የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.37K subscribers
2.67K photos
5 videos
1 file
63 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለስልጣኑ የሁለተኛ ዙር የወታደራዊ እና የስነምግባር ሰልጣኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ወደ ማሰልጠኛ በሰላም ገብተዋል ።

17/03/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የሁለተኛ ዙር የአካል ብቃት እና የስነ-ምግባር ስልጠና ሰልጣኝ አመራሮች እና ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰላም ደረሱ።

ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

የንድፈ ሀሳብ እና በወታደራዊ ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይና በቀጣይ ዙሮች ስልጠናው እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
13👍5
ባለስልጣኑ በወቅታዊ የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ከክፍለ ከተማ ተወካዮችና እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የስራ ግምገማ አካሄደ

ህዳር 17/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አደራሽ የግምገማ መድረክ ተካሄደ ።

ግምገማውን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህን ስራዎች ስንሰራ አመራሩ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩን በሚገባ ማወቅ እንዳለበት በተለይም ማህበረሰቡ ስለ ደንብ ማስከበር ያለውን ያለውን ግንዛቤ ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።

አያይዘውም በደንብ ጥስቶች ዙርያ እርማጃ ከመውሰድ ይልቅ ህጉ ምን ይላል የሚለውን ለማህበረሰቡ በመድረክ በቤት ለቤት የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መሰራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ዋና ስራ አስኪያጁ የሽፍት አስተባባሪዎች እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በአፈር አዳይቱ እና በሰንዳፋ ማስልጠኛ ማዕከሎች በስነምግባር ፣ በአቋምና በእውቀት ላይ ተመስርተው ስራዎችን እንዲሰሩ ስልጠናዎች እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮቹ በደንብ ጥሰቶች ዙርያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ሲሰሩ ለማህበረሰቡ የሚያስከትለውን ጉዳት በማሳወቅና ደንቡን በማስረዳት በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ እና በማህበራዊ ሚድያዎች የባለስልጣኑን ገፅታ መገንባት እንደሚገባ የመሳሰሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

በመጨረሻም በባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡
ባለስልጣኑ "የመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ"በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ አካሄደ

20/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ "በሚል መሪ ሀሳብ በ2018 በጀት ዓመት የሚከናወኑ የአጭር ጊዜ እቅድ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሀገራችንን እንዲሁም ከተማችን እያሳዩ የሚገኘውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠልና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በስልጠናው በጨበጥነው ሞራል በከፍተኛ ተነሳሽነትና በላቀ ቁርጠኝነት ወደ ስራ መግባት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል ።

አክለውም የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን በማስፋት የግንዛቤ ስራዎች በማጠናከርና በማስፋት የቁጥጥርና የእርምጃ አወሳሰድ ተግባራትን መቀነስ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ የ2018 በጀት ዓመት የአጭር ጊዜ እቅድ በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ አቅርበዋል ።

በከተማችን የደንብ መተላለፍ በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም የስልጠና ግንዛቤ ስራዎችን በማጠናከር የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊና ተደራሽ በማድረግ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እና ባለቤት በማድረግ ህገወጥነት በከተማችን እንዲቀንስ ማስቻል እንደሚገባ በሰነዱ ተገልጿል ።

የሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታገል የ 7/24 የስራ ባህልን በማዳበር በበጀት ዓመቱ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የቀጣይ ሰራዎች ላይ በእቅድ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን የባለሥልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

በማጠቃለያው አመራሩና ሰራተኛው በስነ-ምግባር የታነፀ ከብልሹ አሰራር የጸዳ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መፈጸም የሚችል ለሌሎች አካላትና በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች አርአያ በመሆን ሌት ተቀን መትጋት እንደሚገባ ዋና ስራ አስኪያጁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች
🥰2👍1