#ቁጥር ⬆️
አሁን ላለው የሂሳብ ሳይንስ እንደ ስልጣኔ መጀመርያ የሚወሰደው የቁጥሮች መፈልሰፍ ነው።
ቁጥሮችን ሁልጊዜ እንጠቀማቸዋለን የተማረም ያልተማረም በተወሰነ መልኩ ነገሮችን መቁጠር ይችላል።
💡ነገር ግን ስለ ቁጥሮች ምን ያህል እናውቃለን?በርግጥ ቁጥር ማለቅያ የለውም ነገር ግን የሰው ልጅ የሚያውቀው ትልቁ ቁጥር ምንድን ነው ? ብዙዎቻችን እንደ ሚልዮን ቢሊዮን እና ትሪሊዮን ያሉ ቁጥሮች እጅግ በጣም ትልቅ እንደሆኑ እናውቃለን ለምሳሌ የኢትዮጵያ ህዝብ 114 ሚሊዮን አከባቢ ይደርሳል፤ የአለም ህዝብ ደግሞ 7.8 ቢሊዮን እንዲሁም የአለማችን ሀብታሙ ሰው Elon Musk ጠቅላላ ሀብት ወደ 12 ትሪሊዮን ብር ይደርሳል።
እኚህ እንግዲህ መደበኛው ሰው የሚያውቃቸው ቁጥሮች ናቸው። አሁን ደግሞ ተለቅ ያሉ ቁጥሮችን በምሳሌ እያየን ወደ ትልቁ የተባለው ቁጥር እናመራለን።
💡ከትሪሊየን ቀጥሎ ያለው ቁጥር ኳድሪሊየን ነው ይህም 15 ዜሮዎችን ያስከተለ ቁጥር ነው። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ አለም ላይ ያሉት ጉንዳኖች ቁጥር ወደ ኳድሪሊየን(1* 10^15) ይደርሳል።
💡ቁጥሎ ያለው ደግሞ ኩዊንቲሊየን (10^18) ይህም ፀሃይ ያለችበት የኛው ጋላክሲ (Milkyway) ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ 1 ኩዊንቲሊየን ኪሎሜትር ይረዝማል ቀጣዩ ቁጥር ደግሞ ሴክስቲሊየን(10^21)ነው።
💡በሚታየው ህዋ ውስጥ ያሉት ከዋክብት ብዛት ወደ 200 ሴክስቲሊየን ይሆናል ተብሎ ይገመታል።ቀጥሎ ያለው ቁጥር ሴፕቲሊየን (10^24) ነው። በምድር ውቅያኖሶች ውስጥ ያለው ውሃ በሙሉ ወደ መደበኛ ብርጭቆ እንጨምር ብንል ወደ 1 ሴፕቲሊዮን ብርጭቆዎች ያስፈልጉናል (አስቡት 1 ብላችሁ 24 ዜሮዎች) አሁን ደግሞ ብዙ ቁጥሮችን ዘለን Googol የተባለውን ቁጥር እንመልከት በተለምዶ የምታውቁት Google ስያሜውን ያገኘው ከዚህ ነው ይባላል። ይህ ቁጥር መቶ ዜሮዎችን ያስከተለ ነው (10^100) Googol እጅግ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በምድር ሆነ በጠፈር ውስጥ እሱን ተጠቅመን የምንገልፀው ምንም ነገር የለም። የጠፈር ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ አንድ ክብደቱ የኛን ጋላክሲ የሚያክል ብላክ ሆል ለመበስበስ(to decay) ወደ 1 Googol አመት ያስፈልገዋል።ሆንም ግን ይህ ቁጥር የአለማችን ትልቁ ቁጥር አይደለም።የሰው ልጅ ትልቅ ብሎ ማሰብ የቻለው ቁጥር Googol ዜሮዎች ያሉት ቁጥር ነው ይህም Googolplex (10^googol) ይባላል ።ይህ ቁጥር እጅግ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ በአዕምሮአችን ለማሰብ ይከብዳል አስኪ ከረዳችሁ በምሳሌ ላስቀምጥላችሁ፤ እንበልና በአንድ መፅሐፍ ላይ አንድ ሚሊዮን ቁጥሮችን ብትፅፉ Googolplex ጋር ለመድረስ ወደ googol መፅሐፍት ያስፈልጋችኋል የመፅሐፍቱ ክብደትም 400 ቢሊዮን ከዋክብትን ከያዘው የሚሊኪዌይ ጋላክሲ ክብደት ይበልጣል።አስቡት እንግዲህ ይህ ቁጥር እጅግ በጣም ትልቅ ነው ! ነገር ግን ይህ የቁጥር መጨረሻ አይደለም ይህ ቁጥር ምንም ያህል ቢተልቅ ከinfinity ይልቅ ለ0 የቀረበ ነው።
#numbers #maths #inspiration
▬▭▬▭▬▭▬▭
Follow us: YouTube, Telegram, Tiktok
@innovate_aastu

👍2😱2