የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ “በህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችን እንከላከላለን” በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት አካሄደ

18/08/2016ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እና የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት በ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ እና በደንብ ቁጥር 150/2015 የአፈፃፀም መመሪያ ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ አከናወነ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ፅዱ እንድትሆን ሌት ተቀን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው ብለዋል።

አክለውም የ 2016 በጀት አመቱን ሲጀመር እቅዱን ለህዝብ በማስተቸት ወደ ስራ እንደገባ ገልፀው። ለባለስልጣኑ የጀርባ አጥንት የሆነውን የህብረተሰባችንን አስተያየት በመቀበል ስራዎችን ስንሰራ የቆየን ሲሆን በዛሬው ዕለትም በ9 ወራት ውስጥ ምን ተሰራ ምንስ ይቀረናል የሚለውን የምናይበት መድረክ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።


የባለስልጣኑን የሶስተኛ ሩብ ዓመትን የዕቅድ አፈፃፀም በእቅድ እና በጀት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ኮነሬል አድማሱ ተክሌ በበጀት ዓመቱ ከህብረተሰብ ጋር ተቀራርበን በመስራታችን ብዙ ለውጦች መምጣታቸውን ገልፀዋል።

ሌላው በደንብ ቁጥር 150/2015 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሰነድ ያቀረቡት የቅድመ መከላከል እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ናቸው ።

በቀረቡት ሁለት ሰነዶች ላይ ሀሳብና አስተያየቶች ከህብረተሰቡ የተሰጡ ሲሆን ስራዎችን በጋራ መስራት ለውጤት እንደሚያደርስ እና ይህንን ለማስቀጠልም ተቀራርቦ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ መስራት ከጀመርን በኋላ ለተቋማችን ትልቅ ኃይል ሆናችኋል ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የተናገሩት የውይይት መድረኩን ሲመሩ የነበሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ናቸው ።

ሌላኛው መድረኩን ሲመሩ የነበሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፋፉ እንዳሉት በዛሬው ውይይታችን ያየናቸውን ነገሮች ለሁሉም ህብረተሰብ ማድረስ እንደሚገባ እና ለከተማዋ ልማት እንዲሁም ለተቋሙ ራዕይ እና ተልዕኮ እንቅፍት የሚሆኑ ህገወጦችን ከእናንተ ጋር በመሆን እንታገላለን ብለዋል። ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየት ምላሽ የሰጡ ሲሆን የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3
አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ንግድ ቤቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች 3ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች በህጋዊ ንግድ ሽፋን የሚፈፀሙ አዋኪ ድርጊቶች እና ሌሎች ህገ ወጥ ተግባራት ለወንጀል መስፋፋት በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ከደንብ ማስከበር አባላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሩን ለማስወገድ እየሰራ ይገኛል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት  በተለያዩ ንግድ ቤቶች ላይ በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ተገኝተው እርምጃ እንደተወሰደባቸው እና  በህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳተፉ በርካታ ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ 

ሰሞኑንም በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች ፖሊስ እና የደንብ ማስከበር አባላትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ባከናወኑት ተግባር በህገ ወጦች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች 3ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር በማዋል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የማስወገድ ስራ ተሰርቷል፡፡

ድንገተኛ ቁጥጥር የተደረገባቸው እና ለወንጀል መስፋፋት መንስዔ የሆኑ ድርጊቶች ሲፈፀምባቸው የነበሩት
መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ፔንሲዮኖች፣ ማሳጅ ቤቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ)
👍5
“ንፁህ ከተማ - ጤናማ ማኅበረሰብ ለመገንባት”

ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የከተማ ንፅህና ከውበት ባለፈ በበርካታ መንገዶች ከህዝብ ጤና ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው።

ንፁህ እና ፅዱ ከተማ በሚተገብረው ከተማን ንፁህ በሚያደርጉ ተግባራት እና ፖሊሲዎች አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ማኅበራዊ ጤናን በማጠናከር ለነዋሪዎቹ ደኅንነት ቅድሚያ ይሰጣል።

ከመገለጫዎቹም መካከልም በቂ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና አገልግሎቶችን ለሁሉም ነዋሪዎች ዝግጁ እና ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም ንፁህ አየር፣ ውኃ እና የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን መገንባት ይገኝበታል።

ንፁህ እና ፅዱ ከተማ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ እና ባህላዊ ሁኔታዎች የእርስ በርስ መስተጋብር ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይነገራል።

የንፁህ ከተማ እና አካባቢ የጤና ጥቅሞች፦

1. የአየር ብክለትን መቀነስ - ንፁህ ከተሞች ዝቅተኛ የአየር ብክለት ያላቸው ሲሆን ይህም በአየር ብክለት ሳብያ ሊከሰት የሚችልን የመተንፈሻ አካላት ሕመም፣ የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች እንዲሁም ያለጊዜ የመሞት ዕድል እንዲቀንስ ያስችላል።

2. የውኃ ወለድ በሽታዎችን መከላከል - በንፁህ ከተሞች የሚተገበሩ የቆሻሻ አወጋገድ እና የንፅህና አጠባበቅ አሠራሮች የውኃ ምንጮችን ከመበከል ይከላከላሉ። ይህም እንደ ኮሌራ፣ ታይፎይድ፣ ትኩሳት እና ተቅማጥ ያሉ የውኃ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከል ያግዛል።

