Code IT | Remote Work
1.95K subscribers
405 photos
72 videos
12 files
200 links
Exploring code, AI, remote work & building in public. Join the lab and grow with us!
Download Telegram
[ Breaking ] #space #technology

ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ እና 10 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በሚያወጣው የናሳው ጄምስ ዌብ የተሰኘ ስፔስ ቴሌስኮፕ የተነሳ ፎቶ ዛሬ በዋይትሃውስ የተለቀቀ ሲሆን፣ በስፔስ ምርምር ታሪክ ወደ ህዋ በጥልቀት በኢንፍራሬድ የተነሳ ቁልጭ ያለ የመጀመሪያው የአጽናፈ ዓለም ምስል ሆኗል።
የዌብ ቴሌስኮፕ የመጀመሪያ ጥልቅ መስክ ተብሎ የተጠራው ይህ የአጽናፈ ዓለማችን የጋላክሲዎች ጥርቅም ምስል “SMACS 0723” ሲባል፣ የሰው ልጅ በታሪኩ አጽናፈ ዓለምን በእድሜ ርዝመትም ሆነ በርቀት በጥልቀት ያየበት እና አጽናፈ ዓለም ወደተፈጠረበት መነሻ ሰዓት አካባቢ የወሰደን የመጀመሪያው ታሪካዊ ምስል ነው ተብሎለታል።

ምስሉ እጅግ በርቀት ያሉ የጋላክሲዎች ጥርቅም ከ4.6 ቢሊዮን ዓመት በፊት የነበራቸውን ይዘት የሚያሳይ ሲሆን ይሄ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ጋላክሲዎች እጅግ ሩቅ ከመሆናቸው የተነሳ ከነሱ ላይ የሚያንጸባርቀው ብርሃን በህዋ ውስጥ ተጉዞ ወደ ቴሌስኮፑ ሌንስ ደርሶ ፎቶ እስከሚነሳ ድረስ የሚወስድበት ጊዜ በቢሊዮኖች ዓመታት የሚቆጠር ስለሆነ ነው።

ለንፅፅር ያህል፣ ግዙፉን አጽናፈ ዓለም እጅግ በጥቂቱ ወክሎ የሚያሳየው ይህ ምስል አንድ ሰው ከምድር ሆኖ እጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ መያዝ ይችላል ብለን ብናስብ የሚሸፍነው የሰማይ ክፍል አንዲትን እጅግ ደቂቅ የሆነች የአሸዋ ጠጠር የሚያህል ነው። ይህ የሚያሳየው የአጽናፈ ዓለምን ከአዕምሮ በላይ የሆነ ግዝፈቱን ነው።

Source: White House
#Daily_Tech_News
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
C RAM new military defence System can track and neutralize its target in blink of eyes.

#military #technology

▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu
@innovate_aastu
At the library in Utrecht,

Netherlands you can recharge your electric devices by cycling . 🔥


#technology #science
@innovate_aastu