የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የዒድ አል-አድሐ አረፉ በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-አድሐ/አረፋ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
የኢድ አል-አድሐ አረፉ በዓል የሰላም ፣የጤና ፣የደስታ፣የፍቅር እና የመረዳዳት በዓል እንዲሆንልን እየተመኘሁ ህዝበ ሙስሊሙ በበዓሉ ወቅት በአብሮነት፣በመተሳሰብና ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ በማጋራት ያለውን በማካፈል በአሉን በማክበር የተለመደው አብሮነቱን ሊያስቀጥል ይገባል ።
ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ስራ ላይ ሁሉም ዜጋ በንቃት በመሳተፍ አዲስ አበባ ከተማችንን የደንብ መተላለፍ የማይስተዋልባት፤ ለነዋሪዎቿና እንግዶቿ ምቹ እንድትሆን እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
በራሴ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤት ስም መልካም በዓል እንዲሆንልን ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
ዒድ ሙባረክ!
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ

👍1