የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.86K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ከእድር ምክር ቤቶች ጋር በጋራ መስራት የደንብ መተላለፍን በመከላከል ረገድ ሚናው የላቀ መሆኑ ተገለፀ።

መጋቢት 23/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ለሚገኙ እድር ምክር ቤት አመራሮች በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ግንዛቤ ፈጠረ።

የደንብ መተላለፍን በዘላቂነት ለመከላከል በከተማዋ ውስጥ ከሚገኝ አጠቃላይ ማህበረሰብ ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባና በተለይ የማህበረሰቡ እሴትና መስተጋብር አውዎንታዊ በሆነ መልኩ በሚገነባበት እድሮች ጋር ተቋሙ ሲሰራ እንደቆየና በቀጣም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዘርፉ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠርካለም ጌታሁን ገልፀዋል።

አክለውም በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

በመድረኩ በየቀጠናው ከሚገኙ የባለስልጣኑ ቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ኦፊሰሮች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ለህብረተሰቡ ግንዛቤን በማስጨበጥ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍ አስቀድሞ በመከላከል ምቹ አዲስ አበባን በጋራ መገንባት እንደሚገባ ወ/ሮ ሠርካለም ተናግረዋ።

የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን አስቀድሞ ለመከላከል በዘርፉ በርካታ የቅድመ መከላከል ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የዕድር አመራሮች በህብረተሰቡ ውስጥ ያላችሁን ተደማጭነት በመጠቀም ከተቋሙ ጎን ተሰልፋችሁ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ እየቀረፍን ውጤታማ ስራዎችን እናከናውናለን በማለት ማንኛውንም ጥቆማዎች በተቋሙ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ላይ እንዲጠቁሙ አስታውሰዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ከእኛ ጋር በይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት እና አዲሱ ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ግንዛቤ መፈጠሩ እጅግ የሚበረታታ ነው፤ እኛም በማህበረሰባችን ዘንድ ያለንን ተደማጭነት በመጠቀም የሚጠበቅብንን ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለፅ አልፎ አልፎ የስነ-ምግባር ጉድለት የሚስተዋልባቸው ኦፊሰሮች ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ነው።
👍21
ዛሬ ማለዳ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ለውጥ 6ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፋቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል።

ለውጡ ሀገራችንን ከፍ ባደረጉ ታላላቅ ስራዎች እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ከፍ ብሎ አንድነት የደመቀበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምረን ያጠናቀቅንበት፣ የቱሪዝም መስህቦች እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ የጀመርናቸው ለሰው ልጅ ቅድሚያ በሰጠው ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶች የኑሮ ሸክም ቀልሎ እምባቸው ታብሶ ተስፋቸው የለመለመበት ነው።
በቀጣይም መዲናችንን የብልጽግና ተምሳሌት፣ እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል የማድረግ ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ሁሌም ድጋፋቸው ላልተለየን የከተማችን ነዋሪዎች አክብሮታችን ከፍ ያለ ነው፤ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