3. ወባን የመሰሉ ትንኝ ወለድ በሽታዎችን መቆጣጠር - ንፁህ ከተሞች እንደ ትንኝ እና ዝንብ በመሳሰሉ ነፍሳት አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ጠንካራ ቁጥጥር ያደርጋሉ።

ንፁህ ከተሞች ነፍሳቱ በከተሞች እንዳይራቡ የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ በበሽታዎቹ የመያዝ ዕድልን ይቀንሳሉ።

4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማስተዋወቅ - ንፁህ የሆነ ከተማ ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ማራኪ የሕዝብ ቦታዎችን በማቅረብ ይታወቃል።

ይህም ነዋሪዎች የእግር እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እና የተለያዩ ከቤት ውጪ የሚደረጉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል።

በዚህም ከመጠን በላይ ውፍረትን፣ የስኳር በሽታን እና ሌሎች ከአኗኗር ዘይቤ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሥር የሰደዱ ሕመሞችን ለመከላከል ይረዳል።

5. ለአዕምሮ ጤና - ንፁህ እና በጥሩ ሁኔታ የተያዘ የከተማ ገጽታ ከተሻሻለ የአዕምሮ ጤና ጋር ይያያዛል።

አረንጓዴ ቦታዎች፣ መናፈሻዎች እና ውበትን የሚያጎናጽፉ አካባቢዎች ጭንቀትን ይቀንሳሉ። ይህም ለአጠቃላይ ሥነ-ልቦናዊ ጤና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

6. የምግብ ደኅንነት እንዲኖር ያደርጋል - ንፁህ ከተሞች ተገቢ የምግብ ማከማቻ፣ አያያዝ እና አወጋገድን ጨምሮ ለምግብ ደኅንነት ቅድሚያ ይሰጣሉ።

በዚህም በምግብ እና በውኃ መበከል የሚከሰቱ በሽዎችን ለመከላከል ያግዛል።

7. የማኅበረሰብ ትሥሥር ይፈጥራል - ንፁህ ከተማ በነዋሪዎች መካከል ጠንካራ የእርስ በእርስ ግንኙነት እና የኃላፊነት ስሜትን ያጎለብታሉ።

ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር በሚደረጉ የጽዳት እንቅስቃሴዎች፣ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ፕሮግራሞች እና በሌሎች ማኅበረሰብ አቀፍ እንቅስቃሴዎች ላይ ዜጎች የመሳተፍ ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ የማኅበረሰብ ተሳትፎ እና ትብብር እንዲጨምር ዕድል ይፈጥራል።

8. ድንገተኛ አደጋዎችን መቋቋም - ንፁህ ከተሞች እንደ ወረርሽኝ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ለመሰሉ የሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች እና ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ናቸው።

በከተሞቹ በሚገባ የተያዙ መሠረተ ልማቶች፣ ቀልጣፋ የቆሻሻ አወጋገድ እና የተቀናጁ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሥርዓቶች በሕዝብ ጤና ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ ይቀንሳሉ።

ለከተሞች ንፅህና ቅድሚያ በመስጠት ጤናማ፣ ደስተኛ እና ጠንካራ ትውልድ መፍጠር ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም “ፅዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ቃል የማኅበረሰቡ የፅዳት ባህል ክብርን የጠበቀ ለማድረግ ያለመ ንቅናቄ ይፋ አድርገዋል።

ለዚህ ተግባር የሚውል የ“ፅዱ ኢትዮጵያ” የዲጂታል ቴሌቶን ተጀምሯል።

ንፁህና ፅዱ ከተማን መፍጠር የማዘጋጃ ቤት አልያም የባለሥልጣናት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎችን ንቁ ተሳትፎ እና የጋራ ጥረት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያዊያንም ለንቅናቄው በጎ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

እስከአሁን በ#ፅዱኢትዮጵያ ቴሌቶኑ ያልተሳተፉ ዜጎችም በመጪዎቹ ቀናት እና ሳምንታትም እንዲቀላቀሉ ጥሪ መቅረቡ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
👍2
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የባለጉዳይ የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ይፋ አደረገ።

*አዳስ አበባ*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተቋሙ ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን መቀበል የሚያስችል ባር ኮድ የያዘ ፎርም ይፋ አደረገ።

ተቋሙ የአሰራር ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ከመቼውም ጊዜ በላይ የህብረተሰብ አገልጋይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ይፋ በማድረጉ ማንኛውም ባለጉዳይ በተቋሙ ላይ ያለውን ቅሬታ በቀላሉ በማቅረብ ቅሬታው መፈታቱን መከታተል እንደሚች ያሳወቁት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ናቸው።

አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 9995 የተባለ ነፃ የስልክ መስመር እንዳለውና የተለያዩ ጥቆማዎችን እንደሚቀበልና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።
👍1
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በየ 15 ቀኑ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚታተም አምድ በዚህ ሳምንት ለመዲናዎ መዘመን የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በሚል ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችና ሌሎች.... ተሰንዶበታል።
እንድታነቡት ተጋዛችኋል :-