የተመሠረተ ስፖርት ክለብ ነዉ። ለዚህም ነዉ የኢትዮጵያ ቡና በሄደበት ባይተዋር የማይሆነው ። ለዚህ ነው ቡኒ እና ብጫ ቀለማት በአራቱም ማዕዘናት የማይታጡት።

የኢትዮጵያ ቡና መሠረቱ እና የታነፀበት ማዕዘን ፍትሃዊነት እና ፍትሃዊነት ብቻ ነዉ። የኢትዮጵያ ቡና ህልሙ በውድድር የሚገኝ ድል፣ በፍትህ የሚዳኝ ኳስ፣ በህግ የሚመራ እግር ኳስ ዕውን ሆኖ ማየት ነዉ።

ነገር ግን በእነዚህ ዓመታት የገጠመው መገፋት፣አድሎ እና ጫና ነበር። ውብ ጨዋታ እየተጫወተ ውጤት አጥቷል። ድንቅ ተጨዋቾችን እያፈራ ዕዉቅና ተነፍጓል። የሜዳውን ድባብ የማያሞቅ ደጋፊው ያለ ጥፋት ታስሯል፣ ተደብድቧል...መስዋዕትነት ከፍሏል። ለሀገራችን እግር ኳስ ዋጋ የከፈሉ አመራሮቻችን ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል።

በአጠቃላይ ቡና በዕድሜ ከዋንጫው በላይ መከራዉ፣ ከድሉ በላይ በደሉ በዝቶበት ተስፋ ሳይቆርጥ በስፍራው የቆየ ክለብ ነው። በጊዜያዊ ድልና ዋንጫ ሳያሳብብ በህይወት ዘመን ፍቅር የታሰረ፣ ከዓመት ዓመት እየበዛ የሚሄድ ደጋፊ ባለቤት ነዉ። ከግል ችግራቸው ይልቅ ለክለባቸው ህልውና የሚተጉ አጋሮች እና ደጋፊዎች ያሉት ክለብ በመሆኑ አስቸጋሪ ጊዜያትን ሁሉ እያለፈ ዛሬ ላይ የደረሰ፣ነገም የሚቀጥል ፣ኢትዮጵያን ያስቀደመ ኢትዮጵያዊ ክለብ ነዉ።

ክለባችንና የክለባችን የቦርድ አመራሮች የኢትዮጵያ እግር ኳስ እና ተጨዋቾች ዓለምአቀፍ እይታ እንዲኖራቸው፣ሊጉ ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ባለፉት አራት አመታት በታሪክ የሚዘከር ሥራ ሠርተዋል።

እናም በነዚህ ዓመታት የሊጋችን ተፈላጊነት ፣የክለቦቻችን ገቢና ተመልካች ቁጥር ከፍ ብሏል። የዳኝነት እና አጠቃላይ የአመራር ሥርዓቱ ለሁሉም ግልጽ በመሆኑ ክለባችን እንደሌሎቹ ሁሉ ተጠቃሚ እና ደስተኛ ነዉ።

በተጠናቀቀው የዉድድር ዓመት በሶስተኛ ደረጃ ያጠናቀቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ዋንጫን ለስድስተኛ ጊዜ አሸንፏል። በዉድድር ዘመኑ ደጋፊዎቻችን በጨዋነት፣ክለባችን የሚደርሱበትን ጫናዎች በትዕግሥት አሳልፏል።

ያም ሆኖ ባለፈው እሁድ በታላቅ ድምቀት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የኢትዮጵያ ዋንጫን በተመለከተ በተጋጣሚው ክለብ በአንዳንድ ወገኖች በኩል የሚነዙ አሉባልታዎችን ክለባችን በጥሞና ሲከታተል ቆይቷል። በእርግጥ ሽንፈትን በፀጋ መቀበል ከባድ በሆነበት ውስጥ ተሸናፊው ቡድን ሊሰማዉ የሚችለዉን ስሜት መገንዘብ ብንችልም ክለባችን ያለ ግብሩ ስሙ ሲጎድፍ፣ ያለ ባህርይው ስም ሲሰጠዉ ማየት ግን ያማል። በዕለቱ የነበረው ዉድድር በሚመለከታቸው አካላት በአግባቡ ተመርቶ የክለባችን አሸናፊነት የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ ቡና በአድሎ ዋንጫ እንዳነሳ ተደርጎ የሚናፈሰዉን በሬ ወለደ ውሸት አጥብቀን እናወግዛለን።

እግር ኳሱን የሚመረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጉዳዩ ላይ ተጨባጭ ማስረጃዎችን በማጣቀስ መግለጫ መስጠት እንዳበት ክለባችን ያምናል። ዛሬ ክለባችንን በክፉ ስም የሚያነሱ ክለቦች ባሉባቸው ዞኖችና ክልሎች በአግባቡ መጫወት እና ደጋፊዎቻችን በነፃነት ክለባቸውን መደገፍ ምን ያክል ፈተና እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ።

የኢትዮጵያ ቡና ዕድሜ ዘመኑን ለፍትህ የታገለ፣ ፈተናዎችን የተጋፈጠ፣ አድሎኣዊነን የሚታገል እና በጥረት ብቻ ዉጤታማ መሆንን የሚያምን ያንን በተግባር ያረጋገጠ ክለብ ነዉ።

መላው ደጋፊቻችን አሁን ላይ በክለባችን ላይ የተቃጣውን ስም ማጥፋትና በሐሰት ላይ የተመሰረተ ክስ በመጋፈጥ ትክክለኛ ማንነታችንን እንድታስመሰክሩ ጥሪ እናቀርባለን። የሚመለከታቸው አካላትን ተገቢውን ፍትህና ፍርድ እንድትሰጡ ብሎም የእግር ኳሳችንን ዕድገትና ስፖርታዊ ጨዋነትን እንዲያስከብሩ በትህትና እንጠይቃለን። በተረፈ ቡና ሁልጊዜም ለመማር፣ ለለዉጥ ብሎ ፍትህ የሰፈነበት እና ዘመናዊ የእግር ኳስ ዉድድር እንዲኖር ይተጋል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከያ ተደረገ

የ2017 የውድድር ዘመን የዝውውር ጊዜ ሐምሌ 15/2016 እንደሚከፈት ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ሆኖም ቀኑን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዲሱ የዝውውር መጀመርያ ቀን ከሰኞ ሐምሌ 8/2016 ጀምሮ እንዲሆን ተወስኗል።



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ቡና ሰኔ 30/2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል ሆኖም በጨዋታው ላይ በርካታ ድራማዊ ክስተቶች ተፈጥረው ተመልክተናል። በጨዋታው ላይ የነበሩ የዳኝነትም ሆነ የደጋፊዎችን ችግር አስመልክቶ እግርኳስ ፌዴሬሽኑ መርምሮ ውሳኔ ይሰጥበታል ብለንም እናምናለን።

ኢትዮጵያ ቡና የበደልን ብዛት ግፍን ተቋቁሞ ከንጋት ኮከብ እስከ ኢትዮጵያ ቡና አልወድቅም ብሎ ፀንቶ የቆሞ ለእውነተኛ ፍትህ እና ለንፁህ እግርኳስ የሚታገል ግንባር ቀደም ስፖርት ክለብ ነው።

ኢትዮጵያ ቡና በዘር በጎሳ በአካባቢ ያልተደራጀ በውብ እግርኳሱ የሁሉንም የሃገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች ልብ ያሸፈተ በብሄራቸው በዘራቸው በአካባቢያቸው የተቋቋሙ በርካታ ክለቦች እያሉ የሚኖሩበት ርቀት ሳይገድባቸው ልባቸውን ውብ እግርኳስ ለሚጫወተው እና ለዘመናት በበደል በግፍ በሴራ በርካታ ዋንጫዎችን ለተነጠቀው ሁሌም ለመልካም የስፖርት አስተዳደር ለሚታትረው ኢትዮጵያ ቡና አስረክበዋል!!

ከእሁዱ የጨዋታ መጠናቀቅ በሁዋላ አንዳንድ የወላይታ ደጋፊዎች እና ሌሎች የተለየ አላማ ያላቸው ግለሰቦች የክለባችንን ስም በማጉደፍ ላይ ይገኛሉ እኛም ነገሩን ተመልክተን እግርኳስ ስሜታዊ የሚያደርግ ስፖርት ስለሆነ ከዛ ስሜታቸው ሲወጡ ነገሩን ይተውታል ወይም አስተውለው ያስብቡታል ብለን ዝምታን መርጠን ቆይተናል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ አፀያፊ ስድቦችን የተሰደበ ደጋፊ የለም እኛ ግን ነገሩን ጎትተን ወደ ሌላ አቅጣጫ ወስደነው አናውቅም!! የወላይታ ዲቻውን ግብ ጠባቂ የተወሰኑ ደጋፊዎች ሊስትሮ አሉት ብሎ የነገሩን አቅጣጫ ወደ ዘረኝነት መጎተት ለምን እንደተፈለገ ግልፅ ባይሆንልንም ሊስትሮ የሚለው ቃል የስራ እንጂ አንድን ብሄር አሳንሶ የሚያሳይ ወይም የሚያንቋሽሽ አይደለም!! በዚህ ሙያ ውስጥ ደግሞ በርካታ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ሰርተው አልፈዋል እየሰሩም ይገኛሉ ቃሉ የወላይታን ማህበረሰብ ብቻ የሚወክልም አይደለም።

ሌላው ነገር ለምን በረኛው ብቻ ተሰደበ ሌሎቹ የወላይታ ተወላጅ የሆኑ የዲቻ ተጫዋቾች ምን አልተሰደቡም? ነገሩ የዘረኝነት ከሆነ ማለት ነው ነገር ግን ቢኒያም ደጋፊው ላይ ላደረገው ነገር ብቻ ደጋፊው ምላሽ ሰጥቶታል እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ለሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ትልቅ አክብሮት ያለው በስታዲየም ውስጥ ከሚደረጉ ብሽሽቆች በዘለለ ሌላ አላማ የሌለው የማንም መጠቀሚያ ያልሆነ ንፁህ እግርኳስን ብቻ ብሎ የመጣ ስርአት ያለው እግርኳስ ተመልካች ነው።

#ኢትዮጵያ_ቡና_ለዘለዓለም_ይኑር 👆



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዳኝነቱ ነገር

እግር ኳስ ላይ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት አይሰጥም አንዴ ብለን እራሳችንን እስክንጠራጠር ድረስ አዋቂውም አላዋቂውም እየመጣ እኝኝ ይልብናል እውነታው ግን ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምቶቹ ላይ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሰራ ገለልተኛ ለሆነ እግር ኳስ ተመልካች ሁሉ ግልጽ ይመስለኛል።

ጨዋታው ላይ አንዳንድ አወዛጋቢ ውሳኔዎች ሊኖሩ ይችላል ለአብነት ያህልም ዲቻ ላይ የተሻረው ኳስ በቡና በኩል ደግሞ ሶስተኛ ፍፁም ቅጣት ምት መከልከሉ እንዲሁም ያላግባብ ዱላ ቀረሽ ንትርክ ያረጉት ተጨዋቾች በዝምታ መታለፋቸው አስገራሚ ነበር።

ነገር ግን እነዚህን ደካማ ጎኖች በመጠቀም ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና በማይታወቅበት በሌለበት ስም ለመስጠት የተኬደው ርቀት ያስተዛዝባል።


አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ

💛@coffeefc🤎
💛@coffeefc🤎
የ CAF confederations cup የኢትዮጵያ ቡና ከኬኒያው Kenya police ጋር ተደልድሏል።
የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ የግብፁን ዛማሊክ የሚገጥም ይሆናል።
ውድድሮቹ በAug 16 እና በ Aug 18 መካከል ይደረጋሉ።
የኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያውን ጨዋታ ወደ ኬንያ አቅንቶ የመጀመሪያውን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።
#Ethiopia_bunna_fc
#ኢትዮጵያ_ቡና
#ቡናችን
#ኢትዮጵያ_ቡና_ህዝባዊ_ክለብ



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች

በቅንነት ስልካችሁ ላይ ላለ 10 የቡና ደጋፊ ይሄንን ፖስት share በማረግ ቻናሉን ትልቁ የእግርኳስ ክለብ ቻናል እናርገው

ለመቀላቀል
👉 @coffeefc
👉 @coffeefc
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኢትዮጵያ ቡና ጎል & ቪዲዮ ቻናል (Leo)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አርባምጮች እናመሰግናለን
እግርኳስ የሚያቅ እንደዚ ነው

https://t.me/+ENTsdkfDpSZhNmRk
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በ2016ዓ.ም የውድድር ዓመት በተሳተፈባቸው ውድድሮች አራት ዋንጫዎችን ማሳካቱ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን የኢትዮጵያ ዋንጫ
የኢትዮጵያ ቡና U-20 ቡድን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የኢትዮጵያ ቡና ሴቶች ቡድን የአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዝዮን ሻምፒዮን እና የክልል ከተሞች ውድድር ሻምፒዮና ሆነው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል።
በአሰልጣኝ ቶሎሳ ቢርቢርሳ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ቡድን ባለው ዕሮብ የክልል ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታቸውን ሁሉንም በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋገጡት ሲሆን፤ ዛሬ ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በሚደረገው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ የሻምፒዮናነታቸውን ዋንጫቸውን በክብር ያነሳሉ።

#Ethiopiabunna #football #Ethiopiancoffeefc



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🚨The player transfer window is open

🤝የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ተከፍቷል!! ክለባችን የሚፈፅማቸውን ዝውውሮች እየተከታተልን በፍጥነት የምናደርሳችሁ ይሆናል👆

#Ethiopiabunna #football #Ethiopiancoffeefc



አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️  @coffeefc  💛🤎

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና ክለቦች መካከል መካሄዱ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር እና ሥነ ስርዓት ኮሚቴ በዕለቱ በተካሄደው ጨዋታ ጨዋታውን የመሩት የጨዋታ አመራሮችና የውድድር አመራር ያቀረቡትን ሪፖርት አይቶ በመርመር ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

ምንጭ :- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

➡️  @coffeefc  💛🤎
➡️ 
@coffeefc  💛🤎