የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ቢሮው መጪው የአደባባይ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር ተከብሮ እንዲልፍ በየደረጃው ከሚገኙ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ በዘርፉ ቁልፍ ተልዕኮ አፈፃፀም ለይ እና በመጪው የአደባባይ በዓላት ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ሃለፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ያላ ህዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልምና ባላፈው ዓመት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ወንጀል አንዳይከሰት ቀድሞ በመከላከል በሰራነው ስራ የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ የከተማችን ሰላም ማስቀጠል ችለናል፡፡ወንጀል ከግዜ ወደግዜ እየቀነሰ ቢሄድም አሁንም በከተማችን የወንጀል ድርጊቶች፤የጽንፈኞችና የጸረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴ ስለሚታይ ህብረተሰቡ ከሰላም ሰራዊት አባላት ጋር በመሆን የሚስተዋሉ ስጋቶችን በመለየት ግጭቶችን ማስወገድና በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ለማድረግ ሌት ተቀን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የውይይት መነሻ የሆነውን ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ሲሆኑ በ2016 በጀት ዓመት ማስፈንጠሪያ መሆን የሚችል ተግባር የተፈጸመበት ዓመት ስለመሆኑ፤በዘርፉ የበለጠ ውጤት እንዳይመጣ ያደረጉ ማነቆዎችን አንጥሮ በመለየት በልዩ ትኩረት መስራት ስለሚጠይቁ ወቅታዊ የፀጥታ ስራዎችና እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የፀጥታ አመራሩንና የሙያተኞችን ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ....ወዘተ ላይ ዝርዝር ማብራረያ ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ጠ/መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ፍቅሩ አለማሁ በበኩላቸው እንደተናገሩት በ2017 በጀት አመት ከተማችን ሰላም እንድትሆን ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን ሌት ተቀን መስራታችንን መቀጠል ይኖርብናል ካሉ በኃላ በተለይም በትምህርት ቤቶች አከባቢ ያሉ አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል፣ የኮሪደር ልማት እና የኢኮኖሚ አሻጥር ስራዎች መከላከል ላይ በትኩረት መስራትን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

በመጨረሻም የቢሮው የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ጠ/መምሪያ ወደፊት በጋራ በሚያሰሯቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመዋል፡፡
👍5
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የመስቀል በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

መስከረም 17/2017ዓ.ም

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የመስቀል ክብረ-በዓል ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ሀገራችንን በዓለም ከሚያስጠሩ በዓላቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በዩኒስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ዓለም አቀፋዊ ክብረ በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ስናከብር ኃይማኖታዊ ትውፊቱን እንደጠበቀ በአብሮነት፣በፍቅር፣በመተባበር፣ያለው ለሌለው በማከፈል ፣ሰላማቺንን በማስጠበቅ፣በዓሉ ሀገራችን በክብር እንዳስጠራ የምናስቀጥልበት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የሚፈጠሩ የደንብ መተላለፎችን ፣በመቆጣጠር፣በመከላከልና ህገወጥ ድርጊቶች ተፈፅመው ሲገኙ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከተማዋ ለነዋሪዎቾ ብሎም ለጉብኝት ለሚመጡ እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን እየሰራ ይገኛል፡፡

በአሉ ምክንያት በማድረግ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎችን በተለይም ህገወጥ እርድን በጋራ በመከላከል ጤናማ በዓል አንድናሳልፍ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

መልካም የመስቀል በዓል!

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር በለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
👍3
የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የአሰልጣኞች ሰልጠና መስጠት ጀመረ ።

20/01/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የስልጠና ዳይሬክቶሬት በ2017 በጀት ዓመት ለፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ አሰልጣኞች ለ5 ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮ/ር አህመድ መሐመድ አንደተናገሩት ስልጠናው የነባር ኦፊሰሩን አቅም ለመገንባት እና አዲስ ምልምል እጩ ኦፊሰሮችን ለማሰልጠን ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ሲሰጥ የዋለው የስልጠና ርዕስም "የሀገር ፍቅር ግንባታ" ሲሆን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአመራርና የአቅም ግንባታ ስልጠና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ካሳሁን መኮንን ቀርቧል።

የሀገር ፍቅር በአገልጋይነት የሚገልጽ ፍፁም ለዜጎችና ለሀገር ያለን ታማኝነት እና ብዝሀንነትን ማክበር እንዲሁም አንድነትን መፍጠር ለሀገር ሰላም አስፈላጊ መሆኑን በስልጠናው ለተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።

