የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የዒድ አል-አድሐ አረፉ በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-አድሐ/አረፋ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
የኢድ አል-አድሐ አረፉ በዓል የሰላም ፣የጤና ፣የደስታ፣የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንዲሆንልን እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በበዓሉ ወቅት በአብሮነት፣በመተሳሰብና ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ያለውን በማካፈል በአሉን በማክበር የተለመደው አብሮነቱን ሊያስቀጥል ይገባል ።
ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ስራ ላይ ሁሉም ዜጋ በንቃት በመሳተፍ አዲስ አበባ ከተማችንን የደንብ መተላለፍ የማይስተዋልባት፤ ለነዋሪዎቿና እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
በራሴ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤት ስም መልካም በዓል እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
ዒድ ሙባረክ!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ

👍1
ማስታወቂያ
ቀን፡- 10/10/2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሹፌርነት የስራ መደብ ላይ በቀን 27/09/16 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ መሰረት የተመዘገባችሁ አመልካቾች ለተግባር ፈተና ቅድመ ፈተና የተመለመሉ እና ለፈተና እንዲቀርቡ የተወሰነ በመሆኑ ረቡዕ በቀን12/10/16 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለፈተና እድትቀርቡ እንገልፃለን፡፡
የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ አመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።
1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ባሉ የሴት ባክ (setback) ፕላን ትግበራ ከመንገድ ያላቸው ርቀት መጠን በካቢኔ ወስኖ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል ።
ከዚህ በፊት የተወሰኑ የሴት ባክ ለማስተግበር፤ ሂደቱን ለማሳለጥ እና አገልግሎቱን ለማፍጠን የቀረቡ በደንብ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በጥልቀት ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
2. የመንገድ ዳር መብራት እና መሠረተ ልማቶች ለማስተዳደር የሚችል አስተዳደር ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን በዚህም የመንገድ ዳር መብራቶች እና መሠረተ ልማቶች ስንታንዳርዶችን ማውጣት፣ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
3. ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አደረጃጀት አሰራር ማሻሻያ ደንብን ካቢኔው መክሮበት አፅድቋል ።
በይዘቱም ከተማዋ ከጊዜው ጋር የሚመጥን የፅዳት አጠባበቅ አጠቃቀም እና የቆሻሻ አወጋገድ እና የተሸከርካሪ የመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የመንገድ ፍሳሽ አወጋገድ አለአግባብ የመንገድ ላይ የመፀዳዳት ተግባራትን እንዲጠበቁ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎች እና ተጥሰው ሲገኙ ለማስከበር ህገ ወጥ አሰራሮችን ለመቅጣት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎችን የያዘ ነዉ፡፡

👍10❤3