የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.24K subscribers
2.37K photos
5 videos
1 file
57 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ "18ተኛውን የሠንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት አከበረ።

03/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጲያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ሉአላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ቃል 18ተኛውን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀንን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ ኦፊሰሮችና መላሙ የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት አከበረ።

ክብረ-በዓሉ በብሄራዊ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የዘንድሮውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን የህዳሴ ግድብ እና ለሎች በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ስራ በገቡበት ወቅትና እንዲሁም ተቋማችን ከፍተኛ ውጤት ባስመዘገበበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ሰንደቅ ዓላማችን የክብራችንና የሉአላዊነት መገለጫ አርማችን እንደመሆኑ መጠን ይህንን ቀን ስናከብር አባቶቻችን በደም ጠብቀው ያቆዩልንን ሀገር በስኬት የማንሰራራትና የከፍታ ዘመን የምናስቀጥልበትና በቁርጠኝነት የምንሰራበት ሊሆን እንደሚገባ በአፅንኦት ገልጸዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በወርቃማ የሰኞ ማለዳ የአብሮነት መድረክ በከተማ ደረጃ ተሸላሚ ለሆኑ ዳይሬክቶሬቶች እውቅና ሰጠ

ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዘወትር ሰኞ ማለዳ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀት ተሞክሮ የሚጋራበት የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሂድዋል፡፡

በአብሮነት መድረኩ ላይ ከኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ንጋቱ "የተግባቦት ክህሎት" በሚል ርዕስ ሰነድ በማቅረብ የህይወት ፣ የዕውቀትና የስራ ተሞክሮአቸውን በመድረኩ አጋርተዋል

በመድረኩ የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ የአንኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ስለመድረኩ አስፈላጊነት ፣ ስለዓላማው ፣ ስላጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ በማቅረብ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት ውይይት ተካሂዷል።

የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እና የስ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶረት በ2017 ዓ.ም በተደረገ ምዘና በከተማው ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር በመወዳደር ባስመዘገቡት ስኬትና የላቀ አፈፃፀም "ዕውቅና በላቀ ውጤት " በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ዳይሬክቶሬቶቹ ለስኬት ብቁ ያደረጉ ዋና ዋና ተግባራትን የሚገልፅ ሰነድ በማቅረብ ለዚህ ስኬት የበቁትን የሁለት ዳይሬክቶረቶች ዕውቅናና የመስጠትና ሰርተፍኬት የማበርከት መርሀ-ግብር ተከናውኗል።

በማጠቃለያው ላይ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ለሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እንኳን ደስ አላችሁ መልክት በማስተላለፍ የሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እዚህ ደረጃ ላይ መድረስና እውቅና መሰጠቱ ለሌሎች በባለስልጣኑ ስር ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለቀጣይ በላቀ ትጋት ስራዎች ሊሰሩ ይገባል የሚል መልክትን በማስተላለፍ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍5
ባለስልጣኑ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀው የፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት 300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

ጥቅምት 03/2018 ዓ/ም
**አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀው የፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት የ300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ ።

ድርጅቱ ፍሳሽ ቆሻሻን ባልተገባ መንገድ ወደ ወንዝ ሲለቅ በመገኘቱ ቅጣቱ ተላልፎበታል ።

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት ጠንካራ ክትትል በማድረግ
አስታውቋል ።

ባለስልጣኑ ተቋማትና ግለሰቦች ማንኛውም አይነት ቆሻሻ ወደ ወንዝና የወንዞች ዳርቻ ከመልቀቅ እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ደንብ የሚተላለፉ ግለሰቦችና ተቋማትን እንደማይታገስና እርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡

መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
5👍5👏1
ባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ይገኛል

ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር ባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አደራሽ በመገምገም ላይ ይገኛል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን ገለፀዋል።

አያይዘውም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር በሰው ተኮር ተግባራት በአቅመ ደካማ በቤት እድሳት፣በደም ልገሳ በችግኝ ተከላ እና ማዕድ የማጋራት ስራዎች በሩብ ዓመቱ መከናወን መቻሉን ገልፀዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው
፡፡
8👍6👏4
ባለስልጣኑ በከተማዋ በ83.8% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር ባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አደራሽ የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን በመግለፅ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንፃር የደንብ ጥሰት በ83.8% መቀነሱን ገልፀዋል።

በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር በሰው ተኮር ተግባራት ፣ በአቅመ ደካማ በቤት እድሳት፣በደም ልገሳ ፣ በችግኝ ተከላ እና ማዕድ የማጋራት በርካታ ስራዎች በመስራት በሩብ ዓመቱ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

በሪፖርቱ የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር እርምጃ ከመውሰድ አንፃር ፣ ከኢንሸቲብ ስራዎች፣ከግንዛቤ ፈጠራ አና ከመልካም አስተዳደር አንፃር የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ተመላክተዋል።

በሩብ አመቱ ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ገቢ በማድረግ ለከተማው ልማት እንዲውል መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በግምገማው የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ መነሻ በማድረግ በቡድን በመከፋፈል ከመልካም አስተዳደር ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከብልሹ አሰራር ፣ የደንብ ጥሰቶችን ከመቀነስ እና ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ላይ በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች አወያይነት ሰፊ ውይይት ተደርጎል።

በውይይት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል

በመጨረሻም የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን በተለይ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በትኩረት እንዲሰራና በካዮቹ ተጠያቂ እዲደረጉ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍41