አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
208K subscribers
6.31K photos
265 videos
15 files
988 links
ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።


መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
የትውልድ ቅብብሎሽ👆

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
18
አልማዝ ሆማ - ⚽️
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዛሬ ላለበት ታላቅ የደጋፊ መሰረት እንደ አልማዝ (አልማዞማ) ያሉ የቁርጥ ቀን ልጆች የከፈሉት መስዋዕትነት ትልቅ የታሪክ ድርሻ አለው።

አልማዞማ ክለቡ ገና በሠራተኛ ማህበር ደረጃ በሳሪስ አካባቢ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በጽናት ከሚደግፉ ሴቶች መካከል ቀዳሚዋ ናት። በወቅቱ በሳሪስ "ቀይ አፈር" ሰፈር ውስጥ ቡድኑ ሲያሸንፍ እንደ ሰርግ በሚደመቀው ጭፈራ ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ትታወቃለች።

ለክለቧ ያላትን ጥልቅ ፍቅር ለመግለጽ "ትዳሬ ቡና ነው" የሚል መፈክር ያላትና በቡንዬ አርማ ፍቅር የተለከፈች ቆራጥ ደጋፊ ናት።

በስታዲየም ለሚደረጉ ጨዋታዎች መግቢያ ገንዘብ ሲያጥራት፣ "ቆራሌው" በፉጨት በመጥራት የቤት ውስጥ ዕቃዎችን በመሸጥ ለቲኬት መግዣ ትጠቀም ነበር።

በክለቡ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚ የሚባለው ተግባሯ፣ ገና አራስ ሆና ልጇን ለጎረቤት አደራ ሰጥታ የቡድኑን ጨዋታ ለመመልከት ወደ ድሬዳዋ መጓዟ ነው።

ይህ ለክለቧ ያላት ከልክ ያለፈ ፍቅርና ለጨዋታው ስትል ያደረገችው ጉዞ፣ በወቅቱ ከባሏ ጋር እስከመለያየት (ፍቺ) አድርሷታል።

አራስ ልጇን ጥላ ድሬ የተገኘች፣
"ትዳሬ ቡና ነው" ብላ የቆረጠች።
የታሪክ ማህደር ነሽ የጽናት መማሪያ፣
አልማዝ የቡናችን የፍቅር አውድማ።

ትላንትን አንረሳም ለጀግኖቻችን ክብር እንሰጣለን! 🤎🙌
10
If there is a real channel buyer, contact me.

👉 @Bunnacoffee12
2
• ሻሾ/ አፍሮ በሳሪስ አካባቢ በሚገኙ የቡና ደጋፊዎች ዘንድ እንደ አንዱ ደጋፊ የሚቆጠርና እጅግ ተወዳጅ የነበረ ፍየል ነው። ቡና አሸንፎ በሚመጣበት ወቅት ደጋፊዎቹ እሱን በመያዝ አብረውት ይጨፍሩ ነበር።

ይህ ፍየል ለየት የሚያደርገው ቢራ መጠጣቱ ነበር። የቡና ደጋፊዎች ቢራ ይጋብዙት የነበረ ሲሆን፣ ቢራውንም በጠርሙስ በአፉ ገልብጦ የመጠጣት አስገራሚ ችሎታ ነበረው። እንዲያውም "አራት እግር ስላለው ሰክሮ አይወድቅም" እየተባለ ይቀለድበት ነበር።

ሻሾ የሰራተኛውን የደሞዝ ቀን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። በዚያ ቀን ደጋፊዎቹ ወደሚሰበሰቡበት ቦታ በመምጣት አብሯቸው ይውላል።

በሳሪስ አካባቢ በሚገኝ አንድ የታወቀ መጠጥ ቤት የፓርኪንግ ቦታ ላይ ይተኛና፣ መኪና ይዘው የሚመጡ ሰዎች ካልጋበዙት አይነሳም ነበር። የሚጋብዘው ሰው ከመጣ ግን ተነስቶና ተለጣጥፎ (ስትሬቺንግ ሰርቶ) ከሰውየው ጋር አብሮ ይገባል።

ፍየሉ በህይወት ቢኖር ኖሮ ደጋፊዎቹ ይዘውት ስታዲየም ድረስ ይመጡ እንደነበር ይነገራል። ዛሬ ላይ ሻሾ በህይወት ባይኖርም፣ በሳሪስ ደርቢና በቡና ደጋፊዎች የደስታ ጊዜያት ውስጥ ስሙ ሁሌም የሚነሳ የታሪካችን አካል ነው

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
9
የቡናማዎቹ የመጀመሪያ ሴት ደጋፊ ዮርዳኖስ ከበደ! ☕️👑
በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ታሪክ ውስጥ ስሟ በወርቅ ቀለም ሊጻፍ የሚገባው የዮርዳኖስ ከበደ ታሪክ እጅግ መሳጭና ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ነው! ዮርዳኖስ ከድርጅቱ (ከቡና ቦርድ) ሠራተኞች ውጭ ክለቡን መደገፍ የጀመረች የመጀመሪያዋ ሴት ደጋፊ በመሆን ታሪክ ሰርታለች።

የዮርዳኖስ ታሪክ ልዩ የሚያደርገው በወቅቱ እሷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርተኛና የብሔራዊ ቡድን ዋናተኛ መሆኗ ነበር 🏊‍♀️🥇። የሚከፍላትና የሚያስተዳድራት ንግድ ባንክ ቢሆንም፣ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በሚጫወትበት ጊዜ እሷ ግን አቋሟን ሳትደብቅ በአደባባይ ለምትወደው የቡና ቡድን ድጋፏን ትሰጥ ነበር። ይህ ለፍቅር የታመነ ማንነቷ በብዙዎች ዘንድ እንድትደነቅ አድርጓታል።
ዮርዳኖስ ብቻዋን ከመደገፍ ባለፈ፣ የሚከተሉትን ታላላቅ ስራዎች አከናውናለች፦

• ከየሰፈሩ ሴቶችን በማሰባሰብ የደጋፊነትን ባህል በማስፋፋትና የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውታለች 👯‍♀️🥁

• ላበረከተችው ለዚህ ታላቅ የፍቅር መስዋዕትነት ክለቡ ባዘጋጀው ዓመታዊ በዓል ላይ ተገኝታ የክብር ሽልማትና ከፍተኛ እውቅና ተሰጥቷታል።

ለቡና አርማ የነበራት ጥልቅ ፍቅር ዛሬም ድረስ በታሪክ ማህደር የሚታወስ ይሆናል የዛሬው የቡና ደጋፊ ድምቀትና በስታዲየም የሚታየው የሴት ደጋፊዎች ብዛት መሰረቱ እንደ ዮርዳኖስ ያሉ የጽናትና የፍቅር ባለቤቶች ናቸው! 🙌🤎☕️

ትላንትን አንረሳም፣ ለጀግና ደጋፊዎቻችን ክብር እንሰጣለን! ☕️

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
6
🟤🟡 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የደርቢ ጨዋታ አሸንፈናል! 💪💪
ቅዱስ ጊዮርጊስ 1️⃣ - 2️⃣ ኢትዮጵያ ቡና
⚽️ዮናስ ንጉሴ
⚽️ ዮሀናን ኢሳያስ
⏭️ ቀጣይ ጨዋታ
ወልቂጤ ከተማ 🆚 ኢትዮጵያ ቡና
እሁድ 13/07/2018 9:00 ቡራዩ ስታድየም

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
15
☪️🕌ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለውድ የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ!!

🤎💛የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ!

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
8
📢 ነገ ቅዳሜ ከ 3:00- 5:00 በተወዳጁ የራድዮ ጣቢያ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 አቦል፣ቶና ፣ በረካ በተሰኘው የክለባችን የራድዮ ፕሮግራም ላይ የቀድሞ የክለባችን ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እንግዳ ሆነው ስለሚቀርቡ ፣ ውድ የክለባችን ደጋፊዎች እንድንጠይቅላችሁ የምትፈልጉት ጥያቄ ካለ በአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ ወይም በስልክ ቁጥር 0974380303 መጠይቅ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን! 👆🏾👆

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
👍62
🟡 “የአዲስ አበባ የሴቶች ከፍተኛ ዲቪዝዮን የጨዋታ ውጤት
🟤ኢትዮጵያ ቡና 10-0 ቶፕ ያንግ
ጎሎቹን
3x⚽️ ማርያማዊት ያሬድ
2x⚽️ ሳምያ ሬድዋን
⚽️ እድላዊት ከባዱ
⚽️ ወይንሸት ፉሮ
⚽️ ሳራ ጆርጋ
⚽️ ነፃነት ሲሳይ
⚽️ማርያማዊት ፋንቱ አስቆጥረዋል!

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
13🔥2
Audio
አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
👍3
🟤🟡 የሸገር ደርቢ ተስተካካይ ጨዋታ መርሃ ግብር
እሁድ ሚያዝያ 18/2018 ፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም
09:00 እንደሚደረግ ታውቋል!!!

Via ethiopianpremierleagues.c

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
25😍5
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ውጤት !

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
12
አንቀርም!
አብሮ መዝለቅን፣ነገን በተሻለ ማለምን፣ትናንትን ማክበርን እንጂ መለያየት የለም። በደም ውስጥ ሰርጾ የገባ የነፍስ ዋጋ ያህል በከበረ የህይወት ጉዞ ውስጥ መቀጠል እንጂ መቋረጥ አይኖርም።
መጋቢት 30 ቀን 2018
በአዲስ አበባ ስታድዮም

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
11👍4
😍የክለባችን የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ የሆነው ቡናማው አሚር ተሞሽሮዋል !👫💍

ያማረ የስኬት የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ💍

መብሩክ 👆

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
25🔥1
👆🏻ሚስጥር አለው ቡና📝
እንደወይኑ ፍሬ ጨምቀን እንደያዝነው ይጣፍጣል ቡና ምን ጊዜም ጥኡም ነው ጠላት ቢያሴርብን ቢቆፍርም ጉድጓድ  ግዞትን ሊግተን በሸር ቢንጎራደድ የኛ ቡና አይሞት አይፈራርስ ከቶ ይወድቃል ይደክማል ብሎ የጓጓ ሰው ቃዋን አያውቀውም እውቀትም ያነሰው መስከረም እንዳለ እንደ አደይ አበባ ገና ያምርበታል ይቆነጃል ቡና ቡና በሌለበት አለም አትደምቅም ቡና አደገኛ  ነው ስንል ሚስጥር አለው ገፍተህ የማትጥለው ፅኑ ግድግዳ ነው ጠልተህ የማትጠላው የፍቅር ሙዳይ ነው ሸሽተህ ማታመልጠው ከብርሀን ፈጣን ነው.....✍🏻

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
👍82🏆1
💛 ቀጣይ ጨዋታ 🤎
🆚 ኢትዮጵያ መድን
🏆 ethiopianpremierleagues.c
🗓️ ቅዳሜ 26/07/2018
🕘 10:00
🏟️ አበበ ቢቂላ ስታድየም
🎫 ትኬት http://ticket.ethiosport.pro Away 🔴
#ethiopian_coffee_sc #ቡና_ገበያ #Next_Match

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
12
🟤🟡 ከተማው የናፈቀው ድባብ 🔥🔥🔥
#ቡና_ገበያ #ቅዳሜ

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ
💛 @coffeefc 🤎
💛 @coffeefc 🤎
14