ሰልጣኞችም ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ላነሷቸው ጥያቄና አስተያየቶች በአሰልጣኙ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የእለቱ ስልጠና ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።
👍41
ኢሬቻ - ፈጣሪ ለድንቅ ሥራው የሚመሰገንበት በዓል

መስከረም 24/2017

"ኢሬቻ" ማለት ፈጣሪን (ዋቃ)ን ማመስገን ማለት ነው። ኢሬቻ ለምለም እና እርጥብ ሳር ተይዞ ፈጣሪ (ዋቃ) የሚመሰገንበት ሆኖ የበረከት፣ የመብዛት እና የመፍካት ሕይወትን የሚያመላክት ነው።

በዓሉ የምስጋና፣ የሰላም እና የይቅርታ መገለጫ ተደርጎም ይወሰዳል። የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ትቶ በንፁህ ልቦና ፈጣሪ ንፁህ ወዳደረገው የውኃ አካል ይኬዳል።

ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከክረምቱ የዝናብ፣ የብርድ እና የጨለማ ወቅት ወደ ብርሃናማው በጋ እንዲሁም ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው ፈጣሪው (ዋቃ) ምስጋና የሚያቀርብበት ትልቁ በዓሉ ነው።

በዓሉ መስከረም መጨረሻ ላይ የሚከበር ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብም ፈጣሪ (ዋቃ) ለሰጣቸው በረከት እና ላደረገለት ምሕረት ምስጋና የሚያቀርብበት ነው።

ማኅበራዊ ደረጃ እና የዕድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር እንደቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ማኅበረሰቡ ከየአካባቢው ተጠራርቶ በአካባቢው ወደሚገኝ ወንዝ (ውኃማ ስፍራ) በመትመም ለፈጣሪው (ዋቃ) ምስጋና ያቀርባል። እነዚህ የውኃ አካላት የተቀደሱ ናቸው ብሎም ያምናል።

በበዓሉ ላይ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች፣ ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ ታዳሚዎች፣ ቱሪስቶች እና የተለየዩ የብሔረሰብ ተወካዮች ይሳተፋሉ።

በዓሉ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እና በተለያዩ ሥርዓቶች ይከበራል። በተጨማሪም፣ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት በሚገኙበት የተለያዩ የዓለም ሀገራትም ጭምር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

በቢሾፍቱ ሆረ ሀርሰዲ እና በአዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓላት ላይ የሚሳተፉ ታዳሚያን እርጥብ ሳር በእጃቸው በመያዝ ወደ ሐይቁ ዳርቻ በመጠጋት ለምለሙን እና እርጥቡን ሳር በውኃ እየነከሩ ራሳቸው ላይ ይረጫሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ ውኃ ውስጥ ገብተው ይጠመቃሉ።

ኢሬቻ የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል ሲሆን በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱ ይነገራል።

“ሆረ ፊንፊኔ” የኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ሲከበር እንደቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በዓል በተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ከ150 ዓመታት በኋላ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ዳግም መከበር ጀምሯል።

በዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ።

በጥቅሉ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ የደረሱ አዝዕርት፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ለመሰብሰብ ዝግጅት የሚደረግበት እና በዚህም ሕዝቡ ደስታውን የሚገልጽበት ነው።

ኢሬቻ ፈጣሪ (ዋቃ) የሚመሰገንበት ብቻም ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ አዲሱን ብርሃናማ ዓመት በደስታ የሚቀበልበት በመሆኑ ሁሉም ቤተሰቦች፣ ጓደኛማቾች እና ዘመድ አዝማድ ከያሉበት ተጠራርተው በአንድነት፣ በፍቅር እና በደስታ የሚያከብሩት በዓል ነው።

በበዓሉ ላይ ልጃገረዶች እና ጎረምሶች በባህላዊ ልብስ አጊጠው ባህላዊ ጭፈራ እያሳዩ ይደሰታሉ፤ የተለያዩ ባህላዊ ዘፈኖችን እየተቀባበሉ ያሰማሉ።

በተለይም ምስጋና ወደሚያቀርቡበት ውኃማ ስፍራ ሲያቀኑ የተለያዩ ጣዕም ያላቸውን ባህላዊ ዜማዎች ያዜማሉ፤ በዚህም ለፈጣሪያቸው ምስጋናን ያቀርባሉ። በበዓሉ ላይ ወንድማማችነት፣ እርቅ እና ሰላምም ይንፀባረቅበታል።

ኢሬቻ ከበዓልነቱ ባለፈ በርካታ ቱሪስቶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ የአገርን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ያለው ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ ይነገራል።
👍